በህገ ወጥ ንግድ ስራ ላይ በተሰማሩ ከ60 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ቢሮዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ ባለፉት 10 ወራት በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ከጣቢያችን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ፣ የኑሮ ዉድነቱ አዲስ አበባ በሚሰሩ የንግዱ ማህበረሰብ ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እየወሰድን ነዉ ብለዋል፡፡ለዋጋ ንረቱ መባባስ የህገ ወጥ ነጋዴዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያነሱት አቶ መስፍን ፤በዚህም ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እስከ ማገድ ድረስ የሚደርስ እርምጃ ተወስዶባቸዋል ነዉ ያሉት፡፡
በዚህም 1 መቶ 9 ነጋዴዎች ታግደዋል፤ 2 መቶ 18 ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ ከ19ሺህ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ታሽገዋል ተብሏል፡፡በተጨማሪም ከ39 ሺህ በላይ በሚሆኑት ላይ የፅሁፍ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸዉም ምክትል ሓላፊዉ ነግረዉናል፡፡ባጠቃላይ የኑሮ ዉድነቱ እንዲባባስና የዋጋ ንረቱ እንዲጨምር ሲያደርጉ በነበሩ 60 ሺህ 3 መቶ 45 ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ ተወስዷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በከተመዋ የሚስተዋለዉን የኑሮ ዉድነት ለማረጋጋት ከሸማች ህብረት ስራዎች ጋራ በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁት አቶ መስፍን፣ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ብድር ለሸማች ማህበራት በማመቻቸት ወደ ስራ እንደገቡም ታወቋል፡፡ከዚህ በተጨማሪም እንደ አገር ከዉጭ በሚገቡ የዘይት፤ ስንዴ፤ ሩዝ፤ ስኳርና የሕጻናት ወተት ለ6 ወራት ከታክስ ነፃ እንዲገቡ ስለመደረጉም አቶ መስፍን አስታዉሰዋል፡፡
ከህገወጥ ነጋዴዎች በተጨማሪ የምርታማነት ችግርና ኮቪድ 19 ለኑሮ መወደድ የራሳቸዉ አስተዋፅኦ እንዳለቸዉ የተገለፀ ሲሆን፣ ህብረተሰቡ ከሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት እንዲጠቀሙ መክረዋል፡፡ቢሮዉ ከ1 መቶ ሺህ ኩንታል በላይ የጤፍ ምርት ለሸማች ማህበራት ማከፋፈሉን የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት መንግስት በድጎማ ከዉጭ ያስገባዉን የስንዴ ምርት ከሸማች ስራ ማህበራት በ 2ሺህ 5 መቶ 40 ብር ማግኘት እንደሚቻልም ኃላፊዉ ተናግረዋል፡፡
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria, and the ongoing tensions with… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን በቅጡ የሚገነዘቡ ምሁራን የራስ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ