አሁን የገባንበትን ጦርነት ማሸነፍ የሚቻለው አንድነታችን በማጠናከርና ጦርነቱን እንደ ጠላቶቻችን ህዝባዊ በማድረግ ነው። በአሁኑ ጊዜ የተለያየ አደረጃጀት በፍጠር የህዝባችን አንድነት ለመከፋፈል የምትሞክሩ ወንድሞቻችን ከድርጊታችሁ ታቀቡ!
— Agegnehu Teshager G. (@AgegnehuT) August 13, 2021የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር የተለያየ አደረጃጀት በመፍጠር የሕዝቡን አንድነት ለመከፋፈል የሚሞክሩ አካላትን አስተነቀቁ። አዲስ አደረጃጀት እንዳለ ቀደም ሲል ህግ ጥሰው ሃይል አደራጅተው የነበሩት ዘመነ ጣሴና ማስረሻ ሰጤ አስታውቀዋል። ባለሃብቶችና ከጦርነት ሙያ ጋር አግባብነት የሌላቸው አካላት ከጦር ሜዳ አካባቢ እንዲገለሉ ቢደረግ የሚል ሃሳብም እየተነሳ ነው።
“አሁን የገባንበትን ጦርነት ማሸነፍ የሚቻለው አንድነታችን በማጠናከርና ጦርነቱን እንደ ጠላቶቻችን ህዝባዊ በማድረግ ነው። በአሁኑ ጊዜ የተለያየ አደረጃጀት በመፍጠር የህዝባችንን አንድነት ለመከፋፈል የምትሞክሩ ወንድሞቻችን ከድርጊታችሁ ታቀቡ!” ሲሉ እጅግ ትህትና በተመላበት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል


” … መዋቅሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ በሁሉም ወረዳዎች የሚመሰረት መሆኑን አውቃችሁ በየወረዳው የተሻሉ እና የበቁ ልጆችን እያዘጋጃችሁ እንድትጠብቁን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በመስራች ጉባኤው የተገኙ የየወረዳ ተወካዮች በሁሉም ወረዳዎች የሚፈጠረውን አደረጃጀት እንዲመሩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል። ወጣቶች የየወረዳ አደራጆችን በቅንነት እንድትተባበሩ እና ራሳችንን ለማስከበር ህዝባችንን ከጥቃት ለመከላከል ለምናደርገው ሁሉን ዓቀፍ ተጋድሎ ራሳችሁን አዘጋጅታችሁ እንድትጠብቁን እና ጥሪ ስናደርግላችሁ እንድትከቱ ፥ ይፋ በምናደርጋቸው ቦታወች ያለምንም ማመንታት እንድትገኙ በታላቅ አደራ ጥሪ እናስተላልፋለን” ሲሉ መግለጫ የአደረጃጀቱ መሪ መሆናቸውን ያስታወቁት ዘመነ ካሴና ማስረሻ ሰጠኝ በገሃድ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ ከውጭ አገር የትህነግ አመራሮች ጋር ግንኙነት ባላቸው፣ በሚታወቁ የሚዲያ ባለቤቶች፣ በሚታወቁ ሚዲያዎችና በሚታወቁ “አክቲቪስት ነን” ባይ የትህነግ ካድሬዎች፣ እንዲሁም የሽግግር መንግስት አዘጋጅተው ከወዲያ ወዲህ የሚሉ ወገኖች በጥምር የሚመሩት መዋቅር በርካቶችን አስቆጥቷል።
አንዳንድ አስተአየት ሰጪዎች እንደሚሉት የክተት ጥሪውን ተከትሎ አንዳንድ ባለሃብቶች በሬክላምና በጭብጨባ እያሳዩ ያሉት እንቅስቃሴ በጥሞና መመርመር አለበት። በተለይም ከትህነግ ጋር ወዳጅ የነበሩ ባለሃብቶች ወደ ግንባር ባይሄዱና ባሉበት ሆነው እርዳታ እንዲያደርጉ ቢደረግ የተሻለ እንደሆነ መክረዋል። ምክንያታቸውን ሲያስረዱም ከነዘመነ ካሴ ጋር ቁርኝት ያላቸው “ዱርዬ ባለሃብቶች” በጥርጣሬ ሊታዩ እንደሚገባ አመልክተዋል። አያይዘውም መንግስት ባለበት አገር እንዲህ ያለ ወቅት ላይ የመንግስትን ህልውና የሚጋፋና ክልሉን መሪ አልባ የማድረግ ተልዕኮ ይዘው በይፋ የሚነቀሳቀሱትን በየትናውም መመዘኛ መታገስ ውጤቱ አገንገት አስደፊ ስለሚሆን መላ ሊባሉ እንደሚገባ ተመልክቷሎ።
ተያያዥነት ያለውን ከስር ያለውን ዜና ያንብቡ።