ሀምሌ 10/2013 (ኢዜአ) ጨፌ ኦሮሚያ በክልሉ የፍትህ ተደራሽነትና ትክክለኝነትን ለማረጋገጥ ያግዛል ላለው የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ምስረታ እውቅና የሚሰጥ አዋጅ አጸደቀ።
ጨፌው የ2014 የክልሉ በጀት 124 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አጽድቋል።
ጨፌ ኦሮሚያ እያካሄደው የሚገኘው 14ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀኑ የባህላዊ ፍርድ ቤቶች ምስረታ እውቅና የሚሰጥ አዋጅን ማጽደቅን ጨምሮ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል። ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ ከቀበሌ ጀምሮ የሚመሰረትና የክልሉ ሕዝብ በቀደመው ባህሉና ወጉ መሰረት ፍትህ እንዲያገኝ ያግዛል ነው ተብሏል።
ፍርድ ቤቶቹ በተለይ በመደበኛ ፍርድ ቤቶች በፍትህ አሰጣጥ ሂደቱ ላይ ፈተና የሆነውን ሀሰተኛ ምስክርነት ለመቀነስ እንደሚረዳም ተገልጿል። በዋናነት የክልሉ ሕዝብ የቀደመ ባህላዊ የፍትህ አሰጣጥ ሂደትን ተከትሎ የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችን ለመፍታት ያስችላልም ተብሏል።
ረቂቅ አዋጁን ያቀረቡት የህግ ተመራማሪው አቶ ሚልኪ መኩሪያ እንደሚሉት ፍርድ ቤቶቹ የፍትህ ተዳራሽነትን የበለጠ ያጠናክራሉ። ከዚህ በፊት በአብዛኛው የክልሉ ነዋሪዎች ፍትህ ለማግኘት ረጅም ጉዞ በማድረግ ለአላስፈላጊ ወጪ ይዳረጉ ነበር ነው ያሉት።
በአዋጁ መሰረት የሚቋቋሙ ፍርድ ቤቶች የክልሉ ሕዝብ ፍትህን በቅርበትና በእውነት ላይ ተመስርቶ እንዲያገኝ ይረዳዋል ብለዋል። ፍርድ ቤቶቹ የመጀመሪያና በፍርድ ሂደቱ ያልረካው አካል አቤት የሚለበት ሁለተኛ እርከን ፍርድ ቤት እንዲኖረው ሆኖ እንደሚደራጅም ገልጸዋል።
ከዚህ ባለፈ ባህላዊ ፍርድ ቤቶቹ አምስት አባላት ያሉትና አባላቱም ለስምንት አመታት የሚያገለግሉ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። እነዚህ ፍርድ ቤቶች ከመደበኛና ከማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ጎን ለጎን የሚሰሩ ሲሆን ለክልሉ ህዝብ ትልቅ ጥቅም የሚሰጡ እንደሆነም ገልጸዋል።
በዚሁ መሰረት አዋጁ በጨፌው አባላት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል። በተመሳሳይ ጨፌው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አዳምጦ ከተወያየበት በኋላ ሪፖርቱን በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል።
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የኦሮሚያ ክልል የአስር ዓመት እቅድ ላይ ሰፊ ውይይት አድርጎ እቅዱን አጽድቆታል። በመጨረሻም የጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት የክልሉን ኦዲተር ጀነራል እቅድ አፈጻጸም፣ የ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት እንዲሁም የ2014 ዓ.ም በጀት ላይ ውይይት በማድረግ አጽድቆታል።
በዚህም የክልሉ የ2014 በጀት 124 ቢሊዮን ብር ለካፒታልና ለተለያዩ ወጪዎች እንዲውል አጽድቋል። በጀቱ 19 ቢሊዮን ብር ለተለያዩ ወጪዎች፣ 29 ቢሊዮን ለካፒታል በጀትና 73 ቢሊዮን ብር ለወረዳዎችና ለከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ እንዲሁም 600 ሚሊዮን ብር ለተጠባባቂ በጀት ተይዟል።
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and International Studies… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር አትሌቲክን በድምሩ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል