የአማራ ክልል ልዩ ኃይል እየወሰደ ባለው ማጥቃት የአሸባሪውን ኃይሎች ከአማራ ክልል እያስወጣ እንደሆነ የክልሉ መንግስት አስታወቋል። ክልሉ ወደ ሙሉ ማጥቃት መዛወሩን ይፋ ባደረግ በቀን ውስጥ ነው ይህን ያለው። የአሸባሪ ቡድኑ ወረራ በአማራ ክልል ተወስኖ ስላማይቀር የሌሎች ክልሎች ኃይሎችም የህልውና ዘመቻውን እየተቀላቀሉ መሆኑን ክልሉ ይፋ አድርጓል።
በሌላ በኩል በጦርነቱ ከተለያዩ ቦታዎች ተፈናቅለዉ ቆቦ የሚገኙ ነዋሪዎች ርዳታን እየጠየቁ ነዉ።
የአማራ ክልል እንዳስታወቀው ህዝብ ለቅረበለት ጥሪ ከበቂ በላይ ምላሽ ሰጥቷል። የአሸባሪው ኃይሎች በሰሜናዊ የአማራ አካባቢዎች ወረራ መፈጸማቸውን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በተደረገ የክተት ጥሪ ተቀብለው በርካቶች ትግሉን ተቀልቅለዋል። ትግሉን ለመቀላቀል በዝግጅት ላይ ሆነው ስምሪት የሚጠብቁም ይልቃሉ።
የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን የመንግስት ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለጀርመን ድምጽ እንድተናገሩት የክልሉ ልዩ ሃይል አሸባሪው ቡድን ይዟቸው የነበረውን አካባቢዎች እያጸዳና እያስልቀቀ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“የአሸባሪው ጥቃት በአማራ ክልል ተወሰኖ እንደማይቀርና ኢትዮጵያን ለማፍረስ እንደሚሰራ በዓለምአቀፍ ሚዲያዎች ጭምር ያረጋገጠው ነው” ያሉት አቶ ግዛቸው ይህን ሴራ ለመበጣጠስ ሌሎች ክልሎችም የፀጥታ ኃይሎቻቸውን ወደ አማራ ክልል እየላኩ እንደሆነ አስረድተዋል፣ እስካሁንም ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች ልዩ ኃሎቻቸውን ልከዋልም ብለዋል፡፡
አሜሪካና አንዳንድ የአውሮፓ አገራት ሕወሓት በማይካድራ በቅርቡ ደግሞ በኤርትራውያን ስደተኞች ላይ ግድያና ማፈናቀል ሲደርስ አንድም ቃል ሳናገሩ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ፍትሃዊ አለመሆኑንን ሃላፊው አስታውቀዋል።
ሃላፊው አይገለጹት እንጂ አላማጣን ጨምሮ የትህነግ ቡድን ለአንድ ቀን ተቆጣጥሯቸው የነበሩትን ስፋርዎች የአማራ ልዩ ሃይል አስመልሷል። እንደሚሰማው ከሆነ የአማራ ልዩ ሃይል በጦርነቱ የበላይነት ይዟል። ይሁን እንጂ አሁንም ሰላማዊ ውይይት እንደሚሻል በስፋት አስተያየት እየተሰጠ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ሰሞኑን ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተፈናቅለው በቆቦ የሚገኙ ወገኖች ችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ አንድ የራያ አማራየወሰንና ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር ለዶቼ ቬለ እንዳሉት ተፈናቃዮች በየዘመዱ ቤት ተጠግተው እንደሚገኙና አሁን እርዳታ ለማቅረብ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አስቸጋሪ መሆኑንን አመልክተዋል።
- “ጀነራሉ ያዋቀሩት ካቤኔ እና እየሄዱት ያለው አካሄድ የነበረውን ሰላም የሚያሳጣ ነው ” የኢሮብ ሲቪክ ማህበርበቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በስምምነቱ የቃል ኪዳን ሰነድ መሠረት አካታች ሊሆን እንደሚገባ የኢሮብ ማህበረሰብ ሲቪክ ማህበር ዋና ዳይሬክተር እና ፖለቲከኛ አቶ… Read more: “ጀነራሉ ያዋቀሩት ካቤኔ እና እየሄዱት ያለው አካሄድ የነበረውን ሰላም የሚያሳጣ ነው ” የኢሮብ ሲቪክ ማህበር
- “በጀግንነት የተጠበቀች፤ በመስዋዕትነት የጸናች”ዓለም ፊቱን አዞረባት ልጆቿ ግን በስስት ተመለከቷት፣ ዓለም ዘመተባት ልጆቿ ግን ለክብሯ ዘመቱላት፣ ዓለም አዋከባት ልጆቿ ግን አረጋጓት፣ ዓለም አደማት ልጆቿ ግን አከሟት፣… Read more: “በጀግንነት የተጠበቀች፤ በመስዋዕትነት የጸናች”
- በደቡብ እስያ ያንዣበበው የጦርነት ስጋትህንድ በፓኪስታን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀቷን የሚያመለክቱ ታማኝ የደህንነት መረጃዎች እንዳገኙ የፓኪስታን የማስታወቂያ ሚኒስትር ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ አታውላህ ታራር ህንድ ባለፈው ሳምንት የተፈፀመውን የፔልጋም… Read more: በደቡብ እስያ ያንዣበበው የጦርነት ስጋት<br>
- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በኒኩለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንድትሰጥ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ተመረጠች።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA)፣ በቻይና መንግስት የ Tsingua University፣ ኦንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ (AASTU) ባደረጉት የተለያየ… Read more: ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በኒኩለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንድትሰጥ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ተመረጠች።
- በጅቡቲ ኢትዮጵያውያኖች በ3 ቀን ውስጥ ውጡ – ዲፕሎማሲ በአስቸኳይ!በጣም ብዙ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነው ያለው፣ ከኢትዮጵያዊ ቀጥሎ የመኖች ናቸው፡፡ ግን ሁሌም ውጡ የሚባሉት ኢትዮጵያውያኖች ናቸው፡፡ ምክንያቱን አላውቅም፡፡ በፖሊስ ሁሌም አፈሳ አለ፣ የሚታፈሱት… Read more: በጅቡቲ ኢትዮጵያውያኖች በ3 ቀን ውስጥ ውጡ – ዲፕሎማሲ በአስቸኳይ!