ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ ደብዳቤ በማስመሰልና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ በማዘጋጀት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ። ባሕር ዳር:ሐምሌ 25/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሐሰተኛ ማስረጃ በማቅረብና ጉቦ በመስጠት በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረ ፌሮ ብረት ክምችት ለማስለቀቅ የሞከሩ ተጠርጣሪዎችን መያዙን የፌዴራል ፖሊስ ገልጿል።
በተጠርጣሪዎቹ ለማስለቀቅ የተሞከረው በቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ አካባቢ በአንድ መጋዝን ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለና በምርመራ ሂደት ላይ ያለ የፌሮ ብረት ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የተፃፈ በማስመሰል “ሕጋዊነቱ ስለተረጋገጠ በቦታው የሚገኘው የፖሊስ ጥበቃ ተነስቶላቸው ወደ ፈለጉበት ማንቀሳቀስ እንዲችሉ ፈቅደናል” የሚል ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅተው በመያዝና ጉቦ ለመስጠት የሚውል ገንዘብ በቼክ አዘጋጅተው ብረቱን በአምስት ተሽከርካሪ ጭነው ሊወጡ ሲሉ ሦስት ተጠርጣሪዎች በኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስና በፋይናንስ ኢንተለጀንስ ጠንካራ ክትትል ሊያዙ ችለዋል።

ባለፈው ሳምንት የተያዘው ብረት ባለቤት ነኝ ከሚል ተክላይ ከሚባልና አሜሪካን ሀገር ነዋሪ ነው ተብሎ ከሚነገረው ግለሰብ ጋር ሦስቱ ተጠርጣሪዎች የጥቅም ትስስር በመፍጠር በኤግዚቢትነት ተይዞ በምርመራ ሂደት ላይ ያለውን የፌሮ ብረት በጥበቃ ላይ ላሉት የፖሊስ አባላትና አመራሮች 500 ሺህ ብር ጉቦ ለመስጠት በአቢሲኒያ ባንክ አዲስ አካውንት ከፈተው ያስገቡ መሆኑም ነው የተገለፀው።
በተመሳሳይ ለሌሎች የጸጥታ አካላት 400 ሺህ ብር በባንክ እና የ25 ሚሊዮን ብር ቼክ አዘጋጅተው ብረቱ እንደሚለቀቅ ከተስማሙ በኋላ የፖሊስና የጸጥታ አካላቱ ጉዳዩን ሚስጥራዊ በሆነ መንገድ ለበላይ ኀላፊ በማሳወቅ ሂደቱ እንዲቀጥል በመደረጉ፤ ብረቱን በአራት ሲኖትራክ እና በአንድ ክሬን ለመጫን ተስማምተው በሁለት ሲኖትራክ እንደተጫነ ባንክ የገባው ብር እና ቼኩ፣ እንዲሁም የተፃፈው ሐሰተኛ ደብዳቤ እና ሦስቱ ተጣርጣሪዎች ከተዘጋጁት ተሽከርካሪዎች ጋር ከነአሽከርካሪዎቻቸው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል።
ተጠርጣሪዎቹ ለጸጥታ አካላት በርካታ ገንዘብ ሰጥተው በማማለል ለሕገ-ወጥ ድርጊት ፖሊስ ተባባሪ እንዲሆን ያደረጉትን ጥረት በማክሸፍና ለሕግና ለመንግሥት ፍፁም ታማኝ በመሆን ወንጀሉ ለሕግ እንዲቀርብ በማድረግ የአሸባሪው ጁንታን እኩይ ሴራ ማክሸፍ መቻላቸውን ፌዴራል ፖሊስ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ኅብረተሰቡ አሁንም በዚህ አይነት የወንጀል ተግባር ላይ ለመሳተፍ የሚጥሩ የአሸባሪው ጁንታና ከጁንታው ጋር ግንኙነት ፈጥረው ሀገሪቱ ላይ የሚያሴሩ ባንዳ ግለሰቦችን እየጠቆመ አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግ ፌዴራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።
ምንጭ አዲስ አበባ ዜና አገልግሎት
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the repercussions of the aggression on Gaza, developments in Syria, and the ongoing tensions with Iran, its Foreign Minister Gideon Sa’ar found… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት የነበረን የባህር በር ሳታገኝ መቅረቷ ልብ ያደማል። የፖለቲካ ሳይንስን በቅጡ የሚገነዘቡ ምሁራን የራስ ዱሜራን ጉዳይ ወደ አደባባይ ይዘውት ቢመጡ እንዴት… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት እየነሳቸው ያሉ ይመስላል፡፡ በጦርነቱ ወቅት ሲነገሩ የነበሩ ቁልፍ ሚስጢሮችን ሲከላከሉና ሲያመክኑ ቆይተው አሁን ላይ ራሳቸው ይፋ እያደረጉ ነው።ከትግራይ ጊዜያዊ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ ወይሻ ሙሽራነቱን አቋርጦ ነብስ ታድጓል፡፡ ” ለሆስፒታሉ ብቻ ሳይሆን ለአከባቢውም ብቸኛ ስፔሻሊስት ስለነበርኩ ሌላ አማራጭ አልነበረኝም ” – የራሱን… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ አጣጣሉት። ፋኖ አስራ ሶስት አመራሮችን መርጦ ድርጅት መመሰረቱ ተገለጸ። መሪ አለመሰየሙ እያነጋገረ ነው። በቅርቡ የትምህርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚንስትር ደኤታ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ