ያለምንም ቅደም ሁኔታ የተኩስ ማቆም በመታወጁ ምክንያት ከመከላከል ባለፈ ሙሉ ወጊያ ውስጥ ከመሳተፍ የታቀበው የአገር መከላከያ ሰራዊት በድንገት ሙሉ ሃይሉን እኒጠቀም ሊታዘዝ እንደሚችል የኢትዮ12 የመረጃ ሰዎች አስታውቀዋል።
“መቼና እንዴት?” የሚለውን ጉዳይ ወደሁዋላ በመተው መረጃውን ያካፈሉን እንዳሉት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ መንግስት በድጋሚ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ሳቢያ ወደ ሙሉ እምሶ ማጥቃት ሊዛወር እንደሚችል ተድጋጋሚ ማሳሰቢያ እያቀረበ ነው።
አውሮፓ ኮሚሽንና አሜሪካ በተደጋጋሚ በወኪሎቻቸው አማካይነት መንግስት እጅግ መታገሱን አስመልክቶ መረጃ ተሰጥቷቸዋል። የመረጃው ሰው እንዳሉት ከታክቲክም አንጻር የትህነግ ሃይልም ላይ እርምጃ ለመውሰድ ጊዜ ደርሷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ባለፈው ሳምንት ” በጥብቅ ሚስጢር እየተዘጋጀን ነው። ጁናታው ይነቀላል። ይህን ህዝብም ዓለምም ያየዋል” በማለት ጊዜው ሩቅ እንዳልሆነ መናገራቸው አይዘነጋም።
የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ መኮንኖችና የህዝብ ግንኙነት ክፍሉም በየመድረኩ ” ስንታዘዝ ሁሉንም የማድረግ አቅም አለን” በማለት ለህዝብ ቃል እየገቡ ነው። የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ በበኩላቸው ” ከመቼውም ጊዜ በላይ ታትቀንና ተዘሃጅተን ማናቸውንም ትቃት በተፈለገው ቦታ ለመፈጸም ትዕዛዝ እየተተባበቅን ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።
በገለልተኛ ካል ባይረጋገጥም በራያ ግንባር ትሀን አንዳንድ ቦታዎችን መያዙ ቢነገርም ” ታገሱ” የሚሉ ድምጾችም እየተሰሙ ነው። የአማራ ክልል በማይጸብሪ አቅጣጫ ጥቃት ለመጀመር ዝግጅት ማተናቀቁን የአካባቢውን ፋኖ አመራሮች በማቅረብ በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። የአርበኛ ጎቤ ልጅ ” ያውቁናል እኛ ስንመጣ ይሸሻሉ” ሲል በተድመጠበት ቪዲዮ ሰፊ ቁጥር ያለው የአካባቢው አርበኛ ስንቁን ሰንቆ እየገባ ነው።
በከፍተኛ ጀነራሎችና አመራሮች ራሱን መልሶ ያደረጀው የአማራ ልዩ ሃይ በማይጸብሪ ከገፋ ነገሮች እንደሚቀያየሩ ባለሙያዎች ይገምታሉ። በትግራይ ከፍተኛ በደል ደርሶበታል የተባለው ሰራዊት አሁን ላይ ከድካምና ከብስጭት መዳኑንን የሚናገሩት ምንጮች ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል ስለተቀላቀላቸው ሃይላቸው መገንባቱን ገልጸዋል። መንግስት ለመከላከያ ሙሉ መመሪያ ስለመስጠቱ ይህ እስከታተመ ድረስ በይፋ ያለው ነገር የለም። የግጭቱ መስፋትና ግጭቱን አስመልክቶ ከአንድ ወገን የሚወታው ሪፖርት ግን ግርታ ፈጥሯል። ” ታገሱ” የሚሉ ወገኖች ደግሞ ሰፊ ኦፕሬሽን እንደሚከናወን ያምናሉ።

- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል