ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ኢ/ር ስለሺ በቀለን፣ ጠ/ሚ አብይ አህመድ ብርቱካን ሚደቅሳን አመጡ፡፡
.
ኢ/ር ስለሺ ኒውዮርክ፣ ለተባበሩት መንግስታት ይሰሩ ነበር፤ ትልቅ ደሞዝ ነበራቸው፤ ልጆቻቸው ጥሩ ትምህርት ይማሩ ነበር፡፡ ደምወዛቸውም ሆነ ኑሯቸው ኢትዮጵያ አይታሰብም፡፡
ብርቱካን ሚደቅሳ ሀርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛ ዲግሪዋን ሰርታ እዚያው አሜሪካ እየኖረች ነበር፡፡ ኢትዮጵያ እያለች በወጣትንቷ ብዙ መከራ ተቀብላለች፤ ብዙዎች በገንዘብና በፖለቲካ ጥቅም ለሚቸረችሩት ፍትህ አንገቷን ሰጥታለች፤ ስለዲሞክራሲ መከበር ፖለቲከኛ ሆና ምርጫ በማሸነፏ በተደጋጋሚ ታስራለች፤ አሸባሪ ተብላ እድሜ ልክ እስራ ተፈርዶባታል(?)፡፡ በወጣትነቷ በተጋተችው የሚያንገሸግሽ መከራ የተነሳ ከህልሟ ተፋትታ በስደት ትኖር ነበር፡፡
.
ሁለቱ ጠ/ሚንስትሮች ሁለቱን ወደሀገራቸው ጋበዝዋቸው፡፡ ለኢ/ሩ የድሎት ኑሮ፣ ለብርቱካን የደረሰባት መከራ አላስቀራቸውም፡፡ ይልቁንም ለሀገራቸው ያላቸው ቀናኢነት፣ ለወገናቸው ያላቸው ፍቅር ጥሪውን እንዲቀበሉ አደረጋቸው፡፡
.
ቁምነገሩ ጥሪውን ተቀብለው መምጣታቸው አይደለም፤ ያመጣቸው የሀገርና የወገን ፍቅር ላይ ለእውነት ያላቸው ታማኝነትና ክብር ተደምሮ በአጭር ጊዜ የሰሩት ተግባር እንጂ፡፡ ኢትዮጵያ ከውስጥ የከሀዲ ጁንታዎች፣ ከውጭ የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች ጥቃት በጠነከረባት በዚህ ወቅት፣ ኢ/ር ስለሺ የኢትዮጵያ የልማት ጉዞ ከተጀመረበት ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ጋር፣ ወ/ት ብርቱካን ደግሞ የዲሞክራሲያዊነትና ፍትሀዊነት ፍንጭ ከታየበት፣ በተወዳዳሪ ፓርቲዎች ተቀባይነት ካገኘ፣ ከሁልም በላይ ሰላማዊ ሆኖ ከተጠናቀቀው 6ኛው ምርጫ ጋር ግብራቸው በታሪክ ሲወሳ ይኖራል፡፡
.
ወደ ሀገራችሁ ግቡና ለወገናችሁ ስሩ ሲባሉ፣ ‹‹ስንት ይከፈለናል? ምን አይነት ቤት ይሰጠናል; . . ወዘተ. እያሉ የሚደራደሩ አሉ፡፡ በውጭ የበጎ አድርጎት ድርጅቶች ጥያቄያቸው ተሟልቶ መጥተው በአመታት ጠብ የሚል ስራ ያልሰሩ በርካቶች ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች ሳስብ ነው፣ . ‹‹ካመጡ አይቀር ጠማቂውን ነው፤ ወገኑን በደስታ የሚያሰክረውን! የሚያንቃርርማ እዚህስ ማች ጠፋ!›› የምለው፡፡
TIPS
Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
The Wars We Still Can Stop
Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
A Nation Silenced: How the 1993 Referendum Stripped All Ethiopians of Their Sea
The 1976 TPLF Manifesto: TPLF’s “Republic of Greater Tigray”
Away from the global spotlight, Eritreans are trapped in a garrison state
Testimonials of a Sudanese Intelligence Officer on the Proxy war between Sudan and Ethiopia from 1970s to early 1990s
Ethiopia-Eritrea Tension: A Volatile History that Never Truly Ended – Could Assab Become Africa’s Crimea?
“As an outlier among the five tplf leaders, I wasn’t part of the armed struggle tradition”
Former Tigray fighters say no to war
Don’t Risk Your Future: The United States Cracks Down on Illegal Immigration
Counter-Video by EBC Challenges EBS Broadcast, Sparks Public Outcry Over Alleged Misinformation
Ethiopia and Eritrea Slide Closer to War amid Tigray Upheaval
Sea Outlet Serious and Unabated Agenda for Ethiopia: Retired Lieutenant General Yohannes
Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
Egyptian, Eritrean FMs reject involvement of non-bordering countries[Ethiopia] in Red Sea security