
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ሰዓረ መኮንን እና ጓደኛቸውን ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ወንጀል ተከሶ የነበረው አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ ጥፋተኛ መባሉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገልጸ።
ውሳኔውን አርብ ግንቦት 27/2013 ዓ.ም የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሦስትኛ የጸረ ሽብርና የሕገመንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።
ከሁለት ዓመት በፊት በአዲስ አበባ በጀነራል ሰዓረ መኮንን መኖሪያ ቤት ውስጥ ግድያውን በመፈጸም የተከሰሰው አስር አለቃ መሳፍንት ጉዳይን የተመለከተው ችሎት ተከሳሹ የሰፊ የወንጀል ድርጊት አካል ሆኖ ወንጀሉን መፈጸሙን አመልክቷል።
ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ባወጣው መረጃ መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ የተላለፈበት ተከሳሹ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ በአማራ ክልል የቀድሞ የሰላምና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኃላፊ በነበሩት በብርጋዲየር ጀነራል አሳምነው ጽጌ በተመራ ሰፊ ከባድ የወንጀል ድርጊቶች ሴራ ውስጥ ተሳታፊ እንደነበር አመልክቷል።
በዚህም ተከሳሹ በዚሁ ሴራ ውስጥ የአገሪቱ ጦር ሠራዊት ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ሰዓረ መኮንን እንዲገድል እንዲሁም ሌላ ግለሰብ ደግሞ ምክትል ኤታማዦር ሹም የነበሩትን ጀነራል ብርሃኑ ጁላን እንዲገድል ተልዕኮ ሰጥቷቸው እንደነበር ተገልጿል።
ዐቃቤ ሕግ እንዳለውም ግንቦት 15/2011 ዓ.ም ምሽት ሦስት ሰዓት ላይ አስር አለቃ መሳፍንት ባሕር ዳር ከተማ የተፈፀመውን ጥቃት ሲሰማ “ተኩሶ ጀነራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራን በመግደል ለማምለጥ ሲሞክር ተከቦ በቁጥጥር ስር ውሎ” ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ መቆየቱን ገልጿል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ ሦስትኛ የጸረ ሽብርና የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በክሱ ላይ የቀረበውን የግራ ቀኝ ክርክርና ማስረጃ ከመዘነ በኋላ ነበር ተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ በመስጠት የቅጣት አስተያየት ለመስማት ለሰኔ 11/2013 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል።
ሰኔ 15/2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የተገደሉት ኤታማዦር ሹሙ፤ ለረጅም ዓመታት በኃላፊነቱ ላይ የቆዩትን ጄነራል ሳሞራ የኑስን ተክተው የአገሪቱ ሠራዊት አዛዥ ከሆኑ ብዙም አልቆዩም ነበር።
በጥቃቱ ወቅት በአጋጣሚ በጄነራሉ ቤት የተገኙት ጓደኛቸውና የቀድሞ የሠራዊቱ አባል ጀነራል ገዛኢ አበራም በተፈጸመባቸው ጥቃት ተገድለዋል።
ዐቃቤ ሕግ የዚሁ ሴራ አካል ነው ባለው ድርጊት በዚያው ዕለት ምሽት ጥቂት ሰዓታት ቀደም ብሎ በባሕር ዳር የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር የነበሩትን ዶ/ር አምባቸው መኮንንና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮቻቸው ላይ ግድያ መፈጸሙ ይታወሳል። BBC amaharic
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል