የትግራይ ሕዝብ ነሳ አውጪ ግንባር / ትህነግ ” ብቸኛ የአሜሪካና አውሮፓ ጥቅም አስጠባቂ ነኝ፣ የተረጋጋች አገር መምራት የምችለው እኔ ብቻ ነኝ” በሚል የአሚሪካን ፖሊሲ አውጭዎች ለማሳመን በወር ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ተጠቆመ። ወጪው የነሳ አውጪውን ድርጅት ዓላማ የሚስተጋቡ የሚዲያ ሰዎችና ነጭ አክቲቪስቶች የሚከፈለውን አይተቃልልም።
አምስት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ለምግብ ችግርና አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ለከፋ ችጋር እንደታጋለጡበት የሚነገርለት የትግራይን ክልል ነጻ ለማውጣት የትጥቅ ትግል ላይ የሚገኘው ትህነግ፣ ይህን ያህል ከፍተኛ ሃብት የሚያፈሰው ለስምንት ከወስዋሾች የገዘፉ የህዝብ ግንኙነት የሚሰሩላቸው ድርጅቶች ነው።
በቂ መረጃ እንዳላቸው ጠቅሰው ከኢትዮ 12 ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ዶክተር ሓይማኖት እንዳሉት “ትህነጎች ስምንት የህዝብ ግንኙነት የሚሰሩላቸው ድርጅቶ ቀጥረዋል። ከለውጡ በፊት በወር አርባ ሺህ ዶላር ይከፍሏቸው ። ከልወጡ በሁዋላ ከ100 እስከ 140 ሺህ ዶላር እንደሚከፍሏቸው መረጃ አለኝ። ይህን ሁሉ ሃብት እያፈሰሱ ነው ኢትዮጵያ ስሟ እንዳየሳ፣ ጉዳይዋ እንዳይሰማ ሁሉንም በሮች የተቆጣጠሩት። ስልጣን ላይ እየሉ ባከማቹት የዘርፊያ ሃብት የህዝብ ግንኙነቱን ስራ በገንዘብ ቆላልፈው ይዘውታል።”
ለዲሞክራቶች፣ ለሪፐብሊካኖች፣ ለሃይማኖቶች ጥምረት፣ለጥቁር አፍሪካ አሜሪካኖች ጥምረት፣ ለዋይት ሃውስ፣ ለኮንግረንስ፣ Lesbian, Gay, Bisexual and Transgender. q ለሚባሉት ጥምረቶችና ለተቀረው የህብረተሰብ ክፍል በህዝብ ግንኙነት የሚሰሩ የታሰበባቸውና የተመረጡ አቅጣጫዎች መሆናቸውን የስምንቱን ተቋማት ሚና በማስረዳት ዶክተር ሃይማኖት አስረድተዋል። ሙሉ ቃለ ምልልሱን እዚህ ላይ ይመልከቱ። የዚዲዮውን ምልልስ ደግሞ በዩቱብ ቻናላችን እዚህ ላይ ያገኙት።
- “ጀነራሉ ያዋቀሩት ካቤኔ እና እየሄዱት ያለው አካሄድ የነበረውን ሰላም የሚያሳጣ ነው ” የኢሮብ ሲቪክ ማህበርበቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በስምምነቱ የቃል ኪዳን ሰነድ መሠረት አካታች ሊሆን እንደሚገባ የኢሮብ ማህበረሰብ ሲቪክ ማህበር ዋና… Read more: “ጀነራሉ ያዋቀሩት ካቤኔ እና እየሄዱት ያለው አካሄድ የነበረውን ሰላም የሚያሳጣ ነው ” የኢሮብ ሲቪክ ማህበር
- “በጀግንነት የተጠበቀች፤ በመስዋዕትነት የጸናች”ዓለም ፊቱን አዞረባት ልጆቿ ግን በስስት ተመለከቷት፣ ዓለም ዘመተባት ልጆቿ ግን ለክብሯ ዘመቱላት፣ ዓለም አዋከባት ልጆቿ ግን አረጋጓት፣ ዓለም… Read more: “በጀግንነት የተጠበቀች፤ በመስዋዕትነት የጸናች”
- በደቡብ እስያ ያንዣበበው የጦርነት ስጋትህንድ በፓኪስታን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መዘጋጀቷን የሚያመለክቱ ታማኝ የደህንነት መረጃዎች እንዳገኙ የፓኪስታን የማስታወቂያ ሚኒስትር ገልፀዋል፡፡ ሚኒስትሩ አታውላህ ታራር ህንድ… Read more: በደቡብ እስያ ያንዣበበው የጦርነት ስጋት<br>
- ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በኒኩለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንድትሰጥ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ተመረጠች።የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ አለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA)፣ በቻይና መንግስት የ Tsingua University፣ ኦንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ… Read more: ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ሀገራት በኒኩለር ኢንጂነሪግ የመጀመሪያ ዲግሪ እንድትሰጥ በአለም አቀፍ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ተመረጠች።
- በጅቡቲ ኢትዮጵያውያኖች በ3 ቀን ውስጥ ውጡ – ዲፕሎማሲ በአስቸኳይ!በጣም ብዙ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ ነው ያለው፣ ከኢትዮጵያዊ ቀጥሎ የመኖች ናቸው፡፡ ግን ሁሌም ውጡ የሚባሉት ኢትዮጵያውያኖች ናቸው፡፡ ምክንያቱን አላውቅም፡፡ በፖሊስ… Read more: በጅቡቲ ኢትዮጵያውያኖች በ3 ቀን ውስጥ ውጡ – ዲፕሎማሲ በአስቸኳይ!