የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ከዘንድሮ አገራዊ ምርጫ ሙሉ ለሙሉ መውጣቱን ያረጋገጠ ሲሆን በእነ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው ኦነግ በበኩሉ፤ በቅርቡ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ በምርጫው የመሳተፍ ፍላጎትና ዝግጁነት እንዳለው ለአዲስ አድማስ አስታውቋል።
ኦነግ ምናልባት በቀጣይ ሳምንት ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጎ የድርጅቱን ህልውና ካስጠበቀ በኋላ፣ የምርጫ ቦርድ ትብብርና በጎ ፈቃደኝነት ከተገኘ፣ እጩዎች አቅርቦ በምርጫው ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑን የፓርቲው ቃል አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ገልጸዋል።
በአመራር ቀውስ ምክንያት እስካሁን ለምርጫው እጩዎች ማቅረብ እንዳልቻለ የሚገልጸው በእነ አቶ አራርሶ የሚመራው ኦነግ፤ የአመራር ቀውሱን መፍቻው መንገድ ጠቅላላ ጉባኤ ስለሆነ ጉባኤውን ለማካሄድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑንና በቅርቡ ጉባኤውን አድርጎ ወደ ምርጫው እንደሚመለስ አስታውቋል፡፡
ምርጫ ቦርድ ለመጨረሻ ጊዜ ያራዘመው የእጩዎች ምዝገባ ከትናንት በስቲያ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ያበቃ ቢሆንም በአመራር ቀውስ ውስጥ ለቆየውና ችግሩን ለመፍታት ጥረት እያደረገ ለሚገኘው ኦነግ፣ በልዩ ሁኔታ ጊዜ ተራዝሞለት እጩዎች ለማቅረብ ይፈቀድለት ዘንድ ለቦርዱ ጥያቄ ማቅረቡን አቶ ቀጀላ ገልጸዋል፡፡
ለጥያቄው እስካሁን ቁርጥ ያለ ምላሽ ከቦርዱ ያላገኘ ቢሆንም ፣ጉዳዩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይታያል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጹት አቶ ቀጄላ፤ ኦነግ በእርግጠኝነት በምርጫ መሳተፍ አለመሳተፉን የሚያረጋግጠው የምርጫ ቦርድ ተባባሪነት ነው ብለዋል። ቦርዱ ጊዜ ሰጥቶን እጩ እንድናቀርብ ከፈቀደልን እናስመዘግባለን ያሉት አቶ ቀጄላ፤ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ እስካሁን ድረስ ተቀራርቦ በመነጋገር ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት እንዳላሳዩም ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል፤ ቀደም ሲል በምርጫው እርስ በእርስ ላለመፎካከር ከኦነግ ጋር ከስምምነት ላይ ደርሶ የነበረው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ፤ በምርጫው እንደማይሳተፍ ሰሞኑን በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።
በኦሮሚያ ጽ/ቤቶች እንደተዘጉበት፣ ወሳኝ አመራሮችን ጨምሮ በርካታ አባላቱ እንደታሰሩበት ሲገልጽ የቆየው ኦፌኮ፤ የፖለቲካ ምህዳሩ በእስርና ወከባ በጠበበት ሁኔታ ለምርጫ ውድድር መቅረብ አልችልም ሲል አስታውቋል።
ኦፌኮ እስከ ረቡዕ ዕለት አንድም እጩ አለማስመዝገቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከምርጫው በፊት የታሰሩ ፖለቲከኞች ሁሉ ተለቀው፣ የብሔራዊ መግባባትና እርቀ ሰላም ውይይት መካሄድ እንዳለበትም ፓርቲው በመግለጫው አስገንዝቧል።
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security