አሸባሪው ህወሃት ለትግራይ ክልል የሚላከው የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይጓጓዝ ማስተጓጎሉና ስላሳ የሚጠጉ እህልና ቁሳቁስ የጫኑ ተሸከርካሪዎች እንዳያልፉ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ መንገስድ መዝጋቱ ተገለጸ። መንግስት በአፋር በኩል የትህነግ ሃይል ድንበር አልፎ ሲመጣ ለምን ዝምታን እንደመረጠ አልተገለጸም። ይሁንና ክልሉ የጸጥታ ሃይሉና ሕዝቡ እንዲዘጋጅ አሳስቧል።
ኢዜአ እንዳለው ለትግራይ ክልል የሚላከው የሰብዓዊ ድጋፍ በአፋር በኩል ወደ መቀሌ ሲጓጓዝ የአሸባሪው የህወሃት ቡድን አካባቢውን በከባድ መሳሪያ በመደብደብ መንገድ ዘግቷል። መንግስት ወደ ትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ በተገቢው መልኩ ለማዳረስ የተናጥል ተኩስ ማቆሙ ተከትሎ ወደ አጥቂነት የተዛወረው አሸባሪው ቡድን ይህን ተግባሩን እንዲያቆም የገሰጸው አካል እንደሌለ መንግስት በተደጋጋሚ እያስታወቀ ነው።
ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ድጋፍ እየቀረበ መሆኑን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በይፋ ባስታወቀበትና ተጨማሪ የኬላ ጣቢያዎችን በማቋቋም ፍተሻውን በማጣደፍ እርዳታ ቶሎ ቶሎ ወደ ተረጂዎች እንዲደርስ እየሰራ መሆኑንን ባመለከተበት ወቅት አሸባሪው ሃይል አፋርን በከባድ መሳሪያ የሚደበድብበት ምክንያት ግልጽ አይደለም። ይሁን እንጂ አቶ ጌታቸው በጤና ሆነው ከሚናገሩት አግባብ ውጭ አንደበታቸው እየተጎተተ ለቪኦኤ ” በወልቃይት በኩል እርዳታ እንዲገባ እናደርጋለን” ካሉት ጋር ሊገናኝ እንደሚችል ግምት አለ።
ዛሬ በአፋር ክልል በኩል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን የጫኑ 60 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እየተጓዙ ሳለ የአሸባሪው ህወሃት ቡድን ተኩስ በመክፈት እንዳይጓጓዝ መንገድ መዝጋቱ ኢዜአ ሲዘግብ መንገዱ እንዲከፈት ምን ጥረት እንደተደረገ የትኛውንም ወገን ጥቀሶ ያለው ነገር የለም።
ለትግራይ ክልል የሚሂድ የእርዳታ ቁስና ምግብ ነክ የሆነ ተፍትሾ እንዲያልፍ ሰርዶ 60 እና ሚሌ ኬላዎች ላይ እየተሰራ ቢሆንም፤ አሸባሪው ህወሃት በዞን አራት ያሉ የአፋር ፖሊስና ልዮ ሀይል አባላትና ማህበረሰብን በከባድ መሳሪያ እየደበደበ “ወደ ትግራይ የሚሄድ እርዳታ አይኖርም” በማለት ሰርዶ ኬላ ላይ መዝጋቱን ከአካባቢ የተገኙ ምንጮች ለኢዜአ ተናግረዋል።
ህወሃት የተኩስ አቁም ውሳኔውን “አልቀበልም” በማለት ግጭቱን ወደ አፋር ክልል ለማስፋት እየሰራ መሆኑም ታውቋል። በቅርቡም መንግስት ሁኔታዎች በማመቻቸቱ ለክልሉ ሰብዓዊ ድጋፍ የጫኑ 61 ከባድ ተሽከርካሪዎች ትግራይ ክልል መድረሳቸው ይታወሳል።
ከዚህ ውስጥ 34ቱ ምግብ ነክ ድጋፎችን የጫኑ ሲሆን፤ 26 ተሽከርካሪዎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን የጫኑ ሲሆኑ፤ ከ47 ሺህ ሊትር በላይ ነዳጅ የጫነ አንድ ከባድ ተሽከርካሪም መቀሌ መድረሱ ተዘግቧል።
በአፋር ክልል ያለውን መንገድ ማስተጓጎል የተፈለገው በውልቃይት በኩል ድንበሩ እንዲከፈት ያለውን ግፊት ለመጨመር ሆን ተብሎ የተደረገ እንደሆነ የሚገልጹ አሉ። ትህነግ በወልቃይት በኩል ያለውም ግምብ ማለፍ ስለማይቻለው በአፋር በኩል ችግር በመፍጠር በወዳጆቹ አገራት አማካይነት የሱዳን ድንበር እንዲከፈትለት ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል። በሌላ በኩል ከመንግስት በኩል ከወታደራዊ ጠቀሜታ አንጻር አሸባሪ ቡድኑ ወደ አፋር ሜዳማ ቦታ እንዲወጣ ይፈለጋል የሚሉም አሉ። እነዚህ ክፍሎች አክለው እንደሚገልጹት ሳይሆን ይህ ሃይል አፋርን ወሮ የጅቡቲን መንገድ ለማስተጓጎል ህልም እንዳለው፣ ወደ አሰብም የማምራት እቅድ እንዳለው ለወዳጆቹ መረጃ መስተቱን የሚያውቁ እየተናገሩ ነው።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል