የአማራ ክልል ርዕሰ ብሄር አገኘሁ ተሻገር ለክልሉ ዓቅሙ የደረሰና ብቁ የሆኑ ወጣቶች የክተት ጥሪ አስተላለፉ። የሽብር ቡድኑ ቃል አቀባይ “ከአማራ ጋር የምናወራርደው ሂሳብ አለ” በሚል በገሃድ ከተናገሩ በሁዋላ ክልሉ ያስተላለፈው ይህ ጥሪ ከዳር እስከዳር ንቅናቄ ፈጥሯል።
“በክልሉ ውስጥ የማንኛውም የመንግሥትን መሳሪያ የታጠቀ፣ የግል መሣሪያ የታጠቀ፣ ለግዳጅ ብቁ የሆነ ወጣት ሁሉ ከነገ ጀምሮ ለህልውና ዘመቻ እንዲዘምት የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የክተት ጥሪ አስተላለፉ” ሲል ነው የክልሉ ሚዲያ ይፋ ያደረገው።
አሜሪካ በኢትዮጵያ መፍንቅለ መንግስት አካሂዳ ትህነግን በመሪነት ለማስቀመጥ እላይ ታች በምትልበት ወቅት የአማራ ክልል ” ለህልውና ዘመቻ ክተት” ማለቱ ስጋት ፈጥሯል።
የትህነግን ምርጫ በብቸኝነት የታዘቡት የኖርዌይ ተወላጅ ፕሮፌሰር ሼትል የአማራ ክልል ይህን ዜና ይፋ ባደረገ ደቂቃዎች ውስጥ በቲውተራቸው አማራ መሳሪያ ያለው ሁሉ ከነገ ጀምሮ ወደ ጦር ግንባር እንዲዘመት መተራቱን ጠቅሰው፤ የሲቪል ጦርነት እንደሚቀሰቀስ ጠቁመዋል። የአቶ አገኘሁ ተሻገርን ምስልና ጥሪ አትመው ለነጮቹ ባሰራጩት መልዕክት ማሳረጊያ እንደተለመደው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ወቅሰዋል።
ዜናው እንደተሰማ በቀጥታ የተላከላቸው የውጩ ማህበረሰብ እንዲያሰራጩ ሲሆን ሰውየው ከቀናት በፊት መንግስት እንደሚገለበጥ የሚያትት ጽሁፍ በማጋራት ” አዳዲስ ተተኪዎቹ ይዘጋጁ” የሚል ሃሳብ አሰራጭተው ነበር።
አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው አገሪቱ ሕዝብ ለመንግስት ድጋፍ እየሰጠ ባለበት፣ ትህነግን እንደማይፈልግ እያወገዘ ድምጹን በሚያሰማበት በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ለመጫን ያሰበችው ሃይል ተቀባይነት እንደማይኖረው፣ ክልሎች ጭራሹኑ ጆሮ እነደማይሰጡት አለመረዳቷ አስገራሚ እንደሆነ ተመልክቷል።
የአማራ ክልል ራሱን በነባር የጦር መኮንኖች ካደራጀ በሁዋላ ለህልውና ዘመቻው እንደሚነሳ ብ/ጄነራል ተፈራ መናገራቸው አይዘነጋም። አዲሱ የልዩ ሃይል አዛዥ እንዳሉት ዘመቻው ስር ነቀለና ትህነግን ለመቸረሻ ጊዜ የሚነቅል ነው።
ትህነግ በትግራይ የሰለጠኑ 250 ሺህ ወታደሮችና አንድ ሚሊዮን በላይ ሚሊሻና ለክተት የተዘጋጀ ሃይል፣ እንዲሁም እጅግ በርካታ ሕጻናትን መልምሎ ውጊያ ላይ ቢያሰልፍም አሜሪካን ጨምሮ ኢትዮጵያ ላይ ውርጅብኝ የሚያወርዱት አገራት ምንም ያሉት ነገር የለም። ይህን በማስረጃ የተደገፈ ጉዳይ በዝምታ ያለፉት አገራቱ የአማራ ህዝብ “ለህልውና” በሚል የጠራውን ክተት ተከትሎ የተለያየ መግለጫና የውግዘት ማሳሰቢያ እንደሚያወጡ ይጠበቃል።
አብዛኞች የሰላም አማራጭ እንዲፈለግ እየወተወቱ ቢሆንም ታላላቁ አገራት መንግስት ለመገልበጥ ከትህነግ ጎን መሰለፋቸው ችግሩን አሳዛኝና ውስብሰብ እንዳደረገው እየተገለጸ ነው።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል