የአሜሪካው ስፔስ ኤጀንሲ ናሳ እና ሀዋይ ዩኒቨርሲቲ በትብብር በሰሩት ጥናት እንዳመላከቱት ጨረቃ በራሷ ዛቢያ ላይ የምታደርገው ተፈጥሯዊ ዑደት መዛባትና የአየር ንብረት ለውጥ በፈረንጆቹ 2030 ሊከሰት ለሚችል የጎርፍ አደጋ ስጋት መንስኤ ሊሆን ይችላል ተባለ፡፡
አሜሪካ ላይ ትኩረቱን አድርጎ በተሰራው በዚህ ጥናትም እንደተመላከተው÷ከፍተኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ የሚከሰተው በፈረንጆቹ 2030 ሲሆን ክስተቱ ለ አስር ዓመታትም ሊቀጥል እንደሚችል ተተንብይዋል፡፡
የአሜሪካ የባህር እና የከባቢ አየር አስተዳደር እንዳስታወቀው በፈረንጆቹ 2019 በአሜሪካ 600 የሚደርስ የጎርፍ መጥለቅለቅ ሲከሰት ይህ አሃዝ ግን እስከ ፈረንጆቹ 2030 ድረስ በብዙ እጥፍ ሊጨምር ይችላል ነው የተባለው፡፡
ፊል ቶምሰን የተባለው የሃዋይ ዩኒቨርሲቲ ረዳት ፕሮፌሰር እና ዋና የጥናቱ መሪ እንዳመላከተው÷ በጨረቃ ዑደት መዛባት ምክንያት የሚከሰተው ይህ የጎርፍ አደጋ በሀሪኬን ምክንያት ከሚደርሰው ይልቅ በመጠኑ ዝቅተኛ የሆነ ውድመት ሊያስከትል ይችላል፡፡
እንደ ጥናቱ በአሜሪካ በወር ከ 10 እስከ 15 ያህል ጊዜ የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ከተከሰተ ተፅዕኖው በንግድ ተቋማት እና በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች (ፓርኪንጎች) ላይ ስለሚበረታ በርካቶች ከስራቸው ሊስተጓጎሉ እንደሚችሉ ተመልክቷል፡፡
የጎርፍ አደጋው ውሃማ በሆኑ የአሜሪካ ዳርቻዎች እንዲሁም እንደ ሃዋይ፣ ጉዋም፣ እና አላስካ ባሉ አካባቢዎች ሊበረታ እንደሚችልም ነው የተገለፀው፡፡
ኢ-መደበኛ የጨረቃ ዑደት አዲስ ክስተት እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በፈረንጆቹ 1728 ተከስቶ እንደነበረም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት፡፡
ምንጭ÷አልጀዚራ
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ ይጠቅማት… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው”… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can StopCameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa… Read more: The Wars We Still Can Stop