በከፍተኛ የህገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ናቸው የተባሉ 387 ዓለም ዓቀፍ ተጠርታሪዎችን መያዟን የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ አስታወቀ ዜናው ህገወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪ ናቸው የተባሉት 387 ተጠርጣሪዎች አገርና ዜግነትን ይፋ አላደረገም። የተጠርጣሪዎቹ ስምና አገር ይፋ ባይሆንም ዜናው በአገር ቤት መነጋገሪያ ሆኗል።
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በሀገሪቱ ቀደም ሲል 521 ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ወንጀሎች ይፋ ተደርገው በጥምረት ክትትል ሲደረግባቸው ነበር።
ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውሩ የተሳተፉ 387 ግለሰቦች ከዓለም አቀፍ የሕግ አስከባሪ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አመላክቷል፡፡ ምርመራው በቅንጅት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።
በሕገ ወጥ ገንዘብ አዘዋዋሪዎች ሲንቀሳቀስ የነበረ ከ4 ቢሊየን ድርሃም በላይ ገንዘብ በመንግስት መወረሱን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ም/ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሌ/ጄ ሼክ ሳይፍ ቢን ዛይድ አል ናህያን ሕገ ወጦችን ለመቆጣጠር የተወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል፡፡
እርምጃው የሀገሪቱን ብሄራዊ ደህንነትከማስጠበቅ ባለፈ በእድገት ጎዳና ላይ የጀመረችውን ጉዞ ለማስቀጥ ል ሚናው ከፍተኛ ነው ማለታቸውን ገልፍ ቱ ዴይ ዘግቧል፡፡
ምንም እንኳን የተጠርጣሪዎቹ ስምና ዜግነት ይፋ ባይሆንም ዜናው በአገር ውስጥ መነጋገሪያ ሆኗል። በርካታ በሙስና ወንጀል የሚጠረጠሩና ከውጭ ገንዘብ ምንዛሬና ኤሊሲ ጋር በተያያዘ በርካታ ኢትዮጵያዊያን በኢመሬትስ ስለሚንቀሳቀሱ፣ መንግስትም ከኢምሬትስ መንግስት ጋር ጥብቅ ወዳጅነት ስላለው ዜናው ምን አስከትሎ ይመጣ ይሆን የሚል ጉጉትም አሳድሯል።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop