የጎንደር ከተማን በተለያዩ አቅጣጫዎች ለማጥቃት ተኩስ ከፍተው የነበሩ ታጣቂዎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች መመለሳቸውን የጎንደር ከተማ ወጣቶችና የከተማ አስተዳደሩ ዐስታወቁ።
ታጣቂዎቹ ከትናንት በስትያና ትናንት የጎንደር ከተማን የሽብር ማዕከል ለማድረግ በሦስት አቅጣጫዎች ተኩስ ከፍተው ጉዳት ማድረሳቸውን በጎንደር የአማራ ወጣቶች ማኅበር ፕሬዚደንት ተስፋ ታምራት ለዶይቼ ቬለ ተናግሯል። «ጎንደርን የሽብር ቀጠና ለማድረግ ሥራ ተሠርቶ ነበር። ድንበር አካባቢ ሰው በማገት እየተደራደሩ ገንዘብ ሲቀበሉ ቆዩ።
አሁን ደግሞ በሕዝብ ላይ ግልጽ የኾነ ጦርነት ከፍተው በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንዲሁም የአካባቢው የፀጥታ ኃይል ሕልማቸው አልተሳካላቸውም። አሁን ዛሬ ነው፤ ጥሩ ሠላም ነው።»የጎንደር ከተማ የሰላምና ደህንነት መምሪያ ኃላፊ አቶ ናትናኤል ጎሹ በበኩላቸው በስም ያልጠቀሷቸውና «የተደራጁ ቡድኖች» ያሏቸው ኃይሎች በሦስት የጎንደር ከተማ አቅጣጫዎች ጥቃት ከፍተው በመንግሥት ታጣቂዎች መመለሳቸውን አብራርተዋል።
«አንደኛው ቁስቋም ይባላል፣ አንዱ ብላጅግ ዳብርቃ ነው፣ ሌላኛው ደግሞ አዘዞ ሳይድ (አቅጣጫ)፣ በእነዚህ ሦስቱ ቦታዎች፣ ያው ቁስቋም ትንሽ ጠንከር ያለ ነበር። በርከት ያለ የጥፋት ኃይል ገብቶ ከተማውን የማጥቃት ፍላጎት ነበረው። ይህን ያህል ሕይወት ጠፋና ይህን ያህል ቆሰለ ምናምን እንደዚህ የምጠቅሰው ነገር አይኖረኝም፣ ግን የተቃጠሉ ቤቶች አሉ ዳር ወጣ ወጣ ብለው ያሉ።
ድርጊቱን የፈፀመውን ሰው በክትትል አንዳንዶቹን በቁጥጥር ስር አውለናል፤ ክትትል እያደረግን ነው።»በነበረው የተኩስ ልውውጥ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰና የታጣቂዎችን ማንነት በተመለከተ ዶይቼ ቬለ የጠየቃቸው አቶ ናትናኤል «በጥናት ይመለሳል» የሚል ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል። አሁን የጎንደር ከተማና አካባቢው ሰላም እንደሆነ መምሪያ ኃላፊው ማመልከታቸውን የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን የላከልን ዜና ይጠቁማል።
DW Amharic
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው።… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ