ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ የተሰጠ መግለጫ ቁ.6
ታኅሣሥ 14 ቀን 2014 ዓም
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ ማምሻውን ባደረገው ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ አፈጻጸሙን ገምግሟል፡፡ በግምገማውም በግንባር ለተገኘው ድል የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውን፣ ሞያቸውንና ገንዘባቸውን ለሀገራቸው ሳይሰስቱ በመስጠት የፈጸሙት የደጀንነት ገድል አኩሪ መሆኑን ተመልክቷል፡፡ ለዚህ የሕዝባችን ከፍተኛ አስተዋጽዖ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ ምስጋና ያቀርባል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዙ የተገኙ ድሎቻችንን ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን፣ ለዚህም በማኅበረሰቡ፣በአስተዳደር አካላትና በጸጥታ አካላት መወሰድ የሚገባቸውን ተግባራት በመለየት የሚከተሉትን ትእዛዛት ሰጥቷል፡፡
- ከሕዝብ ችግር ለመጠቀም የሚፈልጉ አንዳንድ አካላት፣ ወደ ሀገር ቤት የሚመጣውን የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ምክንያት አድርገው ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ለማድረግ መነሣሣታቸው ተደርሶበታል፡፡ ይህ ደግሞ ድኻውን የኀብረተሰብ ክፍል ስለሚጎዳ በእነዚህ ሕገ ወጥ አካላት ላይ መንግሥት አስፈላጊውን ቁጥጥርና ሕግ የማስከበር ተግባር እያከናወነ ነው፡፡ በመሆኑም በየአካባቢው በመሠረታዊ ፍጆታዎችና አገልግሎቶች ላይ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለው የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉና ያለ አግባብ በሚያከማቹ አካላት ላይ፣ የንግድ ቢሮዎችና የጸጥታ አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ ታዝዘዋል፡፡
- ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በወጡት አካባቢዎች አስተዳደርን መልሶ የማቋቋምና መሠረታዊ የኅብረተሰብ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ያለው እንቅስቃሴ ወጥ በሆነ ሁኔታ እየተተገበረ አለመሆኑን ገምግሟል፡፡ በዚህም ምክንያት የጸጥታ ችግሮችና የወንጀል ተግባራት ነጻ የወጣውን ማኅበረሰብ እያማረሩት ነው፡፡ በመሆኑም የአማራ ክልል መንግሥት የየአካባቢውን አስተዳደር በአስቸኳይ በብቁ አመራሮች እንዲያደራጅ፤ መደበኛ የፖሊስ ኃይሎችም የተጠናከረ ሥራ እንዲጀምሩ እንዲያደርግ፣ እነዚህን ለማድረግ ባልተቻለባቸው ቦታዎች የሚንቀሳቀስ የመከላከያ ኃይል፣ ነጻ በወጡ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በሚፈጥሩ አካላት ላይ፣ ሕጋዊ ርምጃ እንዲወስድ ታዝዟል፡፡
- አሸባሪው ኃይል ተቆጣጥሯቸው በነበሩ አካባቢዎች፣ ባደራጃቸው ሕገ ወጥ መዋቅሮች አማካኝነት፤ የቀደመው አስተዳደር ይጠቀምባቸው የነበሩትን ማኅተሞች በመጠቀምና አዳዲስ ሕገ ወጥ ማኅተሞችን በመቅረጽ ሕገ ወጥ መታወቂያዎችን መስጠቱ፤ የተለያዩ ሕገ ወጥ ሰነዶችን ማዘጋጀቱ ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም በየአካባቢው የተቋቋሙ የመስተዳድር አካላትና የጸጥታ ኃይሎች አሸባሪው ሕወሐት ያስቀረጻቸውን ማኅተሞች፣ መታወቂያዎችና ሌሎች ሰነዶች እንዲያመክኑ ታዝዘዋል፡፡
- ነጻ በወጡ አካባቢዎች ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ዝውውሮችና ጠላት አንጠባጥቧቸው የሄዱ የጦር መሣሪያዎች በመኖራቸው ለሕዝብ ሰላምና ደኅንነት ሥጋት ሊሆኑ የሚችሉ አዝማሚያዎች መኖራቸው ተደርሶበታል፡፡ በመሆኑም የየአካባቢው ልዩ ኃይልና ፖሊስ በአስቸኳይ እነዚህ ጉዳዮች ሥርዓት እንዲያሲዙ ታዝዘዋል፡፡ እነዚህ ኃይሎች ባልተጠናከሩባቸው አካባቢዎችም የመከላከያ ኃይል አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ተሰጥቷል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ዕዝ
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ አሁን ላይ የሆነው… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ አድናቆት እየተቸረው ነው።… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior fellow in the… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን መውሰድ የቻለው ማንችስተር… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ የበላይነት በአውሮፓ ለማሳየት… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ
- UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan AuthorityMore stories EU launches reset with Africa after pandemic disruptionFebruary 19, 2022 France reacts… Read more: UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan Authority
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም” ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ የተዋቀረው የትግራይ ጊዚያዊ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነውእድሜው ለጋ ሀሳቡ ትልቅ ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን አሻግሮ ማየት ችሏል። ኃይለሥላሴ አበራ… Read more: ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው
- Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s SuccessEthiopia will have a very strong market and economy within a relatively short time… Read more: Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
- Port Sudan endures fresh drone attack amid fighting between military rivalsMore stories UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan AuthorityMay 8, 2025… Read more: Port Sudan endures fresh drone attack amid fighting between military rivals
- Ethiopia has highest rate of scientific paper retractionMore stories Port Sudan endures fresh drone attack amid fighting between military rivalsMay 8,… Read more: Ethiopia has highest rate of scientific paper retraction