ባለፈው አርብ የጸደቀው የውሳኔ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አባል አገሮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የበለጠ እንዲተጉ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
‘Countering disinformation and promotion and protection of human rights and fundamental freedoms’ የሚል ርዕስ ያለው ይህ የውሳኔ ሀሳብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት በሰብዐዊ መብቶችና መሰረታዊ በሆኑ ነጻነቶች እንዲሁም ዘላቂ በሆኑ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals) ላይ እያስከተለ ያለውን አሉታዊ ሚና አጽኖት ሰጥቷል።
ሀሰተኛ መረጃ ለግጭት፣ ለመድሎ፣ ለሰብዐዊ ቀውሶች መከሰትና ለአለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የውሳኔ ሀሳቡ እውቅና ሰጥቷል። በተጨማሪም የውሳኔ ሀሳቡ የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በማናቸው የመገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ጥላቻንና ግጭትን የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎችን አውግዟል።
የውሳኔ ሀሳቡ አገሮች ለሰላምና ለትብብር ጠንቅ የሆነውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጻረር መልኩ የመዋጋት ሀላፊነት እንዳለባቸውም ያሳሰበ ሲሆን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የፖሊሲ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ያሰመረ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽነትን በማስፈንና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚያበረታቱ አሰራሮችን በመቀነስ የራሳቸውን በጎ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርቧል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመዋጋት ረገድ ቀዳሚ ሚና እንዲጫዎቱም ሀላፊነት ሰጥቷል።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ በፓኪስታን አርቃቂነትና በበርካታ አገሮች ድጋፍ የቀረበ ሲሆን ለወራት ውይይት ሲደረግበት ነበር።
EthiopiaCheck Updates
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ
- UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan AuthorityMore stories Ukraine will lose more than $1 trillion due to the… Read more: UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan Authority
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም” ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነውእድሜው ለጋ ሀሳቡ ትልቅ ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን አሻግሮ ማየት ችሏል።… Read more: ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው