በአሁኑ ሰዓት በፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ሰፊ ስራ እየሰራ ያለው የትህነግ ሃይልና ደጋፊዎች ጀነራል ጻድቃንን በመጥቀስ ወደ አዲስ አበባ ለመገስገስ የሚያግድ ነገር እንደሌለ እየገለጹ ነው። አማራ ክልል በጥቅል ክተት የጥረአ ሲሆን ዳንሻ ላይ ዛሬ ሁሉም እንዲነሳ ታዟል።
ኔሽን የጠቀሳቸው ጄኔራሉ በቆቦና ወልደያ ግንባር ድል ቀንቶታል ያሉት ሰራዊታቸው ወደ አዲስ አበባ ለመገስገስ ምንም ችግር እንደሌለበት አመልክቷል። ይሁን እንጂ እንዴትና የት ይህ ሊሆን እንደሚችል የተብራራ ነገር የለም።
ሁሉም የተካተቱበት የኢትዮጵያ ጦር፣ እንደቀድሞው ወደ ትህነግ ክልል ከመግባት ይልቅ እያፈገፈገ በመሳብ ከቦ ጉዳት የማድረስ ስልት መከተል ከጀመረ ወዲህ ከፍተኛ ሰብአዊ ጉዳት እንደደረሰበት እየተነገረ ነው።
በብዛት ሃይል እያስለፈ ሰብሮ የሚገባውን ሃይል በመሸሽ እያሳሱ መምታት የሚለው አዲስ ስትራቴጂ ሰፊ ጉዳት እንዳደረሰበት በየአቅጣጫው መረጃ ቢወጣም የትህነግ ሃይል ግን እጅግ እያተቃ እንደሆነ መናገር ከጀመረ ሳምንት አልፎታል። አቶ አገኘሁ ዛሬ እንደተናገሩት ትህነግ የአባቶቹን የባንድነት ታሪክ በማደስ ያለ የሌለ ሃይል፤ኡን አስለፎ የባንዳነት ጦርነት መክፈቱን አመልክተዋል። አያይዘውም በውልቃይት የሚኦከረው መጠነኛ ትንኮሳ የተመከተ ሲሆን በራያ ግንባር እየተፋለሙት እንደሆነ አመልክተዋል።
ለጥንቃቄ ባሉት መልዕክታቸው ” ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” ሲሉ ህዝብ የፕሮፓጋንዳ ሰለባ እንዳይሆን መክረዋል። የፌስ ቡክ አንቂዎችም ጦርነቱን በማህበራዊ ሚዲያ ለመምራት መሞከራቸውን እንዲሁም መረጃ መስጠት እንዲያቆሙ ተማጽነዋል። ሁሉም ዓይነት መረጃ መስጠት እንደሚችገር አመልክተው” ሕዝብ ከመንግስትና ከመከላከያ ትክክለኛ መረጃ ይስማ” ሲሉ ተናግረዋል።
ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ለመሄድ የሚያግደው ሃይል እንደሌለ በሚገልጽበት በአሁኑ ሰዓት ህዝብ ከዳር እስከዳር ” ትህነግ አሸባሪ ነው፤ እስከመጨረሻው እስኪወገድ አስፈላጊውን ዋጋ እንከፍላለን” በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እያደረገ ይገኛል። ትህነግ እንዳለው ሃይሉ እየተበተነ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የሚያስችል አጋታሚ እንኳን ቢገኝ ሊሳካ እንደማይችል ዜናውን የተከታተሉ ከዜናው ስር ጽፈዋል።
በትግራይ ” ወገን አልባ ተብሎ እንደተመታው የመከላከያ ሰራዊት፣ የትህነግም ሃይል በተመሳሳይ ከትግራይ ሲወጣ ደጀን አይኖረም፤ ተመሳሳይ እርምጃ ይጠብቀዋል፤ ይህንን ጠንቅቆ ያውቃል። ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ካልሆነ በስተቀር …” የሚል አስተያየት ሰፍሯል። በአማራ ክልል ሙሉ በሙሉ ክተት በመታወጁና ከትህነግ ጋር በተያያዘ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ በመታዘዙ ጦርነቱ የህዝብ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ እንደሚያደርገው የጠቀሱም አሉ። ከዛም በላይ ሰላማዊ ዜጎች እንዳይጎዱ ያሳሰቡም አሉ። ከስር የዳንሻው ትሪ ሪፖርት ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የተውሰደ ነው።
ሁሉም አማራ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥሪ አቀረቡ። ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 18/2013 ዓ.ም
በዳንሻ ከተማ ዛሬ ታላቅ ሕዝባዊ ሰልፍ ተካሂዷል። የሰልፉ ዓላማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ክብር ለመስጠት፣ ለሁለተኛው ዙር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የውኃ ሙሌት ደስታን ለመግለጽ፣ አሸባሪውን ትህነግ ማውገዝ እና ሕዝቡ የሕልውና ዘመቻው ተሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ ነው ተብሏል። ውስጣዊ አንድነትን በማጠንከር የጋራ ጠላትን በብቃት መመከት እንደሚገባ በሰልፉ ተነስቷል።
ለዚህም ሕዝቡን መስለው ለጠላት የሚሠሩ አካላትን መምከር ይገባል፤ የማያርፉ ከሆነ ግን ለሕዝቡ ህልውና ሲባል የማያዳግም ርምጃ ሊወሰድ እንደሚችል ተመላክቷል። የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ኀላፊው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ “ዛሬ የተገናኘነው ዲስኩር ለማሰማት ሳይሆን የመጣብንን ወራሪ አውቀን የመጨረሻውን ፍልሚያ ለመግጠም ነው” ብለዋል።
ኮሎኔሉ አሸባሪው ትህነግ አማራን ለማጥፋት መነሳቱን አንስተዋል፡፡ ይህንን ለመመከትም የአማራ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት አድርጎ በነቂስ ወደ ግንባር እንዲሰለፍ ነው ጥሪ ያቀረቡት። የህልውና ዘመቻው የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ በመሆኑ ራስን ለመከላከልና ለማስከበር መሰለፍ ይገባል ብለዋል። ለአማራና ለኢትዮጵያ መሞት ክብር ነው ብለን ቀድመን መሰለፍ አለብንም ብለዋል።
ኮሎኔል ደመቀ ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ቁርጥ ቀን በመሆኑ ማንኛውም የታጠቀና ትጥቅ የሌለው ኀይል ወደ ማክሰኞ ገበያ፣ ወፍ አርግፍና ሑመራ መክተትና በጋራ ዘምቶ ጠላትን ማሸነፍ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። ክብራችንን ስለምንመርጥ ሁላችንም ለሀገራችን መሞት ይገባናል ያሉት ኮሎኔል ደመቀ የሃይማኖት አባቶችም ጦር ግንባር ድረስ ተሰልፈው በጸሎትና በዱአ ሊያግዙ ይገባል ብለዋል። አቅም ያለው ታጥቆ መግጠም ያልቻለ ደግሞ በሞራልና በስንቅ አቅርቦት ሊደግፍ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በርሃ ያለ ባለመሳሪያ ሁሉ ከነገ ጀምሮ ወደ ግንባር እንዲከትም መመሪያ ሰጥተዋል። የከተማው ሕዝብ በሰልፉ ላይ “የማንነት ጥያቄ ዴሞክራሲያዊ መብታችን ነው፤ የአማራ ሕዝብ በሀገር መከላከያ ሠራዊት አይደራደርም፤ ለአማራ ልዩ ኀይል፣ ለፋኖና ሚሊሻ እንዲሁም ለመከላከያ ክብር ይገባል፤ እኛ አማራዎች የምናወራርደው እንጂ የሚያወራረድብን ሂሳብ የለም፤” እና መሰል መልእክቶችን አንግቦ ነው አደባባይ የወጣው፡፡
አስተያየታቸውን ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሰጡ የከተማው ነዋሪዎችም ስለ ክብራቸው፣ ስለ ነጻነታቸውና ስለ ሀገራቸው ሕልውና ሲሉ ግንባር ለመሰለፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። በሰላማዊ ሰልፉ የዞኑን አስተዳዳሪ ጨምሮ ሌሎች አካላትም ተገኝተዋል።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ