የኢቶጵያ መንግስት የኢምባሲዎችን ቁጥር እንደሚቀንስ፣ ይህም የሚሆነው ኤምባሲዎቹ ወጪ ከማብዛታቸው በላይ የግለሰቦች ምሽግና መጠቀሚያ በመሆናቸው እንደሆነ አስታውቆ ነበር። ይህን ተከትሎ ለተወሰኑና ለተመረጡ አምባሳደሮች በደብዳቤ ጥሪ መላኩን አዲስ ስታንዳርድ ” ሰበር” ሲል ዘግቦታል።
ደብዳቤው በገሃድ የተሰራጨና ባለፈው ዓመት የተጠናው ጥናት ውጤት መሆኑን መንግስት በተደጋጋሚ ሲያስታውቅ እንደነበር ይታወሳል። በተመሳሳይ በዲፕሎማሲው ረገድ ፋይዳ የሌላቸው ዲፕሎማቶች አገሪቱን ዋጋ እንዳስከፈሏት በተደጋጋሚ ሲተች ነበር። በዚሁ መነሻ “እንደቀድሞው በጅምላ በግዢ ዲግሪ የተመረቁ ” ሳይሆኑ አዳዲስ ዲፕሎማቶች ተመልምለው ሲሰለጥኑ እንደነበር መንግስት አስታውቆ ነበር።
የዚህ አካል እንደሆነ የተነገረለት የማስፈጸም ጅማሮ ሲሰሩበት ለነበረው ሚሲዮን ንብረት አስረክበውወደ አገር ቤት በመመልስ ሪፖርት እንዲያደርጉ የታዘዘበትን ደብዳቤ ደብዳቤው ከተላከለት አንድ አካል በመውሰድ “ሰበር” ዜና በሚል አዲስ ስታንዳርድ አትሟል። በደብዳቤው እንደተጠቀሰው ፣ጥሪ የተደረገላቸው እስከ ነሃሴ 15 ቀነ ገደብ ተሰጥቷቸዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ ካሳ ተክለ ብርሃን፣ ተሾመ ቶጋ፣ ኩማ ድሪባ፣ አይነት ዲፕሎማቶች ያሏት አገር መሆኗ እጅግ አሳዛኝ እንደሆነ ለዲፕሎማሲው ቅረበት ያላቸው በተደጋጋሚ ሲተቹ እንደነበር።
የኢትዮ 12 የአዲስ አበባ ተባባሪ ያነጋገራቸው የብልጽግና ከፍተኛ አመራር ” ሰበር ዜና መሆን ያለበት መንግስት ህዝብን ሰምቶ እርምጃ ወሰደ የሚለው በሆነ ነበር” ሲሉ ጥቅል ምላሽ ሰጥተዋል።

- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ ስመ ጥር የእግር ኳስ ኮከቦች ወደ ፓሪሱ… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ