የሃሰት መረጃዎችን በማሰራጨት ህዝቡን ለማደናገር የሚደረግ ሙከራ ተቀባይነት የሌለው ተራ ተግባር መሆኑን ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ፤
ከፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ሾልኮ የወጣ የፓርቲውን ፕሬዚዳንት ንግግር በማስመሰል ተፈብርኮ የተለቀቀውን ድምጽ አስመልክቶ ፓርቲው ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
መግለጫውን የሰጡት የፓርቲው የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ እንዳሉት፣ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሙሉ በሙሉ ሃሰትና የፓርቲው ፕሬዝዳንት በተለያየ መድረክ ላይ ከተናሩት ንግግሮች ተቆራርጦ የተፈበረከ ነው፡፡
አለማውም ህዝቡን ማደናገርና ህዝብና መንግስት መካከል ያለመተማመን እንዲፈጠር ብሎም ውጥረትና ያለመረጋጋት እንዲፈጠር ማድረግ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቢቂላ፣ ተግባሩንም ተቀባይነት የሌለው ሃላፊነት በማይሰማቸው አካላት የሚሰራጭ የወረደ ተግባር ነው ብለውታል፡፡
በዚህ ተግባርና ከጀርባ ያለው ድብቅ አጀንዳ ላይ የኢትዮጵያን እድገት የማይፈልጉ የውስጥ እና የውጭ አካላት እጅ እንደሚኖር ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
መሰል የሃሰት መረጃዎችን ማሰራጨት ባለፉት ቅርብ አመታት እየተለመደ መጥተዋል ያሉት ሃላፊው ህዝቡ መሰረት ከሌላቸውና ምንጫቸው ካልታወቀ መረጃ እንዲጠበቅና መረጃዎችን በጥንቃቄ እንዲመርጥ አሳስበዋል፡፡
ebc
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program… Read more: The Wars We Still Can Stop