ዓለም የተቀባበለው አስደንጋጩ ዜና 244 ተሳፋሪዎችን ይዞ ከሕንድ አህመዳባድ ከተማ በመነሳት በረራ የጀመረው አውሮፕላን መከስከሱ ነበር። መዳረሻው ሎንደን ጋትዊክ አውሮፕላን ማረፊያ ያደረገው ንብርተነቱ የኤር ኢንዲያ የሆነው አውሮፕላን አደጋው እንደደረሰበት “ዛሬ ከአህመዳባድ ለንደን ጋትዊክን የሚበረው AI 171 አደጋ አጋጥሞታል” በማለት ባለንብረቱ አስታውቋል።
ተሰፋሪዎቹ ባለቁበት በዚህ አደጋ አሰቃቂ አደጋ ተዓምር የሆነው ዜና ተሰምቷል። ዜናውም የቪሽቫሽ ኩማር ራሜሽ መትረፍ ነው። በትውልደ ህንዳዊ፣ በዜኘት ደግሞ እንግሊዛዊ የሆነው ይህ ተሳፋሪ መትረፉን የዓለም ዜናዎች አውታሮች እየተቀባበሉት ነው።

ግለሰቡ ቀደም ብሎ ከእንግሊዝ ዘመዶቹን ለመጠየቅ ወደ ህንድ ያቀና እንደነበር ተነግሯል። በዛሬው ዕለት በህንድ ከተከሰተው አሰቃቂ የአውሮፕላን አደጋ መትረፉን አስመልክቶ ቪሽቫሽ ኩማር ራሜሽ ለሂንዱስታን ታይምስ ምስክረነቱን ሰጥቷል።
ቪሽቫሽ ከህንድ ወደ ለንደን እየተመለሰ በነበረበት ወቅት አሰቃቂው አደጋ ሲደርስ የተቀመተው በመስኮት በኩል መሆኑ ከአደጋው ህይወቱ እንዲተርፍ ምክንያት መሆኑን ተናግሯል፡፡
አውሮፕላኑ መሬት ከለቀቀ 30 ሴኮንድ በኋላ ከፍተኛ ድምፅ ማሰማት መጀመሩን እና ወዲያው በሴኮንዶች ልዩነት መከስከሱን ለሂንዱስታን ታይምስ ያስረዳው ቪሽቫሽ ኩማር ፣ አደጋው ሲደርስ ራሱን ስቶ እንደነበር ይናገራል።
“ከአውሮፕላኑ መከስከስ በኋላ ራሴን ስቼ ነበር፤ ነገር ግን ስነቃ የሞቱ ሰዎች አስከሬን አጠገቤ ነበር፤ የሞቱ ሰዎችን አስከሬን ሳይ ተነስቼ ሮጥኩኝ” በማለት ቪሽቫሽ ኩማር ከአደጋው ከተረፈ በሁዋላ ተናግሯል።
ቪሽቫሽ ኩማር በአደጋው ሰውነቱ ላይ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል። ወዲያውም ሰዎች ደርሰው ወደ ሆስፒታል እንደወሰዱት እና ህክምናውን እየተከታተለ እንደሚገኝ ተዘግቧል።
ተዓምር ያተረፈው ቪሽቫሽ ኩማር በእግሩ፣ በደረቱ እና በዓይኖቹ ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰበት የተለያዩ ሚዲያዎች ምስል አስደግፈው ጽፈዋል።
ይህ ሲታተም የ204 ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን፣ ቀሪ ሰዎችን የመፈለግ ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ከስፍራው የሚወጡ ተከታታይ መረጃዎች ያስረዳሉ። አውሮፕላኑ እንድተከሰከሰ የወጣው ዜና ይህን ይመስል ነብወር። ከስር ያንብቡ።
ዛሬ ረፋድ ላይ ከህንድ አህመዳባድ አየር ማረፊያ ወደ ለንደን ጉዞ ለማድረግ ከተነሳ በኋላ በሰከንዶች ልዩነት በመከስከሱ፤ ለበርካታ መንገደኞች ህይወት ማለፍ ምክንያት ከሆነው አስከፊ የአውሮፕላን አደጋ በኋላ አየር መንገዱ በደረሰው አደጋ ማዘኑን ገልጿል።

የኤር ኢንዲያ ባለቤት የሆነው ታታ ኩባንያ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ቤተሰቦች ለእያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን የህንድ ሩፒ ወይም 116 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገደማ ካሳ እንደሚሰጥ በድረገጹ ባወጣው የሀዘን መግለጫ መልዕክት ላይ አስታውቋል።
ከሰዓታት በፊት የመከስከስ አደጋ በደረሰበት አውሮፕላን ውስጥ ከተሳፈሩት ከ242 በላይ ተሳፋሪዎች ሰዎች መካከል አንድ ሰው በህይወት የተረፈ ሲሆን፤ ሌሎች በህይወት የተረፉ መንገደኞችን የማግኘቱ ተስፋ የመነመነ እንደሆነ ዘ ታይምስ ኦፍ ኢንዲያ የአህመዳባድ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽነርን መግለጫ ጠቅሶ ዘግቧል።
የአካባቢው ፖሊስ አዛዥ ለቢቢሲ እንደተናገሩት እስካሁን 204 አስከሬኖች ተገኝተዋል። ከተገኙት መካከል ምን ያህሉ በአውሮፕላኑ ውስጥ እንደነበሩ እንዲሁም አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ወቅት መሬት ላይ እንደነበሩ መለየት ግን አልተቻለም።
በሕንድ ከተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የመቀመጫ ቁጥር 11A ላይ የተቀመጠው ተሳፋሪ በሕይወት መገኝቱ ብዙዎችን አስገርሟል። በታታ ግሩፕ ባለቤትነት የሚመራው ኤር ኢንዲያ፤ 69 ዘመናዊ ኤርባስ አውሮፕላኖችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ205 በላይ አውሮፕላኖች አሉት።
አየር መንገዱ በህንድ ውስጥ ካሉ አየር መንገዶች በግንባር ቀደምትነት የሚነሳ ሲሆን በ93 ዓመት ታሪኩ ከገጠሙት አደጋዎች የዛሬው የከፋ ነው ተብሏል።