ኢትዮጵያ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና ለፕሬስ ነፃነት መከበር የማይናወጥ አቋም ያላት መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነት መብቶች በሕገ-መንግሥቱ የተረጋገጡ እሴቶች ናቸው ያለው ባለሥልጣኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት እነዚህን እሴቶች ለመጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን በድርጊት ያረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል። አሁን በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ወደ ሥልጣን እንደመጣ በቀዳሚነት የወሰደው እርምጃ ጋዜጠኞችን እና የፖለቲካ እስረኞችን መፍታት እንደነበርም በምሳሌነት አንስቷል።
የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች የመረጃ ተደራሽነትን እንዲያገኙ ለማስቻልም ለበርካታ ዓመታት ተጥለው የቆዩት ክልከላዎች እና እንቅፋቶች ሙሉ በሙሉ መነሳታቸውንም ጠቅሷል። በአሁኑ ሰዓትም በ129 ቋሚ ዘጋቢዎች የተወከሉ 35 የውጭ የዜና ድርጅቶች ሀገሪቱ ውስጥ እንዳሉም ባለሥልጣኑ ጠቁሟል። ከዚህ ባለፈም በትግራይ ክልል ሲካሄድ በነበረው የሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅትም ከተለያዩ ሀገራት ለተወጣጡ 82 የውጭ ጋዜጠኞች ጊዜያዊ ፈቃድ ተሰጥቶ ያለውን ሁኔታ መዘገብ የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸቱን አመላክቷል።
ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነት መብቶች በሁሉም ወገኖች መከበር ይኖርባቸዋል ያለው የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን፣ ጋዜጠኞቹ የግጭት ዘገባዎችን በተመለከተ ሁኔታውን በሚገልጽ መልኩ ሙያዊ የሆኑ የአዘጋገብ ደንቦችን አክብረው ይዘግባሉ የሚል እምነት እንደነበረው አውስቷል። በየትኛውም ዓለም እንደሚደረገው ሁሉ ወታደራዊ ዘመቻ በሚካሄድበት አካባቢ ገደብ እንደሚጣል በመግለጽም፣ ፈቃድ የተሰጣቸው የውጭ ዘጋቢዎችም ይህንኑ እውነታ አክብረው እና ጠብቀው ይሠራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ የሕግ ጥሰት ሲያጋጥም በየትኛውም የዓለም ክፍል እንደሚደረገው ሁሉ ባለሥልጣኑ ሕግን የማስከበር ኃላፊነቱን የመወጣት ግዴታ እንዳለበት አስገንዝቧል። በዚሁ አግባብ ዓለም አቀፍ ተሞክሮን በመከተል በትብብር ለመሥራት እና ለዘጋቢዎች በተቻለ መጠን ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኑን ባለሥልጣኑ አመልክቷል። አሁንም ቢሆን መንግሥት ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ እና የፕሬስ ነፃነትን መከበር በተመለከተ የያዘው አቋም የማይናወጥ መሆኑን ገልጾ፣ “ሀገሪቱም ሆነች ባለሥልጣኑ በቅንነት ሥራቸውን የሚሠሩ ጋዜጠኞችን ለማስተናገድ ዝግጁ ናቸው” ሲል ገልጿል። ( ኢዜአ)
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም