የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ከህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያ ለተሰባሰቡ ጥያቄዎች በዝርዝር ምላሽ ሰጥተዋል።
በአጠቃላይ ከ1200 በላይ ጥያቄዎች እንደቀረበላቸው የጠቆሙት ወ/ት ብርቱካን፤ አንደኛው ጥያቄ፡- የድሬድዋና አዲስ አበባ የምርጫ ቀን ከሌላው የተለየበት ቀንን የተመለከተ ሲሆን ቀኑ የተለያየው በተለየ ፖለቲካዊ ምክንያት አይደለም። ቀኑ የተለየው የሁለቱ ከተሞች የምርጫ ወረዳዎች ከዋናው ምርጫ ጋር ለማስፈፀም አመቺ ባለመሆኑ ብቻ ነው ብለዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሰብሳቢዋ የፀጥታ መድረክ ባለባቸው ቦታዎች ስለሚኖር የምርጫ ሁኔታ፣ ፅ/ቤት ተዘግቶብናል የሚሉ ፓርቲዎች አቤቱታ፣ ስለምርጫው ቅድመ ዝግጅት ለ1 ሰዓት ከ16 ደቂቃ በቆየው የፌስ ቡክ ማብራሪያቸው ምላሽ ሰጥተዋል።
በፀጥታ ምክንያት አስቀድሞ በትግራይ ምርጫ እንደማይደረግ መረጋገጡን ያስታወሱት ወ/ት ብርቱካን፤ በሌሎች የከፋ የፀጥታ መደፍረስ ባለባቸው አካባቢዎች ምርጫ እንደማይደረግና ቅድሚያ ለዜጎች ደህንነት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይም ኦፌኮ እና ኦነግ በኦሮሚያ ጽ/ቤቶቻቸው ስለመዘጋታቸው በተደጋጋሚ አቤቱታ ማቅረባቸውን ነገር ግን ክልሉ ሲጠየቅ የዘጋው ፅ/ቤት አለመኖሩን ምላሽ እንደሚሰጥና ፓርቲዎቹ የት አካባቢ ምላሽ አለመስጠታቸውን አስገንዝበዋል።
ከፖለቲከኞች እስር ጋር በተያያዘ ለቀረበላቸው ጥያቄም ጽ/ቤቶቻቸው የተዘጉባቸውን አካባቢዎች አድራሻ እንዲሰጡ ተጠይቀው ምላሽ ለመስጠት ፍላጎት አለማሳየታቸውን አስረድተዋል። ወ/ት ብርቱካን ደግሞ፤ በህግ በተያዘ ጉዳይ ቦርዱ ጣልቃ ገብቶ መፍትሄ መስጠት እንደማይችል ሰብሳቢዋ አስገንዝበዋል።
ቦርዱ ሁሉንም የፖለቲካ ድርጅቶች በገለልተኛነት ለማገልገል የሚያስችለውን ቁመና መላበሱን የገለፁት ወ/ት ብርቱካን፤ ተጨባጭ ማስረጃ ለቀረቡባቸው አቤቱታዎች ፈጣን ምላሽ እየሰጠ መሆኑንም አውስተዋል።
ምርጫ ቦርድ ላይ ህብረተሰቡ እምነት እንዲኖረው የጠየቁት ወ/ት ብርቱካን፤ “በኛ ላይ እምነት ያጣችሁ ለምን እንዳጣችሁ ብናውቅ ጥሩ ነው” ብለዋል።
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security