የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ኢትዮጵያውያንን በልማት ማገዝ እንሻለን፣ ያ የሚሆነው ግን የውሃ ድርሻችንን የማይነካ ከሆነ ነው ብለዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ በሀያ ከሪማ ብሄራዊ ኮንፈረንስ ላይ ትላንት ባደረጉት ንግግር ሲሆን፣ ብሄራዊ ጥቅማችን ማስከበር የማይታለፍ ቀይ መስመር ነው ብለዋል፡፡
ግብጽ ብሄራዊ ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጭ አላት ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ አማራጮቹን እንደ ሁኔታዎች አስፈላጊት መጠቀም ይገባል ሰሉ ነው የገለጹት፡፡ ኢትዮጵያ እየገነባች ባለው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላቸው ስጋት ተገቢ እንደሆነ የገሉት ፕሬዝዳንት አል-ሲሲ፣ ስለግድቡ በዝርዝር እና በተረጋጋ መንፈስ መነጋገር ይሻል ብለዋል፡፡
“እኛ በጉዳዩ ላይ ያለንን ስጋት በምክንያት እና በተጠና እቅድ ነው የምናየው፡፡ እኛ የቅዠት ህይወት አልኖርንም፡፡ የናንተንም ስሜት ለመጠምዘዝ አንፈልግም” ሲሉ ስብሰባው ሲካፈሉ ለነበሩ ሰዎች መናገራቸውን ኢጅብት ቱደይ ዘግቧል፡፡
“ከኢትዮጵያውንና ከሱዳናውያን ጋር የዓባይ ወንዝ ለመልካም ትብብር በር እንደሚከፍት ተነጋግረናል፤ ለሁላችንም መልካም እንዲሆን እንሻለን፤ ኢትዮጵያውያን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ለልማታቸው እንዲያውሉት እንሻለን፤ የኢትዮጵውያንን የኑሮ ሁኔታ እንዲሁ እንዲሻሻል እሻለን፤ ግብጽ የኢትዮጵያውንና የሱዳናውያን ህይወት ብቻ ሳይሆን የመላ አፍሪካ ህይወት እንዲሻሻል ድጋፍ ማድረግ ትችላላች፡፡ ይህ የሚሆነው ግን በአንድ ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ያም የግብጽ የውሃ ድርሻ የማይነካ ከሆነ ነው” ሲሉ አክለዋል፡፡
ጉዳዩ ቀላል ነው፤ እኛ ሙያተኛና የግብርና ምርቶችን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እንልካለን፤ እነሱ ደግሞ የውሃ ድርሻችን እንዳይነካ ያደርጋሉ ማለታቸውንም ዘገባው አስነብቧል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን ወደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የወሰዱት በጉዳዩ ዙሪያ የዓለም ዓቀፉን ማህበረሰብ ትኩረት ለማግኘት መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
አብዱልፈታህ አል-ሲሲ በዓለም ዓቀፍ ህግ አግባብ ተስማምተን በሰላም እና ብልፅግና እንኑር ሲሉ ለኢትዮጵያና ለሱዳን ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል፡፡ ኢትዮጵያ በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ አሳሪ ህግ መፈረም የመጪውን ትውልድ የመበልጸግ እጣ ፋንታ ስለሚገድብ እንዲህ አይነት ግደታ ውስጥ አልገባም ማለቷ ይታወቃል፡፡
የግብጹ ሀያ ከሪማ የሚባለው ብሄራዊ ፕሮጀክት የ50 ሚሊየን ዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ ለማሻሻል የተወጠነ ሲሆን፣ ለፕሮጀክቱ 700 ቢሊየን የግብጽ ፓውንድ ወጪ እንደሚደረግበትና በሶስት አመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል ማለታቸውን ዋልታ ዘግቧል።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza,… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም