በኢትዮጵያዊያን አቆጣጠር የህዳሴው ግድብ ዛሬ ለሌት ሲሞላ ” ኢትዮጵያ ኒኩሌር ታጠቀች” ማለት እንደሆነ ባለሙያዎች አስታወቁ። ሲያብራሩም የህዳሴውን ግድብ መሙላት ማለት ግድቡን ከማንኛውም ክፉ ሙከራ መታደግ እንደማለት ነው።
“በኢትዮጵያዊያን ደም፣ አጥንትና ላብ የተሰራ ነው” ሲሉ ድየውሃና መስኖ ሚኒስትሩ ዶክተር ስለሺ የገለጹት የህዳሴው ግድብ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ተገባዷል። ወይም እንደተገባደደ ይታመናል። በዚሁ ሂሳብ መሰረት ከፍታው ከባህር ወለል በላይ 574 ሜትር ሆኗል። ዶክተር ስለሺ በተደጋጋሚ እንደተናገሩት የውሃው ሙሌት ሲጠናቀቅ በሁለት ተርባይን የኤሌክትሪክ ሃይል ለማምረት የተያዘው ዕቅድ የሚሳካ ነው።
የሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት አስመለክቶ ግብግብ ፈጥራ የነበረችው ግብጽ የውሃው ሙሌት ጫፍ መድረሱንና ምንም ማድርተግ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን ስትረዳ አልሲሲ “ኢትዮጵያን በልማት ማገዝ እንፈልጋለን” ማለታቸውን ያስታወሱ ባለሙያዎች እንዳሉት ካሁን በሁዋላ የህዳሴው ግድብ ጥበቃ አያስፈልገውም።
ግብጽ ግድቡን ብትመታ ሽቅብ ወደላይ ሳይሆን ወደታች ሲወርድ ሱዳንና ግብጽን ተረት እንደሚያደርጋቸው በሂሳብ የሚያስረዱ እንዳሉት፣ ግብጽ ካሁን በሁዋላ ማተረማመሷን ታስቀጥል ካልሆነ በቀር ህዳሴውን ግድብ አስመልክቶ አንዳችም ክፋት ማሰብ አትችልም።
ነገ የወሃው ሙሌቱ ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያዊያን በይፋ ” ኒኩሌር ታጠቁ እንደማለት ነው” ሲሉ የተናገሩትም በዚሁ መነሻ መሆኑንን አመልክተዋል። “ምርጫ ካካሄደች ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” ሲባል የተሳካ ምርጫ ማካሄዷን፣ የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ሙሌት መሳካቱን አንድ ላይ አዳምረው ለኢትዮጵያዊያን ይህ ታላቅ የድል ዜና እንደሆነ እየተገለጸ ነው።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria, and the… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን በቅጡ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ።… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ