ክልሎች ትህነግን ” ፈራንህ” እያሉት ነው። “ዳግም እንዳትመጣ እዛው ባለህበት እናፍንሃለን” እያሉት ነው። “ግጠኸናል፤ ገድለኸናል፣ ቶርቸር አድርገኽናል፣ አፈናቅለኸናል፣ መሪታችንን ሲያሻህ ትቸበችባለህ፣ ሲያሻህ ትበደርበትና እዳ አስታቅፈኸን ትጠፋለህ፣ ሲያሻህ ደኑን መንጥረህ ትሸጣለህ፣ ታከስላለህ፣ ግፍህ ልክ አጥቶ አስረህ ለአውሪ ታስበላን ነበር…” በማለት ያለፈውን ቁስላቸውን እያዩ ዳግም እንደማይታለሉ እይገለጹለት ነው። በተግባርም እያሳዩት ነው። “ሞኝህን ፈልግ” ሲሉ እየዘመቱበት ነው።
“ብሄር ብሄረሰቦች” የሚለው ስም በትህነግ ሲበጅ ዓላማው በእነሱ ስም ” አያ ጅቦ” ለመጫወት ነበር። በእነሱ ስም “ኢትዮጵያ ትቆራረሳለች” በሚል ለማስፈራራት ነበር። ከሁሉም በላይ ሁሉንም ” ሲሚንቶና አርማታ ሆኜ ያያዝኩዋቸው እኔ ነኝ። እኔ ከሌለሁ ሁሉም ይወላልቃሉ” ለሚለው ድራማ ኢትዮጵያ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቆ ለመዝረፍ ነበር።
በዚም ስሌቱ በዙሪያው ያሰለፋቸው ኢትዮጵያን በየአቅጣጫውና በየዘርፉ ተቀራምተው አልበዋታል። ተቋማቷን ቅርጫ አድርገው ግጠዋታል። የከፍተኛ ስፍራ ሃላፊነታቸውን ተጠቅመው እዳ ገብታ ያመጣቸውን ሳይቀር አግበስብሰውታል። በዚሁ የሌብነት መዋቅር ኢትዮጵያ ላይ ልጓም አልባ ሆነው እንዳሻቸው ናኝተዋል። ሌሎች ዜጎችን ደግሞ በወታደሩ፣ በስለላውና በፖሊስ፣ ከሁሉም በላይ በቤት ለቤት አደረጃጀትና አፈና ጠቅጥቀው በመያዝ እንዳይላውስ፣ እንዳይቃወም፣ እንዳይተነፍስ አድርገውት ኖረዋል።
ሰሞኑንን ክልሎች “ትህነግን ከማጥፋት ውጭ ምንም አማራጭ የለም” ሲሉ በምክንያት እንደሆነ ገልጸዋል። ከስልጣን ተባሮ ራሱን ወደ ትግራይ የሳበው የትህነግ ሃይል፣ አሸባሪ እስኪባል ድረስ መንግስትን “አሃዳዊ” ሲል ይከስ ነበር። የፈረደባቸውን “ብሄር ብሄረሰቦች” ዳግም ከአሃዳዊው ስርዓት አልቅቃቹሃለው በሚል “የፌደራል ሃይሎች ስብስብ” ብሎ ሲርመጠመጥ አክተሮቹ እነ ልደቱ አያሌው፣ የኦፌኮ አመራሮችና በኦሮሞ ስም የሚምሉ አክቲቪስትና የሚዲያ ሾፌሮች በግልጽና በስውር አብረዋቸው ነበሩ።
ሁሉም እንዳይሆን ሆኖ፣ ሕዝብም ገሃዱን እያወቀ ሲሄድ፣ በአቋራጭ መንግስት ለመገልበጥ ታዋቂ ሰዎችን በአደባባይ እስከ መግደልና አመጽ አነሳስቶ በህዝብ ደም ለመቆመርና ስልታን ለመያዝ እዛም እዚህም የተሴረው ሴራ ከሽፏል። አገሪቱን ከዳር እስከዳር የዘረፈውን በመበተን ለማተራመስ፣ ህዝቡን ለማፈናቀል፣ ተማሪዎች እትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይውሉ የዘረፈውን ረጨ። መሳሪያ አቀበለ። ገዳይ ሃይል አስለጥኖ አሰማራ። አገሪቱ በታሪኳ አይታው የማታውቀው የግፍ አይነት ተመዘገበ። ይህ ሁሉ ሲሆንና ለዚህ ክፉ ተግባር ሃብት ሲባክን የትግራይ 2 ሚሊዮን ህዝብ ስንዴ እየተሰፈረለት በረሃብና በችግር መካከል ነበር።
ከላይ በተጠቀሱት ጥቂት ማሳያዎች መሰረት የክልሎች ስጋት ምክንያታዊ ከመሆኑም በላይ “አሃዳዊ ስርዓት ሊተከልብህ ነው” የሚለውን የትህነግ ስብከት ባዶ ጫጫታ እንደነበር ያሳየው “ክተት” ለትህነግ ፖለቲካ ሞት ሆኗል። ሞቱ በየክልሉ እየተማሰለት ነው።
ጨዋታው በጋምቤላ
ጋምቤላ ” ሰጋሁ” ሲል ምክንያት አለው። ወንድ ወንዶቹ ብቻ ተመጠው 500 የሚጠጉ አኝዋኮች ለም መሪታቸውን ለመዝረፍ ሲባል ተረሽነዋል። መሬታቸውን እየነተቀ በኢንቨስትመንት ስም በአንድ ፓኮ ሲጋራ መሸጫ ዋጋ ቸብችቦባቸዋል። የመኖራቸው ሚስጢር የሆነውን ደናቸውን ጭፍጭፎ ሸጦታል። አዛውንትና ሕጻናት ሳይቀሩ ተገሎባቸዋል። እተዘረፉት መሬት ዳር ተኝተው በተስፋ መቁረጥ ሲያለቅሱ ታይቷል። በክልሉ በልማት ስም መሬታቸው መያዣ ተደርጎ በቢሊዮን ብር ተዘርፏል። እናም የጋምቤላ ህዝብ ” ትህነግ ስጋቴ ነው” ቢል ከበቂ በላይ ምክንያት ስላለውና የሚጮሕ የንጽኋን ደም ይህን እውነት እንዲክድ ሰላማያደርገው ነው።
ሶማሌ ክልል
በሶማሌ ክልል የሆነው ተዘርዝሮ አያልቅም። የግፉ መጠን ልክ የለውም። ኢጋዴን ዙሪያ ተከቦ ከተቀረቀረበት በሁዋላ ሰዎች በችጋር እንዲሞቱ ሆኗል። በሶሌሜ ክልል ሰው በዱር አራዊት እንዲበላ ተደርጓል። በጄል ኦጋዴን የተፈጸመው ግፍ በአፍሪቃ ወደር የለውም። የሶማሌ ሲቶች በጅምላ ተደፍረዋል። መድፈር ብቻ ሳይሆን ሃፍረታቸውን አደባባይ እንዲያወጡ እየተደረጉ ተገርፈዋል። ክልሉን የኮንትሮባንድ መናኸሪያ በማድረግ ግጠውታል። ህገወጥ የንግድ መስመር ተክለው ቸርችረዋል። የአገር ሃብት እያጋዙ ዶላር አጥበዋል። የተገደሉትን ቤቱ ይቁጠራቸው። ታዲያ የስማሌ ክልል ትህነግን ፍርቶ እዛው ባለበት እንዲከስም ቢታገል ምን ይገርማል? ከዚህስ በላይ ለስጋቱ ምን ምክንያት ሊያቀርብ ይችላል?
ኦሮሚያ ክልል
ኦሮሞ ” ጠባብ” እየተባለ የአገሪቱን እስር ቤት ሞልቶ ነበር። ኦሮሞ በየቀኑ ጭንቅላቱን እየተመታ ይሞት ነበር። የኦሮሞ እናት በተገደለ ልጇ አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ ተደርጋ ተገርፋለች። እነ ደረራ ከፈኒንን የመሳሳሉ የአገር ዋርካዎች ተደፍተዋል። ትህነግ ኦሮሞን አሸማቆ፣ አስሮ፣ አካል አጉድሎ፣ ገድሎ መግዛት አያረካውም ነበር። ከዚህ ሁሉ በላይ ሃብቱን መዝብሮታል። የኦሮሞን ሃብት አመንዥገው በልተዋል። ደሙን ጠጥተዋል። አጥንቱን ከስክሰውታል። እንደ እብድ ውሻ በአልሞ ተኳሾች በየጉዳባውና አደባባዩ ደፍተውታል። ዛሬ ዞሮ ከነሱ ጋር ከገጠሙት ጥቂት ባንዳዎች ውጪ ትህነግና ኦሮሞ ውላቸው ተቀዷል። ታዲያ ኦሮሞ ” ፈራሁ” ብሎ ትህነግ ላይ ቢነሳ ምን ነቀፌታ ሊቀርበበት ይሆን?
ሲዳም ክልል
ክልል በመሆን ራስን ስለማስተዳደር መጠየቁ ወንጀል ሆኖበት ተገርፏል። ታስሯል። ተስዷል። ሃብቱ በተመሳሳይ ተዘርፎበታል። ከምንም በላይ በማንነት ቀውስ ውስጥ ሆኖ እንዲኖር የተፈረደበት ህዝብ ትህነግን ለመፋለም ቢነሳ ክፋቱ ምን ይሆን? በደቡብ ክልል ሃዲያው አገር ጥሎ ሄዷል። ጋሞው፣ ከንባታው፣ ኮንሶው የትህነግ በትር ያረፈበት ህዝብ ነው። ሌሎችም …
አፋር ክልል
ከኤርትራ አፋር ወዳጆቹ እንዳይገና መሬቱ ተዘርፎ ተቆልፎበታል። በክልሉ ያለውን የጨው ሃብት በጠራራ ተቀምቶ የትህነግ ወራሪዎች ባቋቋሙት ፋብሪካ ውስጥ ጆንያ እንኳን ለመስፋት የተከለከለ ህዝብ ነው። የአፋር ህዝብ ልክ እንደ ሌሎች ሁሉ “ለምን” ያሉትን ልጆቹን ከስሯል። በመት ብቻ ሳይሆን በእስርና በግፋ እንዲሰቃዩ ተደርጓል። አፋር ትህነግን ” እሰጋለሁ” ብሎ ቢዘመት ምክንያት አለው።
ለማመላከት ያህል ይህ ካልኩ አዲስ አበባን ጨምሮ በየከተሞቹ፣ እንዲሁም በአገር ደረጃ ትህነግ የሚባለው አሸባሪ ቡድን የኢትዮጵያችን ስጋት ስለመሆኑ ጥርጥር የለም። ይህ ተቀጥሮና እኩይ ባህሪው አገር ማፍረስ የሆነው ቡድን ህልውናቸውን ዘንግቶ ለማስፈራራት ሲጠቀምባቸው የነበሩ “ብሄር ብሄርሰቦች” ዛሬ አንገቱን ለማነቅ መነሳታቸው ምክንያታዊ ይሆናል። መርዙን ይዞ ካለበት ወደ ሰላማዊ ክላላቸው እንዳይመጣ ባለበት ለማስቆም መረባብረባቸው ትክክልም ነው።
ይህ “ካልበላሁ ጭሬ ልበትን” የሚል በደም የተነከረ ድርጅት የአገራችን አበሳ ነው። ይህ ድርጅት ከውልደቱ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት መርሃ ግብር ነድፎ ሲሰራ እህቶችን ከማምከን ጀምሮ ለነጋሪው የማይሆን ግፍ አከናውኗል። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ምስኪኑን የአማራ ህዝብ በሃሰት ትርክት አሳርዷል። በጅምላ አስጨፍጭፏል። አሁንም ይህንኑ ህዝብ ዳግም ለመጨፍጨፍ በገሃድ ” ሂሳብ እናወራርዳለን” ሲል ዝቶ በሃሺሽ ያበዱ ህጻናትን በገፍ መልምሏል። ከሃሺሹ ጋር ጥላቻን እየጋተ ትውልድ ለማጫረስና መላ አገሪቱን ለማወክ ተነስቷል። ለዚህ ነው ሁሉም ክልል “አያ ጅቦ” ያለው። በረት እየበሳ ግልገል የሚሰርቅ ልማደኛ በጥሩ ወጥመድ ካልተያዘ ወይም ካልተወገደ የበረቱን ቅጥር ሲያጠቃ እንደሚውለው ሁሉ ትህነግም እንደዛው ነው።
ሰለሞን ጎሽሜ ሃይሉ
ጽሁፉ የጸሃፊው ብቻ አቋም ነው
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል።… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ”… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ