የኢብኮ ማህበራዊ ገጽ(ፌስቡክ) የተጠለፈ በመሆኑ በገጹ የሚተላለፉ መረጃዎች የኢብኮ አይደሉምየአትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ማህበራዊ ሚዲያ(ፌስቡክ ገጽ) የተጠለፈ(‘hack’ የተደረገ) በመሆኑ በገጹ የሚተላለፉ ማንኛውም መረጃዎች ትክክል አይደሉም
Ethiopian News Agency ኢብኮጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በትግራይ ሕዝብ ላይ የደረሰው ግፍና መከራ በዓለም ሕዝብ ፊት አዋርዶናል” ሲል ለ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስታወቃቸውን ነው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ያሰራጨው የሃሰት ዜና።

የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ሰሪቪስ የፌስ ቡክ ገጽ ሃክ ተደርጎ በማህበራዊ ገጾች በፍጥነት እየዲበተን የተደረገው ዜና ፍጹም ሃሰትና ያልተባለ፣ እንዲሁም ሕዝብ በመረጠው መንግስት ለመተዳደር ሲጠብቀው የነበረውን ቀን እያከበረ ባለበት ወቅት ሆን ተብሎ ሃሳብ ለማስቀየር መሆኑ ተጠቋሟል።
“የኢትዮጵያ አንድነት ምሶሶ የሆነው የአማራ ሕዝብ የዚህ እዳ ከፋይ እየሆነ ነው” በሚል በዜናው ውስጥ የተካተተው ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎን ከትህነግ ጋር ግንኙነት እንደፈጠሩ ለማስመሰልና ልዩነትን ለመዝራት እንደሆነ ተመልክቷል።
ዜናው እንደተሰራጨ በርካታ ዜጎች ” ሃሰት፣ ፌክ” ሲሉ ዜናውን በማሰራጨት መመከታቸው ታይቷል። በማህበራዊ ገጾች ዜናው እንደተሰራጨ “ፌክ” በሚል በስፋት ዜናውን የማምከን ርብርብ ተደርጓል።
በዜናው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ” … የህወሃት ድርጅት ጋር ዋልይደር ሳንል ድርድር እንድጀምራለን። ዝርዝሩ ለሕዝብ በቅርቡ ይገለጻል” ያለው የፈጠራ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ህዝብ የሰየመው ፓርላማ አባላቱ ሙሉ በሙሉ ጆሯቸው ተድፍኖ ወይም ተኝተው ስለመሆኑ አላብራራም።
ዕርቅና የሰላም ሃሳብ የሚደገፍ ቢሆንም፣ የትግራይ ሕዝብ ወገን የሆነ ህዝብ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር ባይኖርም፣ ለጊዜው የኢትዮጵያን መከላከያ ካረደና በግፍ ካሰቃየ ከሃዲ ትህነግ ጋር ዕርቅ እንደማይታሰብ ሕዝብ በስፋት በተደጋጋሚ እያስታወቀ ነው። ሕዝብ ሰላምና ዕርቅ ሰፍኖ መኖር እንደሚፈልግ በሚገልጽበት መድረኮች ሰፊው የትግራይም ሆነ የተቀራው የአገሪቱ ክፍል ነዋሪዎች በሰላም እንዲኖሩ የትህነግ መሰሪ ፖለቲካና የህቡዕ አደረጃጀት ሊወገድ እንደሚገባው ምሁራንም ያምናሉ።