ኢዜማን ወክለው በአዲስ አበባ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚወዳደሩት እጩዎች የታወቁ ሲሆን፤ ባልደራስ ከመኢአድና አብን ጋር በምርጫው እርስ በእርስ ላለመፎካከር ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
በዘንድሮ ምርጫ ኢዜማን ወክለው በየወረዳው ለፓርላማ ከሚወዳደሩት 23 እጩዎች መካከል የፓርቲው መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ የፓርቲው ም/መሪ አንዷለም አራጌ፣ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ የኢኮኖሚ ምሁሩ ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌና አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን ተጠቃሽ ናቸው።
ፓርቲውን ወክለው ለፓርላማ የሚወዳደሩ 23 እጩዎች በየወረዳው ሲደላደሉም፣ ምርጫ ወረዳ 1/9 አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን፣ ምርጫ ወረዳ 2/14 አቶ ደረጀ ተክሌ፣ ምርጫ ወረዳ 3 ዶ/ር ጥላሁን ገብረ ሕይወት፣ ምርጫ ወረዳ 4 አቶ ተክሌ በቀለ፣ ምርጫ ወረዳ 5 አቶ አበበ ተሻለ፣ ምርጫ ወረዳ 6 አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ምርጫ ወረዳ 7 ወ/ት ናርዶስ ስለሺ፣ ምርጫ ወረዳ 8 ከውሰር ኢድሪስ፣ ምርጫ ወረዳ 10 አቶ ዘላለም ወርቅአገኘሁ፣ ምርጫ ወረዳ 11 አቶ የጁ አልጋው ጀመረ፣ ምርጫ ወረዳ 12/13 አቶ አንዷለም አራጌ፣ ምርጫ ወረዳ 15 ዶ/ር በላይ እጅጉ፣ ምርጫ ወረዳ 16 ዶ/ር አንማው አንተነህ፣ ምርጫ ወረዳ 17 ዶ/ር ዳዊት አባተ፣ ምርጫ ወረዳ 18 አቶ ወንድወሰን ተሾመ፣ ምርጫ ወረዳ 19 አቶ በላይ ደስታ፣ ምርጫ ወረዳ 20 አቶ ባንትይገኝ ደስታ፣ ምርጫ ወረዳ 21/22 አቶ ብርሃኑ ወልደ ጊዮርጊስ፣ ምርጫ ወረዳ 23 ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ፣ ወረዳ 24 ፕ/ር በፍቃዱ ደግፌ፣ ምርጫ ወረዳ 25 አቶ እንዳልካቸው ፈቃደ፣ ምርጫ ወረዳ 26/27 ዶ/ር መለስ ገብረጊዮርጊስ፣ ምርጫ ወረዳ 28 ዶ/ር ባንትይገኝ ታምራት መሆናቸው ታውቋል።
አዲስ አበባ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ኢዜማ፤ ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ካቀረባቸው 138 እጩዎች መካከል ታዋቂው የኢኮኖሚ ተንታኝና የፓን አፍሪካ ንግድ ም/ቤት ፕሬዚዳንት፣ አቶ ክቡር ገና ተጠቃሽ ናቸው።
አዲስ አበባ ራሷን የቻለች ክልል መሆን አለባት በሚል የሚሟገተውና በእስር ላይ በሚገኘው አቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በበኩሉ፤ ለአዲስ አበባ ም/ቤት 138 እንዲሁም ለፓርላማ 23 እጩዎች ማዘጋጀቱን ገልጾ፣ዝርዝራቸውን ከሰሞኑ ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስታውቋል።
ባልደራስ፤ ከመኢአድና አብን ጋር እርስ በእርስ ባለመፎካከር፣ በአንጻሩ በምርጫው በትብብር ለመስራት የፓለቲካ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለአዲስ አድማስ ተናግረዋል። በዚህም መሰረት ባልደራስ እጩ ባቀረበባቸው ወረዳዎች የአብንና የመኢአድ ድርሻ ድጋፍ መስጠት ሲሆን፤ ባልደራስ በማይወዳደርባቸውና አብንና መኢአድ በሚወዳደሩባቸው አካባቢዎች ደግሞ ባልደራስ ትብብርና ድጋፍ እንደሚያደርግ ሃላፊው አብራርተዋል፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security