ቁጥራቸውን መገመቱ ለጊዜው ይቆይና አስተያየት የሰጡት ሁሉም ምርኮኞች “ተገደን ነው” ሲሉ ለወረራ እንዴት እንደመጡ ተናግረዋል። ከትግራይ ተነስተው ያለፉበትን ከተሞችና መነድሮች የፈጸሙት የተከታተሉና እየተከታተሉ ያሉ ” ተገደው ሊመጡ ይችላሉ። ተገደው ግን ሱሪ አልፈቱም። እህቶቻችንና እናቶቻችንን አልደፈሩም። ተገደው ከተሞችን ወደ አመድነት አይቀይሩም። ተገደው አይዘርፉም። ተገደው በጅምላ ሰላማዊ ሰዎችን አይጨፈጭፉም” የሚሉና በርካታ መሰል ጥያቄዎች እየተነሱ ነው። በተመሳሳይ ሃሳቡን የሚጋሩ ግን በዚህ ተግባር የተሰማሩት ጥቂቶች ናቸው እነሱን መንቀስና ከሌሎቹ የመለየት ስራ ለመንግስት መተው እንደሚሻል የሚናገሩም አሉ።
ከዚህ ቀደም በካሳጊታ ግንባር እጅ ከሰጡ መካከል ” ድፈሩ፣የቻላችሁትን ዝረፉ፣አውድሙ፣ ግደሉ ተብለናል… በገባንበት ከተሞች ፋብሪካና የላቦራቶሪ መሳሪያዎችን የሚፈቱና የሚጭኑ ባለሙያዎች አሉ” ሲሉ ምን ተብለው እደመጡና እግራቸው በገባበት ሁሉ የተባሉትን ስለመፈጸማቸው ምስክርነታቸው ሰጥተው ነበር።
ቀደም ሲል “እንበቀላለን” እንደተባለው መደረጉና ” ለሁለት ዓመት የሚሆን ቀለብና በጀት ከአማራ ክልል ለማጓጓዝ የተያዘው ዕቅድ በዕቅዱ አውጪዎችና አስፈሳሚዎች ዘንድ እንደ ታላቅ ስኬት ተቆጥሮ፣ እያወደሙ በተረማመዱበት ምድር ላይ መንግስት ለመሆን ሲመኙና በሳምንታት ውስጥ ይህንኑ አሳክተው እንደሚነግሱ ሲያዜሙ ጭፈራና ከበሮ እንጂ ” የለም ይህ አያዋጣም” ያለ እንዳልነበር በብስጭት ሲገለጽ ከርሟል። ይህ ቁጣ የወለደው እሳት ክንድ ነበላባል ሲያወርድ ለትግሬ ወራሪዎች ቀሪ ሃብት ሆኖ የታየው ” በገቡበት ከተሞች የዘርፏቸው አዳዲስ ልብሶችን ተላብሰው እጅ ሲሰጡ መታየታቸው ነው” ሲሉ በማህበራዊ ገጾቻቸው በብዛት የጻፉ ቁጣቸው ቀላል አይደለም። ይህ ስሜት ስጋት የሆነባቸውም አሉ። ስጋታቸውንም እየገለጹ ነው።
ሰሞኑንና ከዚህ ቀደም በተለቀቁ ስፋራዎች በግልጽ በፊልም ማስረጃ እንደታየው በተመሳሳይ ጅምላ ግድያ፣ ዘረፋ፣ አስገድዶ መድፈር፣ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ማውደም፣ ትምህርት ቤቶችን አመድ ማድረግ፣ ክሊኒኮችና ሆስፒታሎችን ማፈራርስ … መፈጸሙን ዓለም ዓቀፍ ተቋማትን ጨምሮ በገሃድ ” ሰው ከሆነ የማይጠበቅ” ሲሉ ኮንነዋል። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ የትግሬ ወራሪ ሃይል ” ለምን ከክልሉ ወጥቶ በዚህ ደረጃ አገር ያወድማል፣ ንብረት ይዘርፋል? እንዲህ ያለ የሽሮና እንኩሮ ዝርፊያ ለስማችን አይመጥንም፣ አሳፋሪ ነው፣ ንጹሃንን ለምን ትገድላላችሁ፣ ሴቶችን ትደፍራላችሁ” ብለው የተቃወሙ አልተሰሙም። ይልቁኑም ” ሸዋ ገባን እኛ ልዩ ጀግና ነን” የሚል ቀረቶ ነበር የሚሰማው።
ያ ሁሉ አልፎ ዛሬ ” ተገደን ነው” የሚሉት ምርኮኞች ” ፍላጎቱ ከሌላቸው አፋርና አማራ ክልል ሲገቡ ለምን እጅ አልሰጡም? አናወድምም፣ አንዘርፍም? እህቶቻችንና እናቶቻችንን እንደ እንሣ በደቦ አንደፍርም አላሉም” ሲሉ ዛሬ ነገሮች ከአቅም በላይ ሲሆን “ተገደን ነው” ማለታቸውን ሙሉ በሙሉ ለመቀበል እንደሚያንቃቸው የሚገልጹ በርካታ ናቸው።
“በጋሸና ወራሪው የትግራይ ሃይል ብጥቅሉ ፵0 የሚሆኑ ዜሆችን: ሲመታና ሲሸሽ በዛ ቅጽበት ብቻ አስራ ስድስት ነጹሃንን እንዴት አንድ ቤት ዘግቶ እንደጨፈጨፈ ፊልሙን ማየት በቂ ነው” የሚሉ ወገኖች ” በደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ወልደያና ሌሎች ስፍራዎች የሆነው ይፋ ሲሆን አንድ ላይ ተዳምሮ የተጎጂውን ስሜት ሲግልና ልኬቱን ሲያልፍ እንዴት ማስታመም ይቻላል? እንዴትስ ተደርጎ ይበርድ ይሆን?” ሲሉ ስጋታቸውን የሚገልጹ ” የትግራይና የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀጣይ እንዴት ተማምነው ሊቀጥሉ ይችላሉ? ምን የሚያይዛቸው ነገር አለ? ምን በጎ ነገር ተረፈና ወደ ቀድሞ መተሳሰባቸው ሊመለሱ ይችላሉ? ድህረ ጦርነቱ ከጦርነቱ ወቅት በላይ የከፋ ይሆናልና ከወዲሁ ለጊዜውም ቢሆን ፖለቲካዊ ውሳኔ ግድ ነው” የሚሉ ብቅ እያሉ ነው። የመንግስት ሃይሎች ወይም ጥምር ሃይሎች ዳግም በሚቆጣጠሯቸው ከተሞች ህግ እንዳይፋለስና ስሜታዊነት እንዳይታይ ጥንቃቄ እንዲደረግም የሚያሳስቡ የወደፊቱን የሚያስቡ ጥቂት አይደሉም።
ምንም እንኳን ትህነግ መላውን የትግራይ ሕዝብ የማይወክል፣ ለራሱ በሚጠቅመው መልኩ ሕዝቡን ጥላቻ አስታጥቆ ለፈለገው ዘመቻ ያመቻቸ መሆኑ ቢገለጽም፣ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድመው በማሰብ ገና ከጅምሩ በገሃድ ወጥተው የተቃወሙ አለመኖራቸው ልዩነቱን እንዳሰፋው፣ የአልጃዚራው ሪፖርት “ሃዘኔታ የሚባል ነገር የነጠፈበት” ሲል ውጊያውን እንደገለጸው ከትግራይም ይሁን ከመካከል አገር አዲስ አሳብ ይዘው የሚነሱ የአደጋ ጊዜ መድሃኒት የሚሆኑ ታላላቆችም ይሁን የፖለቲካ ድርጅቶች አለመደመጣቸው ስጋቱን ያንረዋል።
ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ትህነግ ራሱ ያዘጋጀው ህግ በሚፈቅደው መሰረት መገንጠል ከፈለገ ማንም እንዳልያዘው፣ ነገር ግን በህጋዊ ደረጃ ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ አንስተው በገሃድ መናገራቸው ቁጣ ያስነሳው ” እንገነጠላለን፣ ኢትዮጵያዊ አይደለንም” በሚሉት ዘንዳ መሆኑ ” ሰዎቹ ምን እንደሚፈልጉ ግራ ያጋባል” የሚሉ ወገኖች ” አገር ለመምራት ያስባሉ እንዳይባል በሚዲያቸው ‘ በቁሜ ኢትዮጵያ የምትባል አገር ስትፈርስ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም’ ይላሉ። በወረራ የደረሱበትን ስፍራ ሁሉ ያወድማሉ፤ እንዴት እንመናቸው” ሲሉ ሌላ ግራ የሚያጋባና የመቀራረበን ጉዳይ ጭራሽ ውሃ የሚችለስ ትዝብት ያስቀምጣሉ።
በዚህና በሌሎች መሰረታዊ መረጃዎች ታጅበው የሰሞኑንን ምርኮና የምርኮኞችን ቃል ህዝብ እየተወያየበት ነው። በምንም ይሁን በምን ግን እጅ መስጠትና ጦርነቱን መጨረስ አልጃዚራ ” ለምን ህጻናት እንደዚህ እንደሚማገዱ አልገባኝም” ብሎ እጅ መስጠቱ እንደሚመረጥ አስተያየቱን እንዳሰፈረው እጅ መስጠት ብዙ ስጋቶችን ሊቀይር እንደሚችል በርካቶች ያምናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ገና ቀጣይ ትግልና ሌላ ውድመትን የሚናፍቁ አሉ። ለአዲስ ስልታዊ ጥቃት ዝግጅት ምን ያህል ታዳጊዎችና አባቶች እንደተዘጋጁ ባይታወቅም የረገበ ድምጽ እየተሰማ ነው። ከሁሉም በላይ ” ሰው እንዲህ ባለ መልኩ ሲረግፍ አይቼ አላውቅም” እንዳለው የአልጃዚራ ( እነማን እዳለቁ በግልጽ ተናግሯል) ዘራፍ ማለቱ ሲቀር ” ተራ መዛልፍ ውስጥ ተገብቶ በእልቂት ላይ ማላገጥ ያሳዝናል” የሚሉ የንጹሃን አባቶችና እናቶች ጸሎት አንድ መላ ሲፈጥር ሁሉም የእጁን እንደሚያገኝ ይናገራሉ። ለሁሉም ግን ከታች ስለምርኮኞች የተዝገበ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የጠላት ኃይል እጁን እንዲሰጥ ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ የአሸባሪው የትህነግ ወራሪዎች እጃቸውን እየሰጡ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ግንባር አምርተው የወገንን ጦር መምራት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ በሁሉም ግንባር ድል እየተመዘገበና የጠላት ሀይል እየተበታተነ ነው።
‘በዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት’ የወገን ጦር ድል በድል እየደራረበ ሲገሰግስ በአንፃሩ የጠላት ኃይል በየጦር ግንባሩ ሽንፈትን እየደረሰበትና እየተደመሰሰ ይገኛል።

ለአብነትም በጋሸና፣ በሸዋ፣ በወረኢሉ፣ በጭፍራ እና በሌሎች ግንባሮች የወገን ጥምር ጦር ባደረገው ተጋድሎ በርካታ ከተሞችን ከወራሪው ኃይል ነፃ ማድረግ ችሏል፣ የወራሪው ቡድንም ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት በመፈርጠጥ ላይ ይገኛል።
ከመደምሰስ የተረፈው የወራሪና ዘራፊ ቡድኑ ኃይልም እየተበታተነ ሲሆን የወገን ጦር በየግንባሩ የተበታተነውን የጠላት ኃይል የመልቀም ስራዎችን አጠናክሮ ቀጥሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ራዕይና ግቡ በማይታወቅ ጦርነት በዕውር ድንብር ጁንታው ያሰለፋቸው የትግራይ ወጣቶች እንደ ቅጠል እየረገፉ መሆኑን መግለፃቸው አይዘነጋም።
በዚህም ወጣቶች በማያውቁት አካባቢና ራዕይ በሌለለው ጦርነት ገብተው እንዳያልቁ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊትና ለክልል የፀጥታ ኃይሎች እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።
የትግራይ እናቶችም ልጆቻቸው ራዕይ በሌለው ጦርነት እንዳያልቁ “ልጆቻችን የት ደረሱ” ብለው መጠየቅ እንዳለባቸው መግለፃቸው አይዘነጋም።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ ተከትሎም በሺዎች የሚቆጠሩ የሽብር ቡድኑ ለውጊያ ያሰለፋቸው ታጣቂዎች እጃቸውን ለወገን ኃይል እየሰጡ ነው።
እጃቸውን የሰጡት ምርኮኞቹም ባለማወቅና በመገደድ ወደ ውጊያ መሰለፋቸውን ገልፀው፤ ቡድኑ በደረሰበት ሽንፈት እጅ ለመስጠት መገደዳቸውን ገልፀዋል።

የሽብር ቡድኑ አባላት ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች በቤተሰብ ልጅ አምጡ እየተባሉ በአሸባሪው ተገደው ቢሰለፉም በእስካሁኑ ድርጊታቸው ተፀፅተው ይቅርታ ጠይቀዋል።
አሸባሪው ቡድን የሚያሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን አሸባሪ ቡድኑ ተሸንፏል ብለዋል።
በርካታ ጓደኞቻቸው በከንቱ ሕይወታቸውን የሚናገሩት ምርኮኞቹ፤ እነርሱ ግን እጃቸውን ለመከላከያ በመስጠታቸው እድለኞች ነን ብለዋል።
እጅ ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊትና በህብረተሰቡ ለተደረገላቸው እንክብካቤ አመስግነዋል።
ሌሎች የትግራይ ወጣቶችም በአሸባሪው ቡድን እያሸነፍን ነው በሚል በሚዲያ በሚነዛው ሀሰተኛ መረጃ እየተደናገሩ ለውጊያ እንይሰለፉ፣ ውጊያ ላይ የተሰለፉትም እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።
የትግራይ ወጣቶች በጁንታው ጦርነት ከመማገድ ይልቅ ለወገን ጦር እጃቸውን በመስጠት ሕይወታቸውን ማዳን እንዲችሉ የኃይማኖት አባቶች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ ቀርቧል።
በየግንባሩ ተሸንፎ የተበታተነው የጠላት ኃይል የዘረፈውን ሀብት ይዞ እንዳይሸሽ ህብረተሰቡ አካባቢውን ተደራጅቶ እንዲጠብቅ፣ ብሎም የወራሪው ኃይል አባላትን እየማረከ ለመከላከያ ሰራዊት እንዲያስረክብ መንግስት ጥሪ ማቅረቡን ኢዜአ ዘግቧል።