” ከአዲሱ የኢትዮጵያ ካርታ ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጨዉ መረጃ ተቀባይነት የሌለዉና መወገዝ ያለበት ነዉ።”-የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን
የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በሃገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ስራና በአጠቃላይ የኮሚሽኑ ሁኔታ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ ኮሚሽኑ እስካሁን ደረስ ሲሰራ የነበረዉን አጠቃላይ የጥናትና ምርምር ስራ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።
የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ከአስተዳደራዊ ወሰኖች: ከማንነትና ራስን በራስ ከማስተዳደር ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምር በማድረግ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ ምክረ ሃሳቦችን ለማዘጋጀትና ለማቅረብ የተቋቋመ ኮሚሽን ነዉ።
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ እንደተናገሩት ከሰኔ 2012 ጀምሮ በአስተዳደር ወሰን: የማንነትና ራስን በራስ የማስተዳደር ጉዳዮች ላይ አገር አቀፍ የጥናትና ምርምር ስራ ሲያከናዉን እንደነበር ተናግረዋል።
ጥናትና ምርምሩ በፊንፊኔ ዩኒቨርስቲ ባለቤትነት የሚመራ መሆኑን የተናገሩት ሰብሳቢዉ ሌሎች ችግሮች ባሉባቸዉ አካባቢዎች 28 ዩኒቨርስቲዎች የተሳተፉበት መሆኑን ጠቅሰዋል።
በጥናቱ 56 ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የተሸፈኑና 70 ተመራማሪዎችና በርካታ መረጃ ሰብሳቢዎች የተሳተፉበት መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ጣሰዉ ገብሬ በተለያዩ ሁኔታዎች ማለትም በድርሳናት ዳሰሳ/ክለሳ: በቁልፍ መረጃ ሰጪ ቃለ ምልልስ: የትኩረት ቡድን ዉይይት እና ቤት ለቤት በታብሌት የታገዘ የቤተሰብ መረጃ መሰብሰቡን ጠቁመዋል።
በማንነት: ራስን በራስ በማስተዳደር: በአስተዳደር ወሰን እና የሕግና ፖሊሲ አማራጮች ዙሪያ አራት የተጠቃለለ የጥናትና ምርምር ሪፖርት መቅረቡንም ገልጸዋል።
በተደረገዉ ጥናትና ምርምር ዉስጥ ከመዋቅራዊ አደረጃጀት ጋር የተገናኘ ግኝት የሚተካተተበት መሆኑን እና በቀረበዉ ሃገራዊ የጥናት ዉጤት ላይ ተከታታይ የባለድርሻ አካላት ዉይይትና ግብአት በማካተትና በማዳበር ይፋ እንደሚደረግም በመግለጫቸዉ ጠቅሰዋል።
ጥናትና ምርምሩ ለ18 ወራት ሲካሄድ የነበረ ሲሆን ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ከተመረጡ 68 ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች መካከል በ12 ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በጸጥታ ችግሮችና በተያያዥ ምክንያቶች ጥናትና ምርምሩ አልተካተተም።
የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አዲሱ የኢትዮጵያ ካርታ ነዉ በማለት በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቀዉ መረጃ መሠረተ ቢስና መወገዝ ያለበት ነዉ ብለዋል።
ወንድማገኝ አሰፋ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው ሁሉ እረፍት… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው። ዶክተር ብሩክ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ነው” ሲሉ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the Africa program… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር ዩናይትድ ለዩሮፕያን… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት ከአሰልጣኞች አስከ… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ
- UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan AuthorityMore stories One third of EU countries see double-digit inflationMay 22, 2022 German navy chief resigns… Read more: UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan Authority
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም” ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጫ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነውእድሜው ለጋ ሀሳቡ ትልቅ ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን አሻግሮ ማየት ችሏል። ኃይለሥላሴ አበራ ይባላል። ተወልዶ… Read more: ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው