የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሀገራት ኢኮኖሚ ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና ለመቀነስ እና ወረርሽኙን ለመግታት እንዲሆን የአለም ባንክ በቅርቡ በተለይ ለታዳጊ ሀገራት የማገገሚያ ድጋፍ ማድረጉ አይዘነጋም።
ከዚህ ውስጥም ኢትዮጵያ ወደ 207 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ ከባንኩ አግኝታለች። ይህንን የአለም ባንክ የኮቪድ 19 ማገገሚያ የድጋፍ ገንዘብ ኢትዮጵያ ለክትባት ግዥ ልታውለው እንቅስቃሴ መጀመሯን ዋዜማ ከመንግስታዊ ምንጮች ስምታለች።
በዚህም መሰረት ጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ከተሰኘው ከታዋቂው የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ የኮቪድ 19 ክትባት ለመግዛት ውል እንደፈፀመችም ተነግሯል።
ኢትዮጵያ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ 19 ክትባትን ለመግዛት የፈፀመችው ውል 3 ሚሊየን ለሚጠጋ የክትባት ጠብታ (Dose) ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ወደ 4 ሚሊየን የሚጠጋ የአስትራ ዜኒካ ክትባትንም በግዥ ለማስገባት አስፈላጊው ሁሉ እንደተፈፀመ ከጤና ሚኒስቴር ምንጮች ስምተናል።
ኢትዮጵያ ኮቫክስ ከተሰኘው የኮቪድ 19 ክትባትን ለታዳጊ ሀገራት ለማዳረስ በተቋቋመው ጥምረት አማካኝነት በዚሁ አመት መጋቢት ወር ላይ ወደ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ጠብታ (Dose) የአስትራ ዜኒካ ክትባት ተረክባ የመጀመሪያ ዙር ክትባት ስታዳርስ መቆየቷ ይታወቃል።
ሁለተኛውን ዙር ክትባት ለማዳረስ የሚያስችል የአስትራ ዜኒካ ክትባት በተለይ 391 ሺህ የአስትራ ዜኒካ ክትባትን ሀገሪቱ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከኮቫክስ ጥምረት ትረከባለች ተብሎም እየተጠበቀ ነው። ክትባቱ ምናልባትም በቀጣዮቹ አምስት ቀናት ኢትዮጵያ እንደሚገባም ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪም ከነሃሴ እስከ መስከረም ወር ድረስ 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ጠብታ የአሰትራ ዜኒካ ክትባትን ለመረከብ እየተዘጋጀች የምትገኘው ኢትዮጵያ ሰሞኑን ከሚገባው ወደ 400 ሺህ ጠብታ ከሚጠጋው ክትባት ጋር በድምሩ ወደ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ጠብታ ክትባትን እንደምታገኝ ይጠበቃል።
ይህ ደግሞ በመጀመሪያው ዙር የአስተራ ዜኒካ ክትባት የከተበቻቸውን እና አዲስ የሚከተቡ ዜጎቿን በሙሉ ሁለተኛ ዙር የአስትራ ዜኒካ ክትባት ለማዳረስ እንደሚያስችላትም ዋዜማ ራዲዮ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ