መኪናው የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ነው። የመኪና ውሰት ጥያቄ ያቀረበው ደግሞ የዓለም የምግብ ድርጅት ነው። በውሰት የተጠየቀው መኪና የሚጭነው ኢትዮጵያ የምታቀርበውን ስንዴ ነው። ስንዴውን የሚያከፋፍለው የዓለም የምግብ ድርጅት በትግራይ ነው። ከመንገዶች ባለስልጣን በውሰት የተሰጠውን ተሽከርካሪ የሚያሽከረከረው የመቀለ ልጅ ነው።
መኪናው የኢትዮጵያ፣ ስንዴው የኢትዮጵያ፣ አከፋፋይ የዓለም ምግብ ድርጅት፣ ሾፌር የመቀለ ልጅ። እህሉ ተጭኖ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል ለተባሉት ሰዎች ተላከ። አሽከርካሪው እንዲያደርስ የተነገረው ስፍራ ለማራገፍ ጉዞ ጀመረ። ሄደ። በሁለተኛው ቀን ብቻውን ተመለሰ። መኪናውንም ዕርዳታውንም የትህነግ ታጣቂዎች እንደወሰዱበት ገለጸ። ድርጅቱ ሪፖርት ሲያቀርብ የኢትዮጵያ ሰራዊት እርዳታ ማስተጓጎሉን አመለከተ። ይህ አዝናኝ ግን እጅግ ልብ የሚያደማ የዕርዳታ ስርጭቱና የረሃቡ አጀንዳ ውስጥ የተደበቀ አንዱ ማሳያ ነው።
ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነ የዕርዳታ ስራ ሃላፊ ኢትዮጵያን ” ቱጃሯ” ይላታል። የትግራይ ውስጥ ዕርዳታ ስራን ደግሞ ” ድራማ” ይለዋል። እንደ እሱ አባባል ኢትዮጵያ የምታቀርበውን ሰባ ከመቶ እርዳታ የውጭ ለጋሽ የተባሉት ክፍሎች እንዲያከፋፍሉ መፈቀዱ ድራማው የተዋቀርበት ገዢ ጉዳይ ነው።
እሱ እንደሚለው የዓለም የምግብ ድርጅትም ሆነ ሌሎች ለጋሽ ተቋማት እህል ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማድረስ የተለየ የሚያደርጉት ነገር የለም። መንገድ በሌለበት አየር ወይም ሄሊኮፕተር አምጥተው አያሰራጩም። እህሉን ተረጂዎች ዘንድ ለማድረስ የሚጨምሩት አንዳችም ግብዓት አለመኖሩ እየታወቀ ስለምን እንዲህ እንዲፈልጡና እንዲቆርጡ ፈቃድ እንዳገኙ ግልጽ አይሆንለትም። ግን የዕርዳታ ስራ ዋና ተግባብሩንና ለእርዳታ የሚመጡ ልውጦች ተጋባራቸውን ስለሚያውቅ እነሱን ማገድ አስቸጋሪ መሆኑንን ያምናል።
ድራማው ኢትዮጵያ በራሷ መንገድ፣ ራሷ ባቀረበችው ስንዴ፣ በራስዋ ተሽከርካሪ፣ በራስዋ ዜጎች ላይ ወንጀል እንደሰራች ተደርጎ ይመሰከርበታል። መረጃውን የሰጠን ይህ መረጃ ከጦርነቱና ጦርነቱን ተያይዞ ከሚነሳ ማንኛውም መወነጃጀል ጋር እንዲገናኝ አይፈልግም። ግን ዕርዳታውን አስመልክቶ ድራማው እጅግ አስገራሚና ለማመን የሚቸግር ነው።
በትህነግ፣ በዕርዳታ ድርጅቶችና በሚዲያዎች ዘንድ እስከላይ የተያያዘ ዘመቻ ለመኖሩ እንደምሳሌ ያነሳውን ጉዳይ ሲያፍታታ” አሽከርካሪው ባዶ እጁን መጥቶ ተወስደብኝ አለ። በቃ” ካለ በሁዋላ ሪፖርቱ ሲሰራ መሆን ያለበት መኪና መወሰዱን፣ መኪናው በውሰት ኢትዮጵያ የሰጠችው መሆኑ፣ የአሽከርካሪው ስምና አድራሻ፣ የተወሰደው እርዳታ መጠን፣ ማን እንደወሰደው፣ እንዴት እንደተወሰደ፣ የተወሰደበት ቦታና በሃብት ሲለካ መጠኑ ተሰልቶ በሪፖርቱ መካተት ሲገባው ” ኢትዮጵያ ወታደሮቿ አስተጓጎሉ” የሚል ድራማ አዘል ስክሪፕት ተጽፎ እንደሚላክ ያስረዳል።
የሳተላይት ስልክ በጃቸው በመሆኑ ይህንኑ ለሚዲያዎች ያሰራጫሉ። ዜናው የቀድምና ሪፖርቱ ይከተላል። ከዛ መግለጫው ይዘንባል። ኢትዮጵያ እንደ ዘነዘናው ታሪክ ከየአቅጣጫው ትነረታለች። በርካታ ጉዳዮች አሉ።
ዕርዳታ ለማን፣ የትና ምን ያህል እንደሰጡ ሪፖርት ሲጠየቁ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ለከፍተኛ ብክነትና ዘረፋ ያጋለጠ ጉዳይ ሆኗል። ገቢው ለማን እንደሚሆን ባይታወቅም ስንዴ ገበያ ላይ ሲሸጥ ይታያል። ይህ ሁሉ ተዳምሮ ኢትዮጵያ በስምንት ወር ውስጥ 100 ቢልዮን ብር ታልባለች። ብሩ መውጣቱ ሳይሆን ከሌላት ላይ ባወጣቸው መጠን ተሰድባለች፣ ተወግዛለች። ቱጃሯ ኢትዮጵያና የትግራይ የዕርዳታ ድራማ እንዲህ በሚመስሉ ድራማዎች የታጀበ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ደሞዝ የሚከፈላቸው የነበሩ በረሃ እየኖሩ ለወር ደመውዝ እየመጡ ይወስዳሉ። መብራትና ውሃ ከተስተካከለ በሁዋላ በተጠቀሙት ልክ እንዲከፍሉ አለመጠየቃቸውንም ይኸው የመረጃ ሰው ይናገራል። መንግስት ይህን ማድረጉ አግባብ እንደሆነ ቢያምንም ” ቱጃሯ ኢትዮጵያ በምላሹ መቀጥቀጧ፣ ለቃ ከወታችም በሁዋላ የነጮቹ አሽሙር መቀጠሉ ይገርማል። ዓላማቸውም ግልጽ እየሆነ ነው” ሲል ግርምቱን ያስቀምጣል።
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት።… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል