ሲገባና ሲወጣ አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ አርፎ የሚፈለገው ቁጥጥር ከተደረገ በሁዋላ ለመንቀሳቀስ በተደረሰ ስምምነት መሰረት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት በሚል ከአዲስ አበባ ወደ የመጀመሪያ በረራ ወደ መቀሌ ማድርጉ ተሰማ። የተሸከመውን አድርሶ አውሮፕላኑ አዲስ አበባ መመለሱ ታውቋል።
አሸባሪው ቡድን ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ወደ መቀለ ዓለም ዓቀፍ በረራ እንዲደረግ በሽብር ቡድኑ ቃለ አቀባይ በኩል ማስጠንቀቂያ አዘል መግለጫና ማብራሪያ ተላልፎ ነበር።
ኢዜአ እንዳለው ንብረትነቱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሆነው አውሮፕላን ዛሬ ወደ መቀሌ በረራ ያደረገው መንግስት ያዘጋጀውን አሰራር አክብሮ ለመስራት ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነትካገኘ በሁውላ ነው።
ይኸው ንብረትነቱ ንብረትነቱ የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሆነው አውሮፕላን አስፈላጊው ምርመራ ተደርጎለት ወደ መቀለ ሲጓዝ ስድስት ሰዎችን ጭኖ ነበር። ኢዜአ የውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ሆነው ይህንን ሲከታተሉና ሲያስፈጽሙ ከነበሩ አካላት ያገነው እንደሆነ ጠቅሶ እንዳለው መጀመሪያ በረራው የተካሄደው መንግስት ለትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ በአየር እንዲጓጓዝ በፈቀደው መሰረት ነው።
ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ የተደረገው በረራ በምግብና ስነ-ምግብ አቅርቦት የሚሳተፉ በክልሉ ከሚገኙ ወረዳዎች መካከል በ21 ወረዳዎች ለሚሰሩ ሰራተኞች ደመወዝ ፣ ለስራ ማስኬጃ፣ ለምግብ ቁሳቁስ መጫኛና ማውረጃ የሚውል ገንዘብ ለማድረርስ መሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል።
አውሮፕላኑ ወዲያውኑ አዲስ አበባ ተመልሷል።መንግስት በክልሉ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ በተለያዩ መስኮች በትኩረት የሰራ ሲሆን፤ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ክልሉ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ በርካታ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ ማድረጉ ይታወሳል።
መንግስት የሰብዓዊ ድጋፉን በአውሮፕላን ማከናወን ለሚፈልጉ አካላት ሲወጡም ሆነ ሲገቡ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን ብቻ እንዲጠቀሙ ያስታወቀው ጥያቄው ሳይቀርብ ለመተባበር ዝግጁነቱን በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዲፕሎማቶችና ዓለም አቀፍ ተቋማት ሰራተኞች ባስታወቀበት ወቅት እንደነበር ይታወሳል።
ረሃብን የፖለቲካ ማገገሚያ ስልት አድርጎ የተነቀሳቀሰ መሆኑ የሚነገርለት አሸባሪ ቡድን በዛሬው እለት ስልሳ የሚደርሱ ለተራቡ ዜጎች እህል ጭነው በመጓዝ ላይ ያሉ ተሽከርካሪዎች በአፋር በኩል ወደ ትግራይ እያመሩ ባለበት ሁኔታ ተኩስ ከፍቶ መንገዱን መዝጋቱ ዛሬ ረፋዱ ላይ መገለጹ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎ በእርዳታ ማከፋፈሉ ተግባር የተሰማሩት ወገኖች እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center for Strategic and… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም ጋር ደርሷል። ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል