ጁንታው ወጣቶቻችን በስናይፐር ገድሎብናል፤ ዘርፎናል፤ ከፋፍሎናልና ይህንን ተግባሩን እንዲደግም አንፈቅድም ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡

በመስቀል አደባባይ እየተካሄደ ባለው ሰልፍ ንግግራቸውን ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ ጁንታው በመቶ ሰዎች ወንበር ላይ ብቻውን ሲቀመጥ ነበር ያሉ ሲሆን÷ አሁን የሁሉም ብሄር ብሄረሰብ ወንበር እንዲሆን መደረጉን ገልጸዋል፡፡ አሸባሪው ከተቀበረበት እንዳይነሳ አድረገን እንቀብረዋለን ሲሉም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡
በአንድ በኩል ልማት በሌላ በኩል ጁናታውን መመከት ላይ ልታተኩሩ ይገባል ያሉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ ኢትዮጵያዊያነት ደማችን ውስጥ ያለ መሆኑን በዚህ መድረክ አይተነዋል ብለዋል፡፡ ለጁንታ የምትላላኩ ሀይሎች ኢትዮጵያ እንደፈላጋችሁ ማድረግ አትችሉም፣አይሳካላችሁም ሲሉም ነው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት፡፡
አሸባሪው የህውሃት ቡድን በጠምንጃ አፈሙዝ የኢትዮጵያን ህዝብ ለመጨቆንና መልሶ ኢትዮጵያን ለመግዛት እየታተረ ቢሆንም በኢትዮጵያዊን ጀግኖች አይሳካለትም፣
- አሸባሪ ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማፍረስ 40 ዓመት ስርቶዋል፣ ነገር ግን ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን የኢትዮጵያ ጀግኖችን አያውቅም፣
- የኢትዮጵያ ጀግኖች ከጫፍ እስከጫፍ ተሰልፈው አሸባሪውን የህወሓት ቡድን ጠራርገን ወደ ቦታው ለመመለስ የሚያስፈልገውን ሁሉ መስዋትነት እንከፍላለን፣
- ህውሓት ዳግም በከፋፍለህ ግዛ ፈሊጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ሊጫን አይችልም፤ የኢትዮጵያን ጠላቶች ፍላጎት ኢትዮጵያ ላይ አይፈፅምም፤ ዳግም ኢትዮጵያዊነትን ዝቅ አያደርግም፣
- ህውሃት ኢትዮጵያዊነት የደከመ መስሎታል ኢትዮጵያዊነት ግን እጅግ የበረታበት ወቅት ነው፤ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ደማችን ውስጥ ነው ያለው፣
- ኢትዮጵያውያን የመረጡት ፣ የኢትዮጵያን ልማት የሚያፋጥን፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ምድር ላይ ተምሳሌት የሚያደርግ መንግስት መስከረም መባቻ ላይ ይቋቋማል፣
- አንዳንዶች ጃጅተው አርጅተው መቆም አቅቷቸው የተላላኪነት ፍላጎታቸውን ላማሳካት ሽግግር ይመኛሉ፤ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው መንገድ የሚመጥናቸውንና ፍላጎታቸውን የሚያሳካላቸውን መንግስት መርጠዋል፣
- ከውስጥም ከውጪም ለአሸባሪው ህውሃት የሚላላኩ ሀይሎች ከዚህ ስፍራ ግልፅ መልዕክት እናስተላልፍላችዋለን በኢትዮጵያ ላይ ምንም ማድረግ አትችሉም፣
ኢዜአ
ኢትዮጵያውያን በድምፃቸው ማን ሊያስተዳድራቸው እንደሚገባ በመወሰናቸው ማንም የሚያስቀምጥላቸውን አሻንጉሊት መንግስት አይቀበሉም – ከንቲባ አዳነች አበቤ

ኢትዮጵያውያን ማን ሊያስተዳድራቸው እንደሚገባ በቅርቡ ባካሄዱት ምርጫ በድምፃቸው በመወሰናቸው፣ ማንም የውጭ ሃይል የሚያስቀምጥልን አሻንጉሊት መንግስት ሊኖር አይችልም ሲሉ ምክትል ከንቲባ አዳዳነች አበቤ አስገነዘቡ።
ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን ነዋሪዎች አሸባሪው የትህነግ ቡድን በማውገዝ የሀገር አንድነትን ለመጠበቅ የዘመተውን የመከላከያ ሃይል በመደገፍ ባካሄዱት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ባደረጉት ንግግር መከላከያ ሰራዊታችንና መላው የፀጥታ ሃይላችን የሀገራችንን ሉዓላዊነትና ክብር ለመጠበቅ እየከፈሉ ያሉት ተጋድሎ እንዲጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት እያሰሙ ያሉት ድምጽ ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ክብርና ነፃነት የሚሰማ የሚሊዮኖች ድምፅ በመሆኑ ሊከበር እንደሚገባ ምክትል ከንቲባዋ ተናግረዋል።
ይህ የምናሰማው የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የጀግንነት ድምጽ አገር አፍራሽና የእናት ጡት ነካሽ የሆነው ከሃዲው ጁንታ አገራችንን ለማፍረስ የሚያደርገውን ሙከራ በኢትዮጵያ ላይ የሚቃጣውን ማንኛውም ፀረ ኢትዮጵያ ጣልቃ ገብነት በጥብቅ ለማውገዝ የሚሰማ የሚሊዮኖች ድምፅ መሆኑንም አመልክተዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም አማራጭ ቅድሚያ በመስጠት ሰፊና ትዕግስት አስጨራሽ ትግል ሲያካሂድ መቆየቱን ያስታወሱት ምክትል ከንቲባ አዳነች አበቤ÷ በመላው ህዝብ ትግል ከስልጣን የተወገደውን አሸባሪውን የህወሃት ጁንታ ከሞተበት ለማንሳት የሚጥሩ የውጭ ጣልቃ ገቦች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ ጠይቀዋል።