የዓለም መንግስታት ስብሰባ ላይ ለመገነት ኒውዮርክ ያመሩት የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከበርካታ አገራት ከፍተኛ ባለስልጣናትና ከተባበሩት መንግስታት የተለያዩ ሃላፊዎች ጋር መምከራቸው እየተዘገበ ነው። አቶ ደመቀ ካገኟቸው ከፍተኛ ሰዎች መካከል አንዱ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም UNDP ዋና አስተዳዳሪም አንዱ ናቸው።
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ዋና አስተዳዳሪ ሚስተር አችም ስቴይነር አቶ ደመቀን አግኝተው ከተወያዩ በሁዋላ የሰጡት ምስክርነት ግን የተለየ ስሜትን ፈጥሯል። በተለይም የትህነግ ደጋፊዎችና አመራሮች በገሃድ ነቅፈዋል። የትህነግ አመራሮችና ደጋፊዎች ብቻ ሳይሆን እንደ ኖርዌጂያኑ ተሮድ ቮል ሼትል አይነቱ የትህነግ ስራ አስፈጻሚ በገሃድ በቲውተር ገጻቸው አውግዘዋል።

“የኢትዮጵያ ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንንን በደስታ ተቀብያለሁ” ያሉት የUNDP ዋና አስተዳዳሪ፣ ” በጋራ ቀዳሚ ጉዳዬቻችን ዙሪያ ተወያይተናል።በምርጫዎች (elections) የሰላም ግንባታ እና የወደፊት የልማት ጎዳና ላይ ላለን የረዥም ጊዜ አጋርነት እና ቁርጠኝነት አድናቆቴን ገልጫለሁ” ሲሉ ስሜታቸው ገልጸዋል።
አስተዳዳሪው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላካሄደው ምርጫ እውቅና በመስጠት ላስተላለፉት መልዕክት ” ምን ሲባል፣ እንዴት ተደርጎ የተባበሩት መንግስታት ለኢትዮጵያ ምርጫ እውቅና ይሰጣል” በሚል ተቃውሞ ለማሰማት ቅድሚያ የሆኑት የትህነግ ሰዎች ቢሆንም፣ በመናበብ የሚሰሩ እንደሆነ የሚነገርላቸው በተመሳሳይ ተቃውሞ አሰምተዋል።
ዋና አስተዳዳሪው በንግግራቸው የኢትዮጵያን ሃገር አቀፍ ምርጫ እውቅና መስጠታቸው ፖለቲካዊ ሽንፈት የሆነባቸው አካላት፣ ዋና አስተዳዳሪው ” ኢትዮጵያ ለሰላም ግንባታ ሂደትና ለልማት ያላትን ቁርጠኝነት አደንቃለሁ” መለታቸው ደግሞ ምን አልባትም የነገሮች መላካቸውን መቀየር ምልክት ሊሆን እንደሚችል በማሰብ ቅሬታውን ከፍ እንዳደረገው በተቃራኒ ወገን ያሉ ጽፈዋል።