የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር “ትህነግ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!” እንደሆነ በለውጡ ማግስት በሰፊ ትንተና ያስረዱትና ስጋታቸውን ያሰፈሩት ብሮንዊን ብሩተን፣ አሁን ያለውን ሁኔታ ሲገልጹ የጀመሩት “ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ኢትዮጵያን ከፍተኛ በሚባል ደረጃ ረግጦ ሲመራ የቆየው ትህነግ” በሚል ነው። ይኸው ድርጅት “አሁን ላይ ለትግራይ ክልል የሚደረጉ የሰብአዊ ድጋፍ ስራዎችን በማደናቀፍ ድጋፍ እንዳይደርስ እያደረገ ነው” ሲሉ ተጠያቂ የሚያደርጉት የአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክትር ብሮንዊን ብሩተን ናቸው።
ብሮንዊን ብሩተን የስሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ እንዳይገባ መንገድ መዘጋቱን አስመልክቶ ከቢቢሲ ዜና ክፍለ ጊዜ ጋር ባደረጉት ቆይታ “በክልሉ አሁን ላይ የሰብአዊ ድጋፍ መስተጓጎል እንዲገጥም ያደረገው አሸባሪው ህወሓት ነው” ሲሉ ድርጅቱን በስም “አሸባሪ” ብለው ተጠያቂ አድርገዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጠል ተኩስ አቁም ባለመቀበል አሸባሪው ድርጅት ውጊያ ላይ እንደሚገኝ አስረግጠው ተናግረዋል። ለትግራይ ክልል የሚደረገውን የሰብዓዊ ድጋፍ እንዳይጓጓዝ እያደናቀፈ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
ምክትል ዳይሬክተሯ ዓለም ጆሮ የነፈገውን ጉዳይም አንስተዋል። “አጎራባች አማራና አፋር ክልሎች ላይ ድርጅቱ ባደረገው ጥቃት ዜጎች ተፈናቅለዋል” ሲሉ ከሰዋል። ትህነግ ” ከአማራ ጋር የማወራርደው ሂሳብ አለ” ሲል በለኮሰው ጦርነት ከ200 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለዋል። በአፋር በኩል የጅቡቲን መንገድ ለመዝጋት አቅዶ ባደረገው ወረራ ከ100 ሺህ ሰው በላይ ሰላማዊ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው የየክልሉ ሃላፊዎች ማስታወቃቸው ይታወሳል። ብሩተን በቁጥር ባይገልጹም ትህነግ የተኩስ አቁም ከተባለ በሁዋላ እያደረሰ ያለውን ጥፋት በይፋ በመቃወም ግንባር ቀደም ሆነዋል

Ethiopia and Eritrea Have a Common Enemy
Abiy Ahmed and Isaias Afwerki are racing toward peace because they both face the same threat: hard-liners in the Tigrayan People’s Liberation Front.
ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ ከማድረጋቸው አስቀድመው ” የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ እንዳይተላለፍ ዘጋ የምትሉ እስኪ አስረዱኝ” ሲሉ የግርምት ጥያቄ በማንሳት በቲውተር ገጻቸው አኑረው ነበር። በአትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ብሮንዊን ብሩቶን ” ዓቢይ አሕመድ የህወሓትን የበላይነት ማሳሳቱን ቀጥሎበታል። እንደ ሳሞራና ጌታቸው ያሉትን አደገኛና ጨካኝ ሰዎችን ከሥራ እንዲለቁ በማድረግ የሚደረገው ተሃድሶ በቀላሉ ሰዎቹ እንዲተኑ አያደርጋቸውም። ከዚህ ሌላ 95በመቶ ትግሬ የሆኑትን ጄኔራሎች በሙሉ ማባረር ለዓቢይ አዋጭ አይደለም። ስለዚህ የሥልጣኑን መንበር ለማጠናከር አደገኛና ጨካኝ የተባሉትን ማባረር፤ አብረውት ለመሥራት የሚፈልጉትን በማስተባበር ዓመታትን መዝለቅ የግድ ይሆንበታል” ሲሉ “ህወሓት፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የጋራ ጠላት!” በሚል ርዕስ ስር ባቀረቡት ጽሁፋቸው አስቀድመው ስጋታቸውን አኑረው ነበር። ሙሉውን ለምንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
በቃለ ምልልሳቸው ሽብርተኛው ህወሃት ላለፉት 30 አመታት ገደማ አገሪቷን በአምባገነንነት መግዛቱን ገልጸው፤ የለውጡ ሂደት ከመጣ በኋላ ህወሃት የትግራይ ክልል በማስተዳደር የጦርነት ቅስቀሳ ሲያደርግ ቆይቶ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በመከላከያ ሠራዊቱ ላይ ጥቃት መሰንዘሩን አብራርተዋል። በተጨማሪም ሽብርተኛው ቡድን ጥቃቱን በማጠናከር በድጋሚ ወደ ስልጣን ለመምጣት ጦርነት መጀመሩን አመልክተው የፌደራል መንግስትም ይህንን ተከትሎ ወደ ሕግ ማስከበር ዘመቻ መግባቱን መግለፃቸውን አመልክተዋል። በአሸባሪው ቡድን አገዛዝ ምክንያት ከሁለት አስርታት በላይ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ጭቆና፣ በፍርሃትና በማንነታቸው ጥቃት ውስጥ እንደነበሩ ምክትል ዳይሬክተሯ አመልክተዋል።
- Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack… I am trying not to be an alarmist, but there are a lot of things… Read more: Israel’s Peace With Egypt Is Starting to Crack
- U.S. Considers Somaliland Recognition in Exchange for Strategic Military Base Near BerberaAccording Financial Times a U.S. official, discussions have begun regarding a potential deal that would involve the… Read more: U.S. Considers Somaliland Recognition in Exchange for Strategic Military Base Near Berbera
- Brigade Nhamedu’s forthcoming Addis Ababa ConferenceBy Beyene Gerezgher The Ethiopia branch of Brigade Nhamedu (also known as the Blue Revolution Movement)… Read more: Brigade Nhamedu’s forthcoming Addis Ababa Conference
- Eritrea Is the North Korea of Africa: America Must ActThe U.S. Department of the Treasury should also tighten sanctions on Eritrean banks, financial institutions, and… Read more: Eritrea Is the North Korea of Africa: America Must Act
- The Somaliland Alternative: Securing Future Global Shipping Amid the Houthi ThreatThe Port of Berbera can be an alternative logistical hub and military staging ground to high-risk… Read more: The Somaliland Alternative: Securing Future Global Shipping Amid the Houthi Threat