በአንጸባራቂ ድል ወደፊት እየገሠገሡ የሚገኙት ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች አብዛኞቹን የዋግ ኅምራ አካባቢዎች ነጻ በማውጣት የዞኑን ዋና ከተማ ሰቆጣን ተቆጣጥረዋል፡፡
አካባቢው ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በሚወጣበት ጊዜ የዋግ ኽምራ ሚሊሻዎች አስደናቂ ጀብዱ የፈጸሙ ሲሆን፣ የአካባቢው ሕዝብም ከመከላከያ ሠራዊትና ከአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመጣመር ደጀንነቱን በብቃት አሳይቷል፡፡ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ የጸጥታ ኃይሎች ቀሪዎቹን ቦታዎች እያጸዱ፣ የፈረጠጠውን የአሸባሪውን ጀሌ እየደመሰሱ፣ ወደ አበርገሌ በመገሥገሥ ላይ ይገኛሉ፡፡
በተያያዘም ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊትና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች፣ በቆቦ ግንባር በአንድ በኩል ዋጃና ጥሙጋ ላይ የሠፈረውን የጠላት ኃይል በመጥረግ ወደ አላማጣ ከተማ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ተኩለሽን ተቆጣጥረው በማጽዳት፣ ወደ መረዋና ኮረም እየገሠገሡ ይገኛሉ፡፡
በእሳታማው የጀግኖች ክንድ የተደቆሰው አሸባሪው ሕወሐት፣ ተቸካይና ኋላ ቀር በሆነ የጦር ዘይቤ፣ ዕብሪትን እንደ መሣሪያ በመጠቀም፣ ከገባባቸው የአማራና የአፋር ክልል አካባቢዎች እንደገባ መውጣት አቅቶት፣ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሣራ ደርሶበት ተደመስሷል፡፡
ይሄንን ሐፍረቱን መሸፈን ሲያቅተው በአንድ በኩል ለሰላም ሲል የወጣ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሽንፈቱ ውኃ የማይቋጥር ምክንያት እያቀረበ፣ አድኑኝ የሚል እሪታ እያሰማ፣ በለመደው ውሸት የትግራይን ሕዝብና የዓለምን ማኅበረሰብ ለማደናገር እየሞከረ ይገኛል፡፡
በዚህ ጦርነት የመጀመሪያው ገፈት ቀማሽ የሆነውና አሸባሪውን ሕወሐት በጀግንነት የታገለው የዋግ ኅምራ ሕዝብ፣ በጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ በአማራ የጸጥታ ኃይሎች፣ እንዲሁም በራሱ በዋግ ኅምራ ሕዝብ ትግል፣ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ በመውጣቱ፣ በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡
ነጻነታችንን የምናስከብረው በተባበረው ክንዳችን ነው!
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
- “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳየትህነግ ቃል አቀባይ በመሆን ጦርነቱን በፕሮፓጋንዳ ሲያቀጣጥሉት የነበሩት አቶ ጌታቸው ረዳ… Read more: “ ንስሃ ገብቻለሁ እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል ፤ ሲያፈገፍጉ የተረሸኑ ታጋዮች አሉ ” አቶ ጌታቸው ረዳ
- ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪምሰሞኑን ከሚሰማው የሐኪሞች የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ጎን ለጎን የተሰማው ዜና ሰፊ… Read more: ለምህላቸው ከሚኖሩት መካከል – ሰርጉን ጥሎ ነብስ የታደገው ሐኪም
- ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመበጦርነቱ ወቅት ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፕሮፌሰር ክንድያ ገብረህይወት “የደብረፅዮን ቡድን ከተደጋጋሚ… Read more: ፕሮፌሰር ክንድያ የደብረፅዮንን ቡድን “ካለፈ ስህተቱ የማይማር ተቸካይ ” አሉት፤ ፋኖ የደቦ አመራር ሰየመ
- The Wars We Still Can Stop Cameron Hudson (New York TimesMay Opinion Mr. Hudson is a senior… Read more: The Wars We Still Can Stop
- ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማልእየተንገዳግደ የፕሪማየር ሊጉን ዋናጫ ባያነሳም ኤፍ ኤ ካፕን ጨምሮ ሌሎች ዋንጫዎችን… Read more: ዩናይትድ ለፍጻሜ አለፈ ቶተንሃምን ይገጥማል
- ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂበኳታራውያን ባለሀብቶች የሚተዳደረው የፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ በሀገር ውስጥ ያለውን ተደጋጋሚ… Read more: ያለ ኪልያን ምባፔ ለሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜ የደረሰው ፒኤስጂ
- UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan AuthorityMore stories UK announces controversial plan to send asylum-seekers to RwandaApril… Read more: UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan Authority
- የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም” ማናቸውም የውጭ ግንኙነቶች ማካሄድ ስህተት ብቻ ሳይሆን አደገኛም እንደሆነ ጠቅሶ አዲስ… Read more: የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሻዕቢያ ጋር ግንኙነት ለጀመረው ቡድን ማስጠንቀቂያ ሰጠ፤ “አላማው ያልታወቀ ግንኙነት ተቀባይነት የለውም”
- ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነውእድሜው ለጋ ሀሳቡ ትልቅ ነው። ዛሬ ላይ ሆኖ ነገን አሻግሮ ማየት… Read more: ተወንጫፊ የጦር መሳሪያ የሰራው የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነው
- Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s SuccessEthiopia will have a very strong market and economy within a… Read more: Ethiopia: Israel Foreign Minister Says His Country Wants to Be Part of Ethiopia’s Success
- Port Sudan endures fresh drone attack amid fighting between military rivalsMore stories Port Sudan endures fresh drone attack amid fighting between… Read more: Port Sudan endures fresh drone attack amid fighting between military rivals
- Ethiopia has highest rate of scientific paper retractionMore stories UAE Does Not Recognize the Decision of Port Sudan… Read more: Ethiopia has highest rate of scientific paper retraction