በሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ላልይበላ ጠቅላላ ሆስፒታል በከተማዋ ለአራት ወራት ያህል ከርሞ የነበረውን የሽብር ቡድኑን የጭካኔ በትር ተጋፍጦ አገልግሎቱ ሲሰጥ መቆየቱን የሆስፒታሉ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።
ግፈኛውና አሸባሪው ቡድን የሆስፒታሉን ባለሙያዎች ከመደብደብ አልፎ የሆስፒታሉን ቁሳቁስ በመዝረፍ እና በመሰባበር የክፋቱን ጥግ አሳይቷል ብለዋል።

ሆስፒታሉን በተወካይ ሥራ አስኪያጅነት እየመሩ የሚገኙት ባዮ ሜዲካል ኢንጂነር ሲሳይ ታመነ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ሆስፒታሉ በአካባቢው ላሉ 300 ሺ የኅብረተሰብ ክፍል አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ወራሪው ኃይል ወደ ላልይበላ ከተማ ከገባ ጀምሮ ለአንድ ሁለት ቀን ያህል ሥራ አቋርጦ የነበረ ቢሆንም ወዲያው ኮሚቴ ተዋቅሮ የሽብር ቡድኑን የግፍ በትር በመቋቋም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወደሥራ ገብቷል።
በሆስፒታሉ የተቋቋመው ኮሚቴ፣ ለጊዜው የተወሰኑ ዲፓርትመንቶችን በማጠፍ በተለይ ወላጆችንና ስር የሰደደ (ክሮኒክ) ችግር ያለባቸውን ህሙማን አሸባሪው ኃይል የሚያደርሰውን ፈተና በመጋፈጥ ሲያገለግሉ መቆየታውን ተወካይ ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
እርሳቸው እንዳሉት፤ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መንገድ ላይ እየተደበደቡም ቢሆን ወራሪው ኃይል ከተማውን ተቆጣጥሮት በቆየባቸው በአራት ወር ውስጥ ወደ 34 እናቶች በኦፕራሲዮን እንዲወልዱ ማድረግ ችለዋል። ከአምስት ሺ በላይ የሆኑ ስር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ተስተናግደዋል። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ስራውን ሳያቋርጥ ቆይቷል።
በወራሪው ኃይል ተደፍረው ከመጡ ሴቶች መካከል ሁለት ታካሚዎች ሲሆኑ፣ አንዷ እመጫት መሆኗን የተናገሩት ተወካዩ፣ በኑሮ ደረጃዋም ዝቅተኛ ከሚባሉት መካከል የምትመደብ መሆኗ ተናግረዋል። ተደፍረው የመጡ ሴቶች በተገቢው መንገድ አገልግሎት እንደተሰጣቸውም አመላክተዋል።
በሆስፒታሉ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አቤኔዘር ፈንቴ በበኩላቸው፤ ሆስፒታሉ በከባድ ፈተና ውስጥ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ነው ብለዋል። በተለይ የሆስፒታሉ የፋርማሲ ባለሙያዎች ይደበደቡ እንደነበርም ተናግረዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የወራሪውን ዱላ ሳይፈሩ ተቋቁመው አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ኮሚቴ ሰብሳቢው ገለጻ፤ አንዲት እናት ልትወልድ ወደሆስፒታሉ መጥታ እርሷን ለማዋለድ በሚደረገው ሂደት ለጄኔሬተር ናፍጣ መጠቀም እየተፈለገ ወራሪው ኃይል ግን ናፍጣውን በጉልበት ይወስድ ነበር። ከሆስፒታሉ አውቶቡሶች ውስጥ ሁሉ ናፍጣውን በቱቦ እየሳበ ይጠቀም ነበር።
ሆስፒታሉ ከዚህ በኋላ በርካታ ወረዳዎችን የሚያገለግል እንደመሆኑ የክልል ጤና ቢሮ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አቶ አቤኔዘር ጥሪ አስተላልፈዋል። ሆስፒታሉ በመከራ ውስጥ ሆኖ አገልግሎት ሲሰራ በተመቻቸ ሁኔታ አለመሆኑም መታወቅ አለበት ብለዋል።
በሆስፒታሉ የሐብት አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መለሰ አሰፋ በበኩላቸው፤ ወራሪው ኃይል ሆስፒታሉን ካምፕ አድርጎ መክረሙን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ለአንድ ሁለት ቀን አገልግሎት መስጠት ያቆመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ ምንም አይነት መድኃኒት እንዳልነበር ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ የላስታ ላልይበላ ተወላጆች አስቸኳይ እርዳታ በማቋቋም መድኃኒት ተገዝቶ ከዞኑ መቄት ከሚባል ወረዳ ከፍላቂት ከተማ መድኃኒት ተገዝቶ በአህያ ተጭኖ መምጣቱን አስታውሰዋል።
በዚህ መሃል ግን ስር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ይሞቱ እንደነበር አስታውሰዋል። የቅዱስ ላልይበላ ሆስፒታል ክፍት ነው በሚልም ከወልዲያ፣ ከቆቦና ላስታ ድረስ ሰዎች መጥተው ይታከሙ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ መለስ፣ እንዳሉት፣ በወቅቱ ወደ13 የስራ ክፍሎች በወራሪው ኃይል ተሰባብረዋል። ማህበረሰቡን ሲያገለግሉ የነበረው የጥገና ስራ በማካሄድ ነው። በርካታ የሆስፒታሉ እቃዎች በሽብር ቡድኑ አባላት ተሰርቀዋል። በተለይ የህክምና አላቂና ቋሚ እቃዎች ተወስደዋል።
አስቴር ኤልያስ አዲስ ዘመን ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
- Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on EgyptIt was striking that, at the height of Israeli diplomacy’s preoccupation with tracking the… Read more: Growing relations between Israel and Ethiopia: between military deals, intelligence influence, and an eye on Egypt
- የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራኢትዮጵያ ከጅቡቲ ማግኘት የነበረባትን የባህር በር ሳታገኝ እንዲሁም በተመሳሳይ ኤርትራ ስትሄድ ለመውጪያም ሆነ ለመግቢያ… Read more: የመጨረሻው መጀመሪያ የማሪያም መንገድ – ራስ ዱሜራ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው።… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ
- UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan AuthorityMore stories BRICS Officially Announces Financial System Similar to SWIFTJuly 27, 2024 more americans… Read more: UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan Authority
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም” ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነውእድሜው ለጋ ሀሳቡ ትልቅ ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን አሻግሮ ማየት ችሏል። ኃይለሥላሴ አበራ… Read more: ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው