ከአማራ ክልል ከተለያዩ ዞኖች በደላሎች ተታለው በህገ ወጥ መንገድ ከሃገር ለመውጣት የሞከሩ 60 ወጣቶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የባቲ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር መሃመድ አሊ ለኢዜአ እንደገለጹት ወጣቶቹ ጨለማን ተገን አድርገው ከሃገር ለመውጣት ሲሞክሩ ትላንት ከለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ላይ በባቲ ከተማ ተይዘዋል ።
ወጣቶቹ በህገ ወጥ መንገድ ወደ አረብ ሀገር ለመውጣት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 43619 አአ በሆነ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪ ተሳፍረው ከደጋን መስመር ወደ አፋር በመጓዝ ላይ እንዳሉ በከተማው ቀበሌ 03 ቀርሳ ፍተሻ ጣቢያ ላይ መያዛቸውን ተናግረዋል ።
ወጣቶቹ ከ17 እስከ 28 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ጠቁመው ከወጣቶቹ መካከል ሶስቱ ሴቶች እንደሆኑ ገልጸዋል።
እንደ ዋና ኢኒስፔክተሩ ገለጻ ወጣቶቹ ከሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሽዋና ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በህገ ወጥ ደላሎች ተታለው የተሰባሰቡ መሆናቸውን አመልክተዋል።
ወጣቶቹን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ለማሶጣት በታሰበ ወንጀል ተሳትፎ እንዳላቸው የተጠረጠሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ ሁለት ግለሰቦች ተሸከርካሪውን አቁመው መሰወራቸውን ተናግረዋል ።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል መጀመሩን አመልክተዋል ።
ወጣቶቹን በሂደት ወደ አካባቢያቸው ለመመለስ ከወዲሁ ስራዎች መጀመራቸውንም ጠቁመዋል።
ዜጎች ጫካ ለጫካ ጭምር በእግራቸው በመጓዝ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጭ ሀገራት ለመውጣት በሚያደርጉት ሙከራ ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ለመደፈር እየተጋለጡ መሆናቸውን አብራርተዋል።
ድርጊቱ በተደራጀ አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ ለመከላከል አስቸጋሪ እንዳደረገው ያመለከቱት ዋና ኢኒስፔክተሩ የባለድርሻ አካላት ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ድርጊቱን ለመከላከል ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ። via (ኢዜአ)
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት።… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ