ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚ ጉዳይ ጥብቅ ትሥሥር ለመፍጠር በተነደፈ ሰነድ ላይ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ እየመከሩ መሆናቸው ተሰምቷል። ምክክሩ አሜሪካ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ለማዳሸቅ እያሴረች ባለችበት ወቅት መሆኑ ዜናውን አግዝፎታል።
የመነሻው ምክክር በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ አስታውቋል። ሚኒስቴሩ ዝርዝር አላስታወቀም እንጂ ከፍተኛ የቻይና የኢኮኖሚ ጉዳይ አማካሪዎች ብምክክሩ ላይ መገኘታቸውን ኢትዮ 12 ሰምታለች።
ሚኒስቴሩ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን በበኩላቸው፥ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ አገራቸው ቁርጠኛ መሆናቸውን እንደገለጸች ከማስታወቁ በፊት የኢኮኖሚ ባለሙያዎቹ ብመን ጉዳይ ላይ እንደመከሩ ይፋ አላደረግም። ከኢትዮጵያ ወገን የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አሕመድ ከመገኘታቸው ውጪ የትኞቹ ባለስልጣናት በምክክሩ እንደተገኙ ይፋ አልሆነም።
ምክክሩ ለዋናውና ወቅታዊ ለሆነው የሜሪካ ማዕቀብ ዝግጅት በአገራቱ መሪዎች ደረጃ ለሚደረግ ስምምነት መንገድየሚጠርግ ምክክር መሆኑ ተሰምቷል። ቻይና እድገቱ መፋተን እንዳለበትና ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸው ግብአቶች በአገር ውስጥ እንድታመርት የሚያችል ድጋፍ ለመድረግ ፈቃደኛ መሆኗ ታውቋል።ከኢትዮጵያም በኤክስፖርት እቃዎቿ ላይ ማዕቀብ የሚጣልባት ከሆነ በቻይና ሰፊ ገበያ ልትመሰርት ስለምትችልበት ሁኔታ በምክክሩ እቅድ መነደፉ ተሰምቷል።
ቻይና በጸጥታው ምክር ቤት ኢትዮጵያን በገሃድ ከወገኑላት አገሮች መካከል አንዷ ናት።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም