እስከመጨረሻው ድረስ በምርጫው ሄደት ውስጥ በመጓዝ ባለቀ ሰዓት ከምርጫው አፈንግጦ ለመውጣት እቅድ ይዘው እንደሚነቀሳቀሱ በቅድመ ምርጫ ዳሰሳ የተጠቀሱ ፓርቲዎች ከስምምነት ላይ እንዳልደረሱ በምርጫ ታዛቢነት ከሚሰሩ መካከል የኢትዮ12 መረጃ ተባባሪ ገለጹ።
በምርጫ ቅድመ ዳሰሳ ጥናት ላይ ተሳታፊ የሆኑት የመረጃ ተባባሪያችን ከሳምንት በፊት ባልደራስ ተጨማሪ የምዝገባ ቀን እንዲሰጠው እንደሚጠይቅ ገልጸውልን መዘገባችን ይታወሳል።
እኚሁ ሰው ለአዲስ አበባ ተባባሪያችን እንዳስረዱት በቅድመ ምርጫ ትንተና መንግስት ራሱ ካመናቸው የጸጥታ ችግር ካለባቸው ስፋራዎች በቀር ምርጫውን የሚያሰጋ ጉዳይ አልተገኘም። ምርጫ ቦርድም ቢሆን አዲስ ተቋም እንደመሆኑ ካለበት የአቅምና የልምድ ችግር ውጪ እንደተቋም ጥራጣሬ ላይ የሚጥለው ጥቆማም ሆነ ጥፋት ከፓርቲዎች አልተነሳበትም።
እንደ መረጃው ከሆነ በቅድመ ምርጫ ዳሰሳ የታየው አንዱና ትልቁ ጉዳይ ሕዝብ ምርጫው ተጠናቆ ወደ መደበኛ ህይወቱ ለመመለስ የመፈለጉ ጉዳይ ነው። እንዳንድ ነዋሪዎች ስም እየጠቀሱ ሳይቀሩ ፓርቲዎች ላይ ያላቸውን የዕምነት ደረጃ ይገልጻሉ።
ይህ የሕዝብ ስሜት በተለይ በአዲስ አበባና በትላልቅ ከተሞች ሰፊ ሽፋን አለው። በመሆኑም ምርጫውን ለሚያውኩ፣ ለሚያበላሹ ወይም እናበላሻለን ብለው ለሚሰሩ ጆሮ እንደሌለው የመረጃው ባለቤት አመልክተዋል። የአዲስ አበባ ተባባሪያችን በአዲስ አበባ እሱም እንዳስተዋለው ከሆነ ሕዝቡ ለረብሻና ሁከት እድል የሚሰጥ አይመስልም። ምርጫው ተጠናቆ መገላገል፣ ከምርቻው በሁዋላም ሰላምን የመናፈቅ ስሜት ብቻ ነው የሚታይበት።
ተባብሪያችን ያነጋገራቸው አንድ ነዋሪ ” ለማስረበሽ ያሰቡና ሁከት ለማስነሳት የሚፈልጉ ቢኖሩም ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑናና ሕዝብ በአንዴ ሆ ብሎ የሚነሳላቸው ባለመሆናቸው አልሰጋም” እንዳሉ ገልጿል።
የምርጫ ቅድመ ዳሰሳ ሲያከናውኑ የነበሩትና መረጃውን ያካፈሉን እንዳሉት ይህ ከላይ የተገለጸው ስሜት ለፓርቲዎቹም ግልጽ እየሆነ የመጣ በመሆኑ ያሰቡትን ከምርጫው የማፈንገጥና ካልተመረጡ የመረበሽ አካሄድ እንደማያዋጣ ተረድተዋል።
በግል ከተለያዩ ፓርቲ አመራሮች፣ ለፓርቲዎቹ ቅርብ ከሆኑ ዲፕሎላማቶችና የውጭ አገር ሚዲያዎች ጋር በቅርብ የመነጋገርና መረጃ የመቀያየር እድላቸው ሰፊ እንደሆነ የገለጹት የመረጃ ምንጫችን ” በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ አቋማችንን እናስተካክል፣ ያገኘነውን ይዘን በሰላም እንቀጥል፣ አገሪቱ አሁን ባለችበት ሁኔታ ተጨማሪ ችግር መሆን ከሕዝብ ጋር ያጋጨናል። ታሪካዊ ስህተት ይሆንብናል…” በሚል መከራከሪያ በማቅረብ እንደ አማራጭ ስልት የያዙትን መንገድ ለመተው በግልጽ አቋም የያዙ አመራሮች አጋጥመዋቸዋል።
ይህ አድሮ የመጣው አቋም ያላስደሰታቸውና በቀድሞው መንገድ መቀጠል እንደሚገባ የሚገልጹ ቢኖሩም ልዩነቱ ከሰፋና ሕዝብ ጆሮ በዝርዝር ከደረሰ አደጋው ከፍተኛ በመሆኑ አቋማቸውን ለመቀየር የወሰኑት ጫና እይፈጠሩ መሆኑንን ታዛቢው አስረድተዋል።
ይህና መስለ ጉዳዮች በተለያዩ አገራት ዲፖሎማቶችና ኤምባሲዎች በግልጽ የሚታወቅ እንደሆነም ከታዛቢው ገለጻ ለመረዳት ተችሏል። ታዛቢው የፓርቲዎቹን ስም ከመዘርዘር ተቆጥበዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኦነግ ሃይል ነው የተባለ ሰራዊት በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ጥቃት ለማድረስ እንደመሸገ በህዝብ ጥቆማ መድምሰሱ ተሰምቷል። መንግስት በይፋ ባይናገርም ከኦሮሚያ አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ይህ ሃይል ከምዕራብ ኦሮሚያ ተነስቶ የግጭት ቀጠና ለማስፋት ወደ ደቡብ አምርቶ የመሸገ ነው። ሕዝብ አስቀድሞ ጥቆማ በመስጠቱ በመሸገበት አካባቢ ተከቦ መድምሰሱ ታውቋል።
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል