“ከድል በኋላ ያሉ ድኅረ ድል መዛነፎችን ማረም እና የጋራ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ ነው” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ
የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው፡፡
የምክክር መድረኩ ዓላማ የክልሉን አመራር ለቀጣይ ተልዕኮ ማዘጋጀት እና ማብቃት ነው ተብሏል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የገጠማትን የሕልውና ጦርነት በተሟላ ድል የምታጠናቅቀው አፍራሽ አስተሳሰቦች ፈጽመው ሲከስሙ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የገጠማት ጦርነት ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትርጉም ያለው ዘርፈ ብዙ ነበር ያሉት አቶ ተመሥገን አንጸባራቂ ድሎች ተመዝግበዋል፤ ድሉም የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ድል ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል ወረራ ሲፈጽም የሀገሪቱን መውጫ እና መግቢያ በሮች በመቆጣጠር ኅልውናዋን መገዳደርና ወደሚፈልገው ድርድር መምጣት፣ በሱዳን በኩል መውጫ ኮሪደር ማስከፈት፣ የአማራን ሕዝብ አንገት ማስደፋት እና ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ያሉት አቶ ተመሥገን የሽብር ቡድኑ በሁሉም ዘርፎች አልተሳካለትም ብለዋል፡፡
ከድል በኋላ ባሉ የድኅረ ድል መዛነፎችን ማረም እና የጋራ መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተመሥገን በችግሮች ላይ ሰፊ፣ ቀና እና በተግባር የተደገፈ ውይይት ከተደረገ መፍትሔዎቹ ቀላል ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በጦርነቱ የደረሰው ጉዳት ቀላል ባለመሆኑ የጋራ ትብብር እና ሕዝባዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፤ የምክክር መድረኩም በዚህ ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
ክልሉ ለወራት በዘለቀው ወረራ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ መዛነፎች ተፈጥረዋል ያሉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከዚህ ዘርፈ ብዙ ፈተና በፍጥነት ለመውጣት ወጥ አቋም ያለው፣ በቆራጥነት የሚሠራ እና ሕዝብን የሚያገለግል የአመራር ሥርዓት መዘርጋት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ከችግሮቻችን በፍጥነት ለመውጣት ተከታታይ ምክክር፣ ውይይት እና ስልጠና ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የጋራ አቋም፣ ወጥ እሳቤ እና ተቀራራቢ አፈፃፀም አሁን ካለው አመራር የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኘው የክልሉ ሕዝብ ሥራ አስፈፃሚ ከሕዝቡ ጋር መነጋገር፣ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እና በተግባር የተገለጸ ችግር ፈች እርምጃ ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ይህንን ለማድረግ ደግሞ በቂ ጊዜ ስለማይኖር ቀን እና ሌሊት ያለረፍት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ርእሰ መሥተዳድሩ መሰረታዊ የሆኑ የክልሉ ሕዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ቁርጠኛ አቋም መውሰድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች የቀጣይ ተልዕኮ በዚህ “የጊዜ የለንም መንፈስ” የተቃኘ ሆኖ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው፡፡ ምክክሩም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥልም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው – (አሚኮ)
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል