ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሽዋ በትናንትናው ዕለት ህይወታቸው አለፈ።
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሽዋ ማረፋቸውንም ይፋዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ “አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል” በሚልም ሰፍሯል።
ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።
በተከታዮቻቸውም ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሽዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ። በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።
ዘ ሲናጎግ፣ ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ (የሁሉም ህዝቦች ቤተ ከርስቲያን) የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በናይጄሪያ መዲና ሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከታተላሉ።
በቅርቡ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካች ያለው የዩቲዩብ ገፃቸው ከጥላቻ ንግግር ጋር በተያያዘ በሚያዝያ ወር ታግዶ ነበር።
ቅሬታውን ያቀረበው አንድ ገለልተኛ የሰብአዊ መብት ተሟጋች የኢቫንጀሊካን ሐይማኖት ሰባኪውን ሰባት የሚሆኑ የዩቲዩብ ቪዲዮዎች ከተመለከተ በኋላ በሁሉም ላይ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን ለመፈወስ ጸሎት ሲያደርጉ ነበር ብሏል።
ፌስቡክም ቢሆን የሐይማኖት ሰባኪውን የቲቢ ጆሽዋ አንድ ቪዲዮ አጥፍቶታል። በቪዲዮው ላይ ቲቢ ጆሽዋ “እርኩስ መንፈስ” ለማስወጣት በማለት አንዲት ሴትን በጥፊ ሲመቱ ይታያል።ሐይማኖት ሰባኪው በበኩላቸው የዩቲዩብን ውሳኔ በመቃወም ቅሬታቸውን አሰምተው ነበር።
በ57 አመታቸው ያረፉት ቲቢ ጆሽዋ በአውሮፓውያኑ 2011 ፎርብስ ላይ በወጣው መረጃ መሰረት የሃብት መጠናቸው ከ10-15 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል። BBC Amharic
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ