የግብጽ ተንታኞች ስለ ኢትዮጵያ አየር ሃይል ያቀረቡትን ትንተና ኡስታዝ ጀማል እንደሚከተለው ያቀረበውን እንዳለ ለጥፈነዋል።
ይሄው ዛሬ ደግሞ የኢትዮጵያን የአየር ሃይል ብቃት በዝርዝር እየተነተኑ ነው!!!!
ግብፃዊ የጦር ተንታኝ የኢትዮጵያን አየር ሃይል ከአመሰራረቱ ጀምሮ እስከዛሬ ያለውን ብቃት በአረብኛ ፕሮግራማቸው ላይ አንድ በአንድ እያነሳ ገለፃ እየሰጠ ነው!!!!
ዝርዝር ትርጉሙን ወንድማችን ኡስታዝ ጀማል አቀረበው!!!! በጣም ደነቀኝ!!!! ስገረም አመሸሁ!!!! ለውድ ኢትዮጵያውያን ላካፍላችሁም ወደድኩ::
.
ግብፃዊው ተንታኝ ንግግሩን የሚጀምረው እንዲህ ብሎ ነው
ስለ ኢትዮጵያ አየር ሃይል ብቃት የማታውቁትን ላስታውቃችሁ ብሎ ነው:: ይቀጥልና
የአስዋንን ግድብ የሚያሰጋው የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ብቃት ላስቃኛችሁ ይልና
በኢትዮጵያ እና በግብፅ መካከል ያለው ግንኙነት ተበላሽቶ ውጥረት ነግሶና መሪወቹ ዛቻ እየተቀያየሩ ባሉበት በዚህ ወቅት
ግብፅ ውስጥ ያለውን አስዋን ግድብን የሚሰጋው ጉዳይ የኢትዮጵያ አየር ሃይልን ብቃት ነው:: በማለት ወደ ዝርዝሩ ይገባል:: ንግግሩ በስጋት ተጀምሮ በስጋት ያልቃል::
ግብፃዊው ተንታኝ ከተናገራቸው ንግግሮች መሃል የኢትዮጵያ አየር ሃይል በዓፄ ኃ/ስላሴ ዘመን በ1929 እንደተመሰረተ
ከ1929-1936 ኢትዮጵያ 19 የጦር አውሮፕላኖች እንደነበራት
ጣልያንን ካስወጣች በኃላ በ1944 አየር ሃይሏን ዳግም እንዳደራጀች እና የአየር ሃይል ማሰልጠኛ ተቋም እንደከፈተች
የተወሰኑ አውሮፕላኖች/ጀቶች እና መምህሮችን ከፈረንሳይ እና ከአሜሪካ እንዳገኘች
ከዚያም ማሰልጠኛ ተቋሟን አስፋፍታ 75 ቶፕ ሰልጣኞችን እንዳስመረቀች
በ1957 ከስዊዝ ሃገር ኤፍ-83 የሚባሉ 3 የጦር አውሮፕላኖች/ጄቶችን እንዳገኘችና ይህም በወቅቱ ቤስት የሚባል እንደነበር
በ1965-70 አሜሪካ ለኢትዮጵያ F-5ES የተሰኘ ሚሳኤል የሚተፋ ጄት እንደሰጠች
በጂሚ ካርተር ጊዜ ኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነታቸው ተቋርጦ አሜሪካ ፊቷን እንዳዞረች
ከዚያም ኢትዮጵያ ከቀድሞ ወዳጇ ራሽያ ጋር ግንኙነቷን እንደቀጠለች
ራሽያም በወቅቱ አሉ የሚባሉ ሚግ 23 ሚግ 21 ሚግ 17 የሚባሉ ተዋጊ ጀቶችን ሰጠቻት
በነዚህ ጄቶች እና በነበራት የአየር ሃይል ብቃት የሱማሊያ ጦርነትን ኢትዮጵያ በድል እንደተወጣች
ከዚያም ቀጥላ ኢትዮጵያ የአየር ሃይሏን በሚገባ እንዳደራጀች
በተለይ F 16 : ሚግ 23 : ሚግ 27 : SU 25 ሱ 30 እና SU 27 ፍላንከር በሚባሉ ራሽያ ሰር ተዋጊ ጄቶች ራሷን እንዳስታጠቀች
እነዚህን ጄቶች ራሽያ የሰራቻቸው አሜሪካንን ለመግጠም እንደነበር
ከነዚህም ውስጥ SU 27 ፍላንከር ጄቶች ከየትኛውም ጄት በላይ በአናትህ ላይ ሆኖ መብረር የሚችሉ መሆኑን
አንዱ SU 27 ፍላንከር ጄት ለግጥሚያ ሲወጣ ስምንት ሚሳኤሎችን: RBK መትረየሶችን እና ረዥም እና አጭር ተምዘግዛጊ አረሮችን የመሸከም ብቃት እንዳለው
በአንድ ሰዓት ውስጥ 3530 ኪ.ሜ እንደሚያቋርጥ
የጄቱ ክብደት 30,450 ኪሎ ግራም ሲሆን
9400 ኪሎ ግራም መሳሪያ መጫን እንደሚችል በዝርዝር ይተነትናል::
አክሎም ራሽያ ሰራሽ Mil Mi 24 የተሰኙ ስምንት ሰው መጫን የሚችሉ አደገኛ ተዋጊ ሄሊኮፕተሮች አሏት ይላል::
በዚያ ላይ ሚግ 23 አላት::
ሶቪየት ሰራሹ ሚግ 23 ከእይታ ውጭ (beyond-visual-range) የሆኑ ሚሳይሎችን የታጠቀ ነው:: ወዘተ:: እያለ በስጋት ይተነትናል::
ከዚያም አለ የስጋት ተንታኙ….
ኢትዮጵያ በዚህ ወቅት በአጠቃላይ ከ 92 በላይ የጦር ጄቶች እና አውሮፕላኖች እንዳሏትና ከነዚህም ውስጥ
24 ተዋጊ :20 መለማመጃ: 9 ማጓጓዣ : 33 የጦር ተዋጊ ሄሊኮፕተር: 8 አጥቂ ልዩ አንቶኖቭ አውሮፕላኖች ወዘተ እንዳላት ያትታል:: (የማያውቀው እንዳለ ሆኖ)::
በዚህም ሳቢያ ይላል የግብፁ ተንታኝ
በዚህ አቅሟ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃን ይዛለች:: ይህ ትልቅ አቅም ነው::
ያሏት ጄቶች እጅግ አደገኛ ናቸው::
የ SU 27 ጄቶች ባለቤት ናት::
NATO (ኔቶ) ይህ ራሽያ ሰራሹን SU 27ን አይወደውም:: ኔቶ በግልፅ አስቀምጦታል::
በሰዓት ከ2500 ኪሜ እስከ 3530 ኪ.ሜ ይምዘገዘጋል::
ከኢትዮጵያ ግብፅ 2237 ኪሜ ብቻ ነው::
ይህም ከኢትዮጵያ ተነስቶ ግብፅ ለመድረስ አንድ ሰዓት አይወስድበትም ማለት ነው::
አስዋን የተሰራበት አቅም SU 27 በሚተፋቸው ሚሳኤሎች የመፍረስ እድል አለው::
በአንፃሩ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በጄት ድብደባ እንደማይፈርስ አዋቂዎች አረጋግጠዋል::
እንግዲህ በዚህ ስሌቱ ነው የግብፁ ተንታኝ
አስዋን ግድብን የሚያሰጋው የኢትዮጵያ የአየር ሃይል ብቃት እያለ በስጋት ተውጦ ሲተነትን ያመሸው::
ታላቅ ምስጋና ለጀግናው አየር ሃይላችን!!!!!
ታላቅ ምስጋና ለጀግናው የመከላከያ ሃይላችን!!!!
ግብፃዊያኑ እንዲህ ተጨንቀው ቢተነትኑም….
እኛ ግን ሰላም እና እድገት ፈላጊዎች ነን!!!!
ማንንም ለመጉዳት አስበንም ተመኝተንም አናውቅም!!!!
በሰው ጉዳይ እንፈትፍት ያልንበት ታሪክም የለንም!!
ሃይላችን እና ትምክህታችንም ፈጣሪ ነው!!!!
ፈጣሪ ደግሞ የእውነት እና የፍትህ አምላክ ነው!!!!
ፈጣሪ ከኢትዮጵያ ጋር ነው!!!!!
ሃይሉን እና ጥበቡን
ማሸነፍና ድሉን እሱ ይሰጠናል!!!!
ውዶቹ የኢትዮጵያ ልጆችም ለእናት ሃገራቸው ክብር እና ጥቅም ነፍሳቸውን ለመስጠት ሳስተው አያውቁም!!!!
ጠላትን በአንድነት ሆነው ይገጥማሉ!!!!!
ያሸንፉማል!!!!
በውጭ ጠላት ተንበርክከው በፍፁም አያውቁም!!!!!
ልባችንም…ታሪካችንም… እውነታችንም ይሄው ነው!!!!
ሁሌም ድሉ የእኛ
ክብሩ የፈጣሪ ነው!!!!!!
#Ethiopia ሼር ይደረግ!!!!
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር የእግር… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ