በትግራይ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሰራተኛና ደጋፊ በሆኑ ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግድያ አይሏል። ዛሬ የትግራይ ክልል እንዳስታወቀው ኢንጂነር እምብዛ ታደሰ የተባሉ ታፍነው ከተወሰዱ በሁዋላ ተገድለው ተገኝተዋል። ግድያው እጅግ ዘግናኝ እንደነበርና አስከሬናቸውን ጅብ እንደበላው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነው ያስታወቀው።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በኢንጂነር እምብዛ ታደሰና ባለፋት ተከታታይ ወራት በክልሉ በንፁሐን አገልግሎት ሰጪ ሰራተኞች ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችን በጥብቅ እንደሚያወግዝ አስታውቆ ይፋ እንዳደረገው የሟቹ አስከሬን የተገኘው በአሰሳ ነው።
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ከሁለት ቀናት በፊት በመቐለ ከተማ በግምት ከቀኑ ሰባት ሰዓት በኃላ ወጣት እንጅነር እምብዛ ታደሰ ከቢሮ ወደ መቀሌ አሉላ አባ ነጋ የአየር ማረፊያ ለመጓዝ በዝግጅት አልይ እንዳለ ለግዜው ማንነታቸው ባልታወቁ አፋኞች ተፍንነዋል።
በሃይል ታፍነው ከትወስዱ በሁዋላ ደብዛቸው ጠፍቶ ነበር። በፌደራል ፖሊስ የፀጥታ ሐይሎች በተከናወነ አሰሳ ኢንጂነር እምብዛ በጨካኝ የከተማ ሽብር ተልእኮ አስፈፃሚ ወንጀለኞች በዓይደር ልዩ ስሙ ” ማረሚያ ቤት” በተባለ ስፍራ ተገድለው ተጥለው ተገኝተዋል።
ፖሊስ ያገኘው አስከሬን ጅቦች እንዲበሉት ከተጣለበት ስፍራ ትላንት ከረፋዱ አምስት ሰዓት ነው የተገኘው። የሰውነት አካላቸው ተበታጥሶ የተገኘ ቢሆንም ለመለየት በተደረገ በተጨማሪ ምርመራ ነው መለየት የተቻለው። መግለጫውን ተከታትሎ ኢዜአ ይፋ እንዳደረገው ኢንጂነር አምብዛ በጭካኔ መገደላቸውን አስተዳደሩ ማረጋገጥ መቻሉን አመክቷል።።