በፎቶው ላይ የሚታዩት የውሃ፣ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር፣ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ዛዲግ አብርሀ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ፣ ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያም፣ የአገር አቀፍ ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ ናቸው።
በዘንድሮው ምርጫ ብልፅግና ፓርቲ ከ436 መቀመጫዎች ውስጥ 410 ያሸነፈ ሲሆን ለቀጣዩ አምስት አመታትም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ወንበር አግኝቷል።
ለዘመናት የአገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ማዕከል ሆና በቆየችው አዲስ አበባ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ከተማዋ ላይ ባተኮረ መልኩ ፖሊሲዎችን ሲቀርፁና ሲንቀሳቀሱ ይታያሉ።
በዘንድሮው ምርጫ ብዙ ትኩረት በነበረባት አዲስ አበባ የተመዘገቡ መራጮች ቁጥር 1,819,343 ሲሆን ከዚህም ውስጥ 99ኛው በመቶ ድምፅ ሰጥቷል።
አዲስ አበባ ከተማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23 መቀመጫዎች ያሏት ሲሆን ገዢው ፓርቲ ብልፅግና 22 መቀመጫዎችን ሲያሸንፍ በግል የተወዳደሩትና የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት መቀመጫ አግኝተዋል።
ለመሆኑ በቀጣዮቹ አምስት አመታት አዲስ አበባን በፓርላማ የሚወክሏት እነማን ናቸው?
- ምርጫ ክልል 1- ፕ/ር ኢያሱ ኤልያስ
- ምርጫ ክልል 2 ብርሃነ መስቀል ጠና
- ምርጫ ክልል 3 የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ
- ምርጫ ክልል 4 ሙሉ ይርጋ
- ምርጫ ክልል 5 ያስሚ ወህቢ
- ምርጫ ክልል 6 ዶክተር ወንድሙ ተክሌ
- ምርጫ ክልል 7 በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የኢትዮጵያ አቋም ለአረቡ ዓለም በማንጸባረቅ የሚታወቁት መሐመድ ከማል አሊ አል-አሩሲ
- ምርጫ ክልል 8 የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ
- ምርጫ ክልል 10 ዶ/ር ቤተልሄም ላቀው
- ምርጫ ክልል 11 ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያም፣
- ምርጫ ክልል 12 እና 13 ዕጩ ሲሆኑ ዶ/ር ስንታየሁ ወ/ሚካኤል
- ምርጫ ክልል 15 ህይወት ሞሲሳ
- ምርጫ ክልል 16 ሰሃርላ አብዱላሂ
- ምርጫ ክልል 17 የውሃ፣ መስኖ እና ኢንርጂ ሚንስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር፣ ኢንጂነር)፣
- ምርጫ ክልል 18 ዛዲግ አብርሀ
- ምርጫ ክልል 19 ዶ/ር ትዕግስት ውሂብ
- ምርጫ ክልል 20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ
- ምርጫ ክልል 21 እና 22 የብሔራዊ ባንክ ገዢው ዶ/ር ይናገር ደሴ
- ምርጫ ክልል 23 የአገር አቀፍ ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዲላሞ ኦቶሬ
- ምርጫ ክልል 24 ዶ/ር ከይረዲን ተዘራ
- ምርጫ ክልል 25 ዶ/ር ቶፊቅ አብዱላሂ
- ምርጫ ክልል 26 እንዳልካቸው ሌሊሳ
- ምርጫ ክልል 28 በግል ተወዳዳሪነት የቀረቡትና የጠቅላይ ሚኒሰትሩ አማካሪ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ናቸው።
የክልል ምክር ቤቶችን በምንመለከትበት ወቅት ብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባን ምክር ቤት ሁሉንም 138 መቀመጫዎችን አሸንፏል።

ምርጫ 2013 በጨረፍታ
- 37,408,600 መራጮች ተመዝግበዋል ከዚህ ውስጥ 20,317,472 ወንዶችና 17, 091, 128 ሴቶች ናቸው
- 47 ፓርቲዎች 8,209 እጩዎችን አቅርበዋል 125 የግል ተወዳዳሪዎችም
- 634 የምርጫ ክልሎችና 49, 407 የምርጫ ጣቢያዎች
- 52,700 የምርጫ አስፈጻሚዎች፤ በእያንዳንዱ የምርጫ ጣቢያ 5 አስፈጻሚና 1 የኮቪድ-19 ቁጥጥር ባለሙያ
- ሰኔ 14/2013 ዓ.ም በተደረገው ምርጫ ለ445 የፓርላማ መቀመጫዎች ድምጽ ተሰጥቷል
- ጳጉሜ 01/2013 ደግሞ ለቀሪዎቹ 64 ወንበሮች ድምጽ ይሰጣል
ምስጋና ፎቶና ዘገባ ቢቢሲ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program at the Center… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን ሊግ ፍጻሜ ከቶትንሃም… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል