ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱን አመለከቱ።
ዶክተር ሚዛን ኪሮስ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት ፣ ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በጽኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆናለች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በሀገሪቱ የኮቪድ -19 ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መጥቷል፡፡
በሽታው ያለባቸው እና በጽኑ ህክምና ላይ የሚገኙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ በየጊዜው እየጨመረ መምጣት የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው ፡፡ ይህም የበሽታው ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቋሚ ነው ብለዋል፡፡
የምርመራ ውጤቶች ከቀን ቀን የሚሊያዩ ቢሆንም ባለፉት ሶስት ሳምንታት በተለይ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡን አመልክተው፣ በሚፈለገው ልክ ምርመራዎች እየተካሄዱ ባለመሆናቸው እንጂ በሌሎች ክልሎችም የበሸታው ስርጭት እየጨመረ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ምልክቶች እንዳሉ አመልክተዋል። የቫይረሱን አጠቃላይ ትክክለኛ ስርጭት ለማወቅም በቅርቡ ሰፊ ሀገራዊ ጥናት እንደሚካሄድም ጠቁመዋል፡፡
(ኢ ፕ ድ)
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል