የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግን በተደጋጋሚ ” አሸባሪ ቡድን” እያሉ የጠሩት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አስራ አራት ደቂቃ በፈጀው ንግግራቸውን ሲቋጩ የኢትዮጵያን ታሪክ በመረዳትና በማክበር ” ኢትዮጵያዊያን ወዳጆቼ ” አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን በስም ጠርተው ” አብረንዎት ነን” የሚል ማረጋገጫ ሰጡ። የተዘጋጀው የቪዛ ማእቀብ የሚፈይደው አንዳችም በጎ ነገር እንደሌለ አመልክተው ይልቁንም መርዳት እንደሚሻል፣ አብይ አህመድም ሰላሟ የተተበቀ አንድ አገር እየገነቡ እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ አመለከቱ።
” የማይገባ፣ እጅግ ስህተት የሆነ፣” ሲሉ የገለጹትን የአሜሪካ አቋም ” በፍጹም ተቀባይነት የሌለው” በማለት አራክሰው እንደማይቀበሉት ይፋ ካደረጉ በሁዋላ ” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከጎንዎት ነን” ሲሉ በአደባባይ መናገራቸው ይህን ኢትዮጵያን ለሚወዱ ሁሉ ብስራት ሆኗል።
በንግግራቸው ከኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያም ጀመሮ የነበረውን አስተዳደር የቃኙ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ” የተማሩና ብልህ መሪ” ሲሉ አድነቀዋቸዋል። አያይዘውም ” በአፍሪካ እንደ እሳቸው ያለ መሪ አላየሁም” ሲሉ አወድሰዋቸዋል።
ከለውጡ ማግስት ጀምሮ “የሽብር ቡድን” ሲሉ የጠሩት ትህነግ በርካታ ክፉ ተግባራትን ሲያከናውንና መንግስትን ሲያውክ መኖሩን አውስተው፣ በመቸረሻም ራሱን አግልሎ በኮቪድ ምክንያት ምርጫ ሲራዘም በማፈንገጥ የራሱን ምርጫ ያከናወነና ማዕከላዊ መንግስትን የማይታዘዝ ቡድን እንደነበር ጠቁመዋል።
ሴናተሩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የበለጸገች፣ አንድነቷን የጠበቀች፣ ሰላማዊ አገር ለመገንባት እየሰሩ መሆኑንን አመልክተው፣ ወደ ስልጣን ሲመጡ ቃል የገቡትን በመፈጸማቸው ምስጋና እንደሚገባቸው ተናግረዋል። እስረኞች ፈተዋል። ጋዜተኞችን ለቀዋል። የፖለቲካ ምህዳሩን አስፍተዋል ሲሉ በሽግግር ጊዜ ውስጥ ተሰሩ ያሉዋቸውን ዘርዝረዋል።
“አሸባሪው ህወሓት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ደስተኛ አልነበረም፤ ከመንግስትም ጋር አብሮ ለመስራት እንቢተኛ ሆነ፤ ተቃውሞውንም አገሪቷን በማወክ መግለጽ ጀምሮ ነበር፤ በዚህ የህወሓት ሽብር የተሞላበት አካሄድ የተነሳ የኢትዮጵያ ፓርላማ አሸባሪ ድርጅት ብሎ ሰይሞታል፤ ይህንን አሸባሪ ድርጅት የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት እኩል ማየት መጀመሩ ስህተት ነው፣ ተቀባይነት የለውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አንድነቷ የተጠበቀ ኢትዮጵያን ለማስቀጠል ጥረት እያደረጉ ነው” ሲሉ የተደመጡት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ አብይ አህመድ አምላካቸውን የሚፈሩ መሆናቸውንም አክለዋል።
ትሀንግ ካፈነገጠ በሁዋላ ሚሊሻ አደረአጅቶ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት ማጥቃቱንና መሳሪያ መዝረፉን ያስታወሱት ታዋቂው የሪፐብሊካን ፓርቲ አባል እና የኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በፕሬዚደንት ጆ ባይደን የሚመራው የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ኢትዮጵያ ላይ የጣለውን ማእቀብ ከቶውንም ፍትሃዊ ሊባል እንደማይችል አስምረውበታል። ሲቀጥሉም ኢትዮጵያ የብሄራዊ መከላከያ ሃይሏ ከተጠቃ በሁዋላ ምላሽ መስጠቷን ” እውነታው ይህ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ