የህወሓት ታጣቂ ኃይሎች በትግራይ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲያቆሙ አሜሪካ አሳሰበች በትግራይ ክልል በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ በህወሃት ታጣቂዎች እየደረሰባቸው ያለው ጥቃት እና ማስፈራራት እንዲቆም የአሜሪካ መንግሥት አሳሰበ።
በትግራይ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ስደተኞች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን እየተገደሉ፣ እየተደፈሩና ንብረታቸው እየተዘረፈ መሆኑን የማይፀምሪ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ በሪሁን ባለፈው ሳምንት ለኢዜአ መግለጻቸው ይታወቃል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ እየተሰነዘረ ያለው በህወሓት ታጣቂ ኃይሎች እና በትግራይ ሚሊሻ አባላት እንደሆነም ገልጿል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ጄሊና ፖርተር እንዳሉት በትግራይ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ እየደረሱ ያሉትን ዛቻ እና ጥቃቶች የሚገልጹ ተጨባጭ ሪፖርቶች እንደደረሰው ገልጸው፤ጥቃቱ በአፋጣኝ እንዲገታም አሳስበዋል።
በአሸባሪው ቡድን በየቀኑ የሚፈጸሙ በአሰቃቂ ታሪኮች የተሞሉ አሳማኝ ማስረጃዎችን እንደሚቀበል የገለጸው፤ ኮሚሽኑ ሰሞኑን በማይ አይኒ ካምፕ አንድ ስደተኛ በህወሃት ታጣቂዎች የተገደለ ሲሆን ግድያው ከ15ቀናት ወዲህ የተደረገ ሌላኛው ጥቃት መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ባወጣው መረጃ ይፋ አድርጓል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጄሊና “ትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሁሉም ታጣቂ ኃይሎች ኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ጥቃት ከመፈጸም እንዲሁም ዛቻ ከመሰነዘር እንዲያቆሙ እንጠይቃለን” ሲሉ መናገራቸውን ነው ሮይተርስ የዘገበው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በትግራይ ክልል በሚገኙ ወደ 24ሺህ የሚጠጉ ኤርትራውያን ስደተኞች የሰብዓዊ ድጋፍ እንደተቋረጠባቸው መግለጹን ይታወሳል።
ኮሚሽኑ ትላንት ባወጣው ሪፖርት በትግራይ ክልል የሚገኙ በማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች እና በአቅራቢያቸው ግጭት መኖሩን ገልጾ ሁለት ስደተኞች መገደላቸውንም አስታውቋል።
የማይፀምሪ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ አስተባባሪ አቶ ስንታየሁ በሪሁን ባለፈው ሳምንት በትግራይ በሚገኙ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ስደተኞች እየተገደሉ፣ እየተደፈሩና ንብረታቸው እየተዘረፈ መሆኑን ለማስተባባሪያው መረጃ መድረሱን ገልጸዋል፡፡
በትግራይ ክልል ተባብሶ በቀጠለው ግጭት በክልሉ ባሉ ሁለት የኤርትራውያን ስደተኞች ካምፖች ውስጥም በመከሰቱ የስድተኞቹን እጣ ፈንታ አሳሳቢ አድርጎታል ያለው ኮሚሽኑ 24 ሺህ የሚሆኑና በማይ አይኒና በአዲ ሃሩሽ ካምፖች ውስጥ የሚኖሩት ስደተኞች ከሰብአዊ እርዳታዎች ከመራቃቸውም በላይ የሚደርስባቸው ጥቃትና በደል ኑሮቸውን አሰቃቂ አድርጎታል ብሏል።
የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ባለፈው ሰኔ ወር ለኢዜአ እንደገለጹት በትግራይ ክልል ባለው ሁኔታ የሽመ ልባ እና ህፃፅ የስደተኞች ካምፖች ምቹ ባለመሆናቸው የተነሳ መዘጋታቸውንና ይህን ተከትሎም “አለምዋጭ” መጠለያ ጣቢያ መገንባት ማስፈለጉን ተናግረዋል ።
በሚመሰረተው ጣቢያ በነዚህ ካምፖች የነበሩና ሌሎችን ጨምሮ እስከ 20 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ መታቀዱን አቶ ተስፋሁን አስረድተዋል።
አሁን ባለው ሁኔታ አሸባሪው የህወሓት ቡድን እየፈጸመ ባለው ትንኮሳና ግጭት ለክልል ህዝብ ሆነ በክልሉ ለሚገኙ ስደተኞች ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ በቡድኑ መንገድ መዘጋቱ እየተገለጸ ነው።
ወደ ትግራይ ሊጓጓዝ የተጫነን የእርዳታ እህል የያዙ 170 ከባድ ተሽከርካሪዎች በአሸባሪው ህወሓት አማካኝነት ጉዟቸው ተገትቶ መቆሙን የትራንስፖርት ሚኒስር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ትላንት ማስታወቁን ኢዜአ አስታውቋል።

- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria,… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ