ኢትዮጵያን እየወጉ ያሉት በትግራይ በዕርዳታ ስም የገቡ ከፍተኛ ክፍያ የሚከፈላቸው ስውር ኤጀንቶች መሆናቸው ተሰማ። እነዚሁ ኤጀንቶች አስቀድመው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጡት የራሳቸውን የሳተላይት መገናኛ መሆኑ የዚሁ ማረጋገጫ አንዱ ማሳያ ሲሆን አገባባቸው ቁንጮ የትህነግ ሰዎችን በሱዳን በኩል ለማስወጣት ነበር።
ግጭት ባለበት ቦታና አገራት ሁሉ በከፍተኛ የክፍያ ስምምነት በማድረግ በተለያዩ ተቋማትና ሰብአዊ ድጋፍ ሰጪነት ስም የተለያዩ የኦፕሪሽን ማካሄድ የተለመደ ተግባራቸው ከሆኑት ኤጀንቶች መካከል የሚታወቁ በትግራይ መከተማቸውን ያመለከቱት ጉዳዩን የሚከታተሉ ዜጋ ናቸው።
በዕርዳታ ስም ትግራይን ያጥለቀለቁት እነዚሁ ተከፋይ ኤጀንቶች የትኛው የስለላ ተቋም እንደላካቸውና ስም መጠቀሱ ለጊዜው አግባብ እንደማይሆን የጠቆሙት አገር ወዳድ፣ እነዚህ ኢጀንቶች የትህነግን የተበጣጠሰ ሃይል ዘመናዊ መገናኛ በማስታጠቅ ዳግም የግንኙነት ሰንሰለት እንደገነቡላቸው ይናገራሉ።
“እጀባና ክትትል አይስፈልገንም” በሚል በረሃ ከመሸገው ሃይል ጋር እንዳሻቸው ሲገናኙ የቆዩትና የሳተላይት ግንኙነት መስርተው የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት የሃይል አሰላለፍ ሲከታተሉ እንደነበር መረጃውን ያጋሩት አመልክተዋል። መከላከያ እያዋዛ ነቅሎ ሲወጣ በስተመጨረሻ መረጃ የተሰጠው በዚሁ በዓለም አቀፉ የግንኙነት መስመር ምክንያት እንደሆነ ጨምረው ገልጸዋል።
በውጭ አገር ከትህነግ ሰዎች ጋር ተደራድሮ በለጋሽነት ስም የገባው ኤጀንት አስቀድሞ እርምጃ የተወሰደባቸውንና የተማረኩትን የትህነግ ቁልፍ ሰዎች ከትግራይ ለማስወጣት ስምምነት ነበረው። በአሜሪካ ከትህንግ ሴል ጋር ባለ ግንኙነት መነሻ ያገኙትን መረጃ ያጋሩን እንደገለጹት የነዚህ ኤጀንቶች ክፍያ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ትግራይን የሚወዱ ሁሉ በመልሶ ግንባታ ስም መዋጮ እያሰባሰቡ ነው። እነዚህ ኤጀንቶች የዲፖሎማሲው ጫና እንዲበረከት ከማድረግ ጀመሮ ለተመረጡ ባለልጣናት የመሳሪያ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ኔትዎርክድ የሆነ ከላለና ጥበቃም ይሰጣሉ።
ኤጀንቶቹ በተደጋጋሚ በሲዳን በኩል ነጻ ኮሪዶር እንዲከፈት ደጋግመው የሚጠይቁና በዚሁ ስራቸው ባላቸው የዲፕሎማሲ መስመር ሁሉ ጫና እንደሚፈጥሩ ዜናውን ያጋሩን ገልጸዋል። ” የሻቸውን ደብዳቤና መግለጫ ከፈለጉት ክፍል እንዲወጣና ለጫና እንዲውል መጠቀሚያ ማድረግ ይችላሉ” ያሉዋቸው ኤጀንቶች እጃቸው የትኛውም ዓለም ዓቀፍ ተቋምና አገራት መሪዎች ዘንድ እንደሚደርስ፣ ሰውር የሚመስል ግን ግልጽ ግንኙነት እንዳላቸው አመልክተዋል።
እነዚህ ኤጀንቶች ባስገቡት ኢትዮጵያ የማትቆጣጠረው ዓለም ዓቀፍ የግንኙነት ቻናል ወታደራዊ ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል መረጃ ከአጋሮቻቸው በድሳተላይት እየተቀበሉ ጦርነቱን እንደሚያግዙ ከጥቆማ ሰጪዎቹ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል። እነዚህ አካላት ተግባራቸው ጫና እየፈተሩ ባሉ አገራትና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት በገሃድ የሚታወቅ በመሆኑ ኢትዮጵያ እርምጃ ብትወስድባቸው ምንም የሚመጣ ችግር ሊፈጠር እንደማይችል ሊሎች አገሮች ለተመሳሳይ ተግባር ገብተው እርምጃ የተሰውሰደባቸው መኖራቸውን አመስዳክረው ገልጸዋል።
ትህነግ ሰፊ ሚሊሻና ሃይል አደራጅቶ፣ ወደ ሱዳን የሸሹትንና ሱዳን ውስጥ ግብጽ ያስታጠቀቻቸውን ሃይሎች ለማገናኘት የሱዳን ኮሪዶር እንዲከፈትለት ያለ የሌለ ሃይሉን እያስተባበረ እንደሆነ የትህነግ ታማኝ የውጭ ሚዲያዎች እየዘገቡ ነው። አሜሪካ በተደጋጋሚ ” አማራ” ብላ በመጥራት ይህ ኮሪዶር እንዲከፈት ዛቻ እያሰማች ነው። አውሮፓ ህብረትም በተመሳሳይ እነድ አሜሪካ እየዛት ሲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማት ደግሞ ለዕርዳታ ሲባል ኮሪዶሩ እንዲከፈት እየጠየቁ ነው። መንግስት በበኩሉ ” ይህ ጊዜው ያለፈበት ስልት ነው” ሲል ጥያቄውን አይቀበልም። ይሁንና ሰብአዊ ደጋፍ እንዲዳረስ አስፈላጊውን ቁጥጥር እያደረገ የሚፈለገውን የተቸገሩትን የመረዳት ሂደት እንደሚያግዝ አመልክቷል። ነጻ በረራ ወደትግራይ የሚባለውንም ውድቅ በማድረግ አዲስ አበባ ፍተሻ ተደርጎ ወደ ትግራይ መብረር እንደሚችላ አዲስ የአሰራር መመሪያ አውጥቷል።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria,… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ